TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.3K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀዋሳ-VOA 24⬆️

በደቡብ ክልል ሐዋሳ ከተማ ሰዋች #ባልታወቁ አካላት መሽት #ተገለው እየተገኙ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።

የከተማዋ ፖሊስ ሁለት ሰዎች ተገለው መገኘታቸውን ገልፆ፣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ተናግሯል።

@tsegabwolde @tikahethiopia
ሞቶ የተገኘውና ወላጆቹ #አልቅሰው የቀበሩት ወጣት ከሳምንታት በኋላ ወደ ወላጆቹ ተመልሷል‼️
.
.
በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ አስተዳደር አንድ ወጣት ማንነታቸው #ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ ይገኛል፡፡ ይህም ከፖሊስ ጆሮ ይደርሳል፡፡

ጉዳዩን የሰማው ፖሊስ የሟችንም ሆነ የገዳይን ማንነት ለማወቅ ያደረገው ጥረት ለጊዜው ሳይሳካለት ይቀራል፡፡ የወንጀሉ መርማሪ ሳጅን አየነው ጎበዜ እንዳሉት ማንነቱ ያልታወቀውን ሟች ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ወደ ቆቦ ሆስፒታል ይወስዱታል፡፡

ነገር ግን ሐሙስ ሕዳር 20 ቀን 2011ዓ.ም ከሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ 02 ቀበሌ ገረገራ አካባቢ ከምሽቱ 5፡00 አቶ ታረቀ መንግሥቴ የተባሉ ሰው ወደ ፖሊስ በመሄድ ‹‹ሟች የእኔ ልጅ ነው›› በማለት በኮንትራት መኪና አስከሬኑን መውሰዳቸውን ሳጅን አየነው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

አቶ ታረቀ ልጃቸውን ከቀበሩ በኋላ ሕዳር 24 ቀን ወደ ቆቦ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽሕፈት ቤት በመሄድ ክስ መመሥረታቸውንና የልጃቸው ገዳዮች እንዲነግሯቸው መጠየቃቸውንና ፖሊስ በግድያው ዙሪያ የደረሰበትን ለአባት መንገሩን ሳጅን አየነው አስረድተዋል፡፡

አባት አስከሬኑን ሊረከቡ በመጡበት ጊዜ ስለልጃቸው የሚያውቁትን ልዩ ምልክት ተጠይቀው እንደተናገሩና የሟቹን ፎቶግራፍ ሲያዩ በጣም እንዳለቀሱ፤ እንዳጽናኗቸውም መርማሪ ፖሊሱ ተናግረዋል፡፡

የልጃቸውን አስከሬን ከፖሊስ ተቀብለው ሌሊቱን ሲጓዙ ያደሩት አቶ ታረቀ ሕዳር 21 ቀን 2011ዓ.ም ወዳጅ ዘመድ እያስተዛዘናቸው በፍላቂት ገረገራ ደብረ ሃይማኖት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብሩን ያስፈጽማሉ፡፡

‹‹ቆቦ ሰው መሞቱንና የመቄት ሰው ነው መባሉን ስሰማ አጣራሁ፤ ሊቀበር መሆኑን ስሰማም ለማጣራት ሄድኩ፡፡ ደርሼም አስከሬኑን አገላብጨ አየሁ፤ ልጄ ነው፡፡ አምጥቼ ከዘመድ ወዳጅ ጋር ሆኜ ቀበርኩ፡፡ ሥርዓተ ፍትሐቱንም አስፈጸምኩ፤ ሳልስት፣ ሰባት አስቀደስኩለት፡፡ ሰላሳውን ላስቀድስ እየተዘጋጀሁ ሳለ ግን ነገሮች ተቀዬሩ›› ብለዋል አቶ ታረቀ መንግሥቴ ለአብመድ ሲናገሩ፡፡

‹‹ድንገት ስልክ ተደወለ፤ አነሳሁት፡፡ ‹ሞቷል ብላችሁ እንዳለቀሳችሁ ሰምቻለሁ› ብሎ ልጀ ደወለ፡፡ እሱ መሆኑን ስላላመንኩት የተለያዬ ዘመድ እንዲጠራ አደረኩት፤ ተጠራልኝ፡፡ ከዚያም ወደ ቤተሰቡ መጣ›› ብለዋል አባት፡፡

በወቅቱ የሟችን አስከሬን ሲያዩ ከእጁ ጣት ላይና ከጥርሱ ልዩ ምልክትን መሠረት አድርገው ልጃቸው መሆኑን እንዳረጋገጡ የገለጹት አባት ስለተፈጠረው ነገር ተገርመዋል፡፡

‹‹ሞቷል›› ተብሎ የተለቀሰለት አበበ ቤተሰቦቹ ለማመን መቸገራቸውን ገልፆ ‹‹ከሟች ጋር እንዴት እንደተመሳሰልኩ ገርሞኛል፡፡ ለማንኛውም አሁን በወላጆቼ ፊት በመገኜቴና በሕይወት በመሆኔ ደስተኛ ነኝ›› ብሏል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የከፍተኛ አመራሩን ጃል በቴ ኡርጌሳን ግድያ በማውገዝ አፋጣኝ ነጻ፣ ገለልተኛ እና አድሏዊ ያልሆነ ምርመራ እንዲደረግ ጠየቀ። ፓርቲው በግድያው ዙሪያ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫው ፤ የፓርቲው አባል እና የፖለቲካ ኦፊሰር ጃል በቴ ኡርጌሳ ዘግናኝ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ መገደላቸውን አመልክቶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል። " በነቁ የኦሮሞ ፖለቲከኞች እና…
#Update #MNO

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአቶ በቴ ኡርጌሳን ግድያ በፅኑ #እንደሚያወግዝ ገለጸ።

በወንጀሉ ዙሪያ ተገቢው ምርመራ እንደሚደረግና ውጤቱ ለህዝብ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ የኦነግ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ በቴ ኡርጌሳ በመቂ ከተማ #ባልታወቁ_ሰዎች ተገድለው መገኘታቸውን ገልጿል።

" ይህ በማንኛውም መንገድ በየትኛው አካል ይፈፀም ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ያለው የክልሉ መንግሥት ግድያውንም " በፅኑ አወግዛለሁኝ " ሲል አሳውቋል።

" ምንም እንኳን መንግሥት ከአቶ በቴ ኡርጌሳ ጋር የፖለቲካ ልዩነት ቢኖረውም ከግድያው ጋር የሚያገናኘው አንዳችም ነገር የለም " ሲል ገልጿል።

ምርመራ ባልተደረገበት ሁኔታና ወንጀል ፈጻሚው ገና ባልታወቀበት ሁኔታ  ክስተቱን ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ የሚጠቀሙ ኃይሎች መኖራቸውን በማመልከት አጥብቆ አውግዟቸዋል።

" ከመንግስት ጋር የአቋም ልዩነት ስላላቸውና የፖለቲካ አቋማቸው ስለሚለይ ብቻ ግድያው በመንግሥት አካል እንደተፈፀመ ተደርጎ የሚነዛው ፕሮፖጋንዳ ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ፥ " የፖለቲካ ኪሳራ የደረሰባቸው የፖለቲካ ኃይሎች መንግሥትን ለግድያው ተጠያቂ በማድረግ ይህንን ሁኔታ ለመጠቀም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው " ሲል ወቅሷል።

መንግሥት በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ ውጤቱን ለህዝብ እንደሚያሳውቅም ባወጣው መግለጫ ቃል ገብቷል።

የፀጥታ ኃይሎች የግድያውን ፈፃሚ በህግ አግባብ መርምረውና አጣርተው እስካላሳወቁ ድረስ " ይህ አካል ነው ኃላፊነት የሚወስደው " ብሎ መናገር እንደማይቻል ጠቁሟል።

ማህበረሰቡ ገና ውጤቱ ሳይታወቅ እየተካሄዱ ካሉት " እከሌ ነው የገደለው " ከሚሉ ፕሮፖጋንዳዎች ራሱን መጠበቅ አለበትም ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ ተገደሉ። በወረዳው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች የወረዳውን አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽን ትለንትና በምሽት በመግባት እንደገደሏቸው ተሰምቷል። ወረዳው ባወጣው የሀዘን መግለጫው ፥ " አቶ አልብስ ለዓመታት በቀውስ ነጋዴዎች ለችግር ተጋልጦ የሴራ ፖለቲካ መሸቀጫ የተደረገውን የጀውሃና አካባቢው ማህበረሰብ ቀርቦ በማወያየት መተማመን ፈጥሮና አደራጅቶ ወደ ቀደመ…
#AmharaRegion

ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ተገደሉ።

የቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ከተማ ውስጥ ሲንቀሳቀሱ በተተኮሰባቸው ጥይት ተገደሉ።

ወ/ሮ ሚሊሹ በዛሬው እለት ነው የተገደሉት።

እንደ ወረዳው መረጃ ፥ የመንግስታዊ አገልግሎት ላይ ውለው ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ነው ጥቃት ተሰንዝሮባቸው የተገደሉት።

ግድያ የተፈጸመባቸው አመራሯ በእናትነት ላይ ነፍሰ ጡርነትን ይዘው እንደነበር ተገልጿል።

የወረዳው አስተዳደር ዛሬ ምሽት ባወጣው መግለጫ " ግድያው የተፈጸመው በጽንፈኛ አካላት #በተተኮሰ ጥይት ነው "  ብሏል።

ከቀናት በፊት የኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪው አቶ አልብስ አደፍራሽ #በታጣቂዎች_መገደላቸው ይታወሳል።

በሌላ በኩል ከሰሞኑን በወልዲያ ከተማ የመንግስት ባለስልጣናት እና ተቋምን ዒላማ ያደረጉ #የቦምብ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ነዋሪዎች ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ በዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤትና በመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች መኖሪያ ቤት ላይ እንደተፈጸሙ ነው የተሰማው።

ጥቃቱ አነጣጥሮባቸው ነበር ከተባሉት ውስጥ፦

➡️ የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ

➡️ የወልዲያ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ ይገኙበታል።

መኖሪያ ቤታቸው ላይ ነበር ጥቃት የተፈጸመው።

ከዚህም ባለፈ የዞኑ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢም የጥቃት ኢላማ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

" #ባልታወቁ_አካላት " ተፈጽሟል በተባሉት ጥቃቶች በባለስልጣናቱ ላይ ሳይሆን በሌሎች ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱ እንዲሁም ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

በቅርቡ የጉባ ላፍቶ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት እና በፖሊስ ጣቢያ ላይ ተመሳሳይ ጥቃቶች ተፈጽመው እንደነበር ተነግሯል።

ባለፈው #ሚያዚያ ወር የላስታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው መልሴ እና የወረዳው የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሚሊዮን አፈወርቅ ከስብሰባ ሲመለሱ በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸው አይዘነጋም።

#TikvahEthiopia
#BBCAmharic

@tikvahethiopia