TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በደቦ ፍርድ ሰው ተገደለ⬇️

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ከተማ ቤተ ክርስቲያ ግቢ ውስጥ በተፈጸመ የደቦ ፍርድ የአንድ ግለሰብ ሕይወት #አለፈ፡፡ ግድያው የተፈጸመው ቅዳሜ ነሐሴ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 እስከ 12፡00 ሰዓት መሆኑን ሪፖርተር ከፖሊስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ላይ ከቡሬ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኘው የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን የእሳት ጭስ መታየቱን፣ እሳቱን ለማጥፋትም ከቤተ ክርስቲያኑ በቅርብ ርቀት ከሚገኘው የቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞችን ጨምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መትመማቸውን፣ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ዋና ኢንስፔክተር አበበ አጥቁ አረጋግጠዋል፡፡

በቤተ ክርስቲያኑ #ማህሌት ተብሎ ከሚጠራው ክፍል ሳይነሳ እንዳልቀረ የተገመተው እሳትም፣ በሕንፃው ላይ ብዙም ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል፡፡

በቦታው የተሰበሰቡ የአካባቢው ነዋሪዎች እሳቱ ሆን ተብሎ በሰው የተነሳ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረስ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ያሉ የአብነት ተማሪዎችን ማጠያየቅ እንደጀመሩ፣ ከዚያም በቤተ ክርስቲያኑ ተጠልሎ ነበረ የተባለን ግለሰብ ጥያቄ መጠየቅ መጀመራቸውን #ከቡሬ ከተማ የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የሚማሩ የአብነት ተማሪዎች ግለሰቡን እንደሚያውቁት ሲጠየቁ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ከመጣ ቀናት እንደተቆጠሩና የእግዜር እንግዳ መሆኑን መናገራቸውን ገልጸዋል ሲሉ፣ የቡሬ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ቡድን መሪ ወ/ሮ ጉዳይ መለሰ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ሟችን ‹ፀጉረ ልውጥ› በማለት እንደያዙትና ጥቃት እንደሰነዘሩበት የቡድን መሪዋ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስ በበኩሉ መጀመርያ ላይ ሦስት አባላቱን ወደ ቦታው አንቀሳቅሶ እንደነበር ዋና ኢንስፔክተር አበበ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ይህ ችግር እንዳለ 12 ሰዓት አካባቢ ነው ሪፖርት የተደረገልን፤›› ብለዋል፡፡

ነገር ግን በሰዓቱ ግለሰቡን ‹ፀጉረ ልውጥ› ነው ብለውና ቃጠሎውን እንደፈጸመ አድርገው ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ውስጥ በድንጋይ ቀጥቅጠው መግደላቸውን ከዓይን እማኞች ለመረዳት ተችሏል፡፡

‹‹አባላቶቻችን በጥቃቱ ጊዜ ወደ ላይ በመተኮስ ግለሰቡን ለማዳን ሞክረው ነበር፤›› ያሉት ዋና ኢንስፔክተር አበበ፣ ‹‹የነበረው የሰው ብዛት ግን ከአቅማችን በላይ ነበር፤›› ሲሉ አብራርተዋል፡፡ ‹‹መጀመርያ ሦስት የፖሊስ አባላት ወደ ቦታው ተልከው ነበር፡፡ በተጨማሪም የቤተ ክርስቲያኑ ካህናት መስቀል አውጥተው ለመገዘትና ጥቃቱን ለማስቆም ሞክረው ነበር፤›› ያሉት ዋና ኢንስፔክተር አበበ፣ ይህም ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል፡፡ ‹‹ሌላው ቢቀር ሟችን መቃብር ቤት ውስጥ አስገብቶ ለመደበቅ ሁሉ ተሞክሮ ነበር፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ግድያው ከተፈጸመ በኋላ መረጃ ለመሰብሰብ መሄዳቸውን፣ ከቃጠሎው በፊትም ሆነ በኋላ ሟች  አብሯቸው እንደነበር የቤተ ክርስቲያኑ የአብነት ተማሪዎች እንደ ነገሯቸው ወ/ሮ ጉዳይ አስረድተዋል፡፡

‹‹በቦታው የነበረው #በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች (በአብዛኛው ወጣቶች) ነበሩ፡፡ በሻሸመኔ ተደርጎ እንደነበረው ዓይነት ድርጊት ለመፈጸም፣ ግድያው ከተፈጸመ በኋላ ደግሞ #የሟችን አስከሬን ተሸክመው ለመውሰድ ተሞክሮ የነበረ ቢሆንም፣ ከዞኑ በተላከ ተጨማሪ የፖሊስ ኃይል ድርጊቱን #ማስቆም ተችሏል፤›› ሲሉ በሥፍራው ተገኝተው የነበሩት የከተማው የብአዴን የሕዝብ ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ አቶ ግዛቸው ካሳዬ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

እሳቱ እንዴት ተነሳ ለሚለው በመጣራት ላይ መሆኑን፣ አስከሬኑን ተሸክመው ለመውሰድ ከሞከሩት ውስጥ ሁለት ወጣቶች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ #ግድያውን ያስተባበሩትን ለመያዝ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ዋና ኢንስፔክተር አበበ አስታውቀዋል፡፡ 

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የመቶ ሰማኒያ ዘጠኝ ሰዎች ህይወት #አለፈ። ከዋና ከተማዋ ጃካርታ መብረር ከመጀመሩ 13 ደቂቃ በኋላ በሰሜናዊ ጃቫ ደሴት #ከተከሰከሰው አውሮፕላን #የተረፈ ሰው አለመኖሩ የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልፀዋል።

ምንጭ፦ VOA አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia