TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወንድ ህፃናትን የደፈሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ ፦

#አርባ_ምንጭ :

በ10 ዓመት ህጻን ላይ የግብረ-ሰዶም ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አሳወቀ፡፡

ተከሳሽ አቶ ተመኘሁ ጣሰው የተባለ በከተማው የድልፋና ቀበሌ ነዋሪ የሆነ የ39 ዓመት ግለሰብ በቀበሌው ነዋሪ የሆነውን የ10 ዓመት ህጻን ላይ የግብረ - ሰዶም ወንጀል መፈጸሙን ፍርድ ቤቱ በሰነድና በሰው ማስረጃ አረጋግጧል።

ወንጀሉን ለየት የሚያደርገው በአከባቢው ያልተለመደ እና የግል ተበዳይን በተደጋጋሚ በማስፈራራት ተከሳሽ ወንጀሉን እየፈጸመ መቆየቱና በመጨረሻ በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ቀበሌ "ገሮ መኝታ ቤት" ወንጀሉን እየፈጸመ እያለ በአከባቢው ህብረተሰብ ጥቆማ ሊያዝ መቻሉ ነው።

በወንጀል ህግ ቁጥር 631 ንዑስ 1 ሀ መሠረት በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጣራት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።

#ማዕከላዊ_ጎንደር

በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዐቃቤ ሕግ መምርያ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመውን ግለሰብ በእስራት ቀጥቷል።

ተከሳሽ አቶ የምስራች ዓባይ ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 5:00 ላይ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሙሴ ባንብ ቀበሌ የ8 ዓመት ሕፃን ወንድ ልጅ አስገድዶ ደፍሯል፡፡

የሙሴ ባንብ ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት የተከሳሽን የወንጀል ድርጊት በሰው እና በሕክምና ማስረጃ ማረጋገጥ ችሏል፡፡

ተከሳሽ የወንጀል ሕግ ቁ631/1/ለ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡

መልዕክት ፦

ወላጆችና አሳዳጊዎች ህጻናት ለወንጀል ተጋላጭ እና ራሳቸውን ለመከላከል ስለማይችሉ የጥቃት ሰለባዎች እንዳይሆኑ የልጆቻቸሁን አዋዋል ልትከታተሉና ልትቆጣጠሩ ይገባል።

በህጻናት ላይ የተለየና አጣራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ለሚመለከተው አካል ጥቆማ ስጡ።

[ይህ መረጃ የተሰባጠረው ከአርባ ምንጭ ኮሚኒኬሽን ፣ የአርባ ምርጭ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት አቶ አለማየሁ አልታዬ እና ከአዲስ ዘይቤ /Addis Zeybe/ ደረገፅ ነው]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia