" በ26 ቀበሌዎች ድርቅ ቢከሰትም እስከ ዛሬ በተጨባጭ የተሰጠ ድጋፍ የለም " - የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ጽ/ቤት
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሦስት ወረዳዎች በሚገኙ 26 ቀበሌዎች ድርቅ ቢከሰትም ከመንግሥትም ሆነ ከተለያዩ የተራድዖ ድርጅቶች እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) ድጋፍ እንዳልልተገኘ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ በሰሃላ ሰየምት፣ ዝቋላ እንዲሁም በጻግብጅ ወረዳዎች ድርቅ ቢከሰትም " እስከ ዛሬ በተጨባጭ የተሰጠ ድጋፍ የለም " ብለዋል።
ድርቁ የተከሰተው በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አሰተዳደር ፦
- በሰሃላ ወረዳ በሙሉ (13 ቀበሌዎች)፣
- በዝቋላ ወረዳ (7 ቀበሌዎች)፣
- በአበርገሌ ወረዳ (6 ቀበሌዎች) አጠቃላይ በ26 ቀበሌዎች መሆኑን አቶ ምህረት አክለዋል።
በሦስቱ ወረዳዎች ተከሰተ ለተባለው ድርቅ ምክንያቱን ሲያብራሩም ፤ " የ2015 ክረምት ዝናብ ስርጭቱ ፣ ምንም አለመዝነቡ፣ ዘግይቶ መጀመር ፣ ጀምሮ ማቋረጥ " ሲሉ ገልጸውታል።
ጽሕፈት ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ " ወደ 1,236 የተለያዩ እንሰሳት " ሞተዋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ " ሞቱና ችግሩ እየሰፋ ነው። እስከ ዛሬ በተጨባጭ የተሰጠ ድጋፍ የለም። የሚሰሩ ቅድመ ዝግጅቶች ግን አሉ ወደ ተግባር ሲቀየሩ እንገልፃለን " ሲሉ አስረድተዋል።
በ2015 ዓ.ም የክረምት ወቅት ምን ባለመዝነቡ ምን ያህል ሄክታር መሬት ሰብል እንተበላሸ ከቴክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ምህረት፣ "የዝናብ ሰርጭት መቋረጡ ምክኒያት 7,360.5 ሄክታር የተለያዩ ሰብሎች ደርቀዋል " ብለዋል።
በሺሕዎች የሚቆጠሩ የዕለት ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ድጋፍ እንዳላጉኙ፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ እንስሳት ድርቁ እንደተጋረጠባቸው ለማወቅ ተችሏል።
በ2014 የክረምት ወቅት በዞኑ በሚገኙ በሰቆጣ፤ ዝቋላ፣ ጻግብጅ፣ አበርገሌ ወረዳዎች የእርሻ መሬቶች በወቅቱ በነበረው የሰሜኑ ጦርነት በሰብል እንዳልተሸፈኑና ቡቃያዎችም ከጥቅም ውጪ እንደሆኑ የዞኑ ግብርና መምሪያ በምስከረም ወር 2015 ዓም መግለጹ ይታወሳል።
መረጃውን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የቲክቫህ አባል ነው።
@tikvahethiopia

#የዋጋ_ንረት📈
መስከረም 2015 መጀመርያ ላይ ከ6 ሺሕ ብር በታች ይሸጥ የነበረ አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ ለመጀመርያ ጊዜ ከ10 ሺሕ ብር በላይ ዋጋ ያወጣው ሊጠናቀቅ ሰዓታት በቀሩትና አሮጌ ብለን ልንሸኘው በተዘጋጀው 2015 ዓ.ም. ነው፡፡ የጤፍ ዋጋ ነሐሴ 2015 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ እስከ 15 ሺሕ ብር ሲደርስ ይኸው የዋጋ ጭማሪ 1 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከዕጥፍ በላይ እንደደረሰ ያመለክታል።
#የስንዴ_ገበያም በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ የተመዘገበበት ዓመት ይኼው 2015 ዓ.ም. ነው፡፡
በአጠቃላይ ከጤፍና ስንዴ በተጨማሪ በሌሊችም ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ባለሆኑ ሸቀጦች ላይ በዚህ ልንሸኘው ጥቂት ሰዓታት በቀረን 2015 ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ተመዝግቧል።
የኢኮኖሚው ባለሙያ አቶ አወት ተክኤ ምን ይላሉ ?
" በሀገሪቱ ከፀጥታና አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የዋጋ ንረትን በማባባስ ዓይነተኛ ሚና ነበራቸው። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እንዳይስፋፉ ጭምር አድርገዋል።
በ2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ለዋጋ ንረቱ መባባስ በተደጋጋሚ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ባሻገር፣ መንግሥት የወሰዳቸው የፖሊሲ ዕርምጃዎች ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ ነበራቸው።
ለአብነት የኢኮኖሚ የነዳጅ ጭማሪ እና ሌሎች የመንግሥት የፖሊሲ ውሳኔዎች ለዋጋ ንረቱ የራሳቸው አስተዋጽኦ አድርገዋል።
ይህ የዋጋ ንረት በቀጣይ ዓመትም እንዳይተላለፍ ለችግሩ መንስዔ የነበሩት፣ ለምሳሌ የፀጥታና ያለ መረጋጋቶች መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡
በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ውሳኔዎችን በአግባቡ መተግበር ለዋጋ ንረት መርገብ መፍትሔ ሊሆኑ ይገባል፡፡ "
ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ethiopianreporter-09-11
#ሪፖርተር_ጋዜጣ

Attention to all aspiring candidates in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹:
The Jasiri team will be hosting an information session on their telegram channel on Thursday,14th September at 6pm EAT to offer more insights into the Jasiri Talent Investor program and address any questions you might have.
Please follow Jasiri on their telegram channel(Jasiri4Africa) and rsvp for the info session on this link: https://bit.ly/3PuCNpx
Feel free to spread the word – tell a friend 🇪🇹 to tell a friend🇪🇹!
#Jasiri4Africa

#Update
የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23 /2016 ዓ/ም ይሰጣል ተብሏል።
ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ይሰጣል።
ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ፦
- የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21-23/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በበየነ-መረብ የሚሰጥ መሆኑን፤
- ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11 - 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በበየነ መረብ ማመልከት እንደሚገባቸው ፤
- ተፈታኞች ለፈተና ሲያመለክቱ ፈተናውን ለመውሰድ የሚከፈለውን ክፍያ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በቴሌ ብር እንዲከፍሉ ከወዲሁ የቴሌ ብር አካውንት መክፈት እንደሚገባቸው መረጃው በትክክል እንዲያውቁ እንዲደረግ ፤
- ተቋማት ለመማር ያመለከቱና የሚያመለክቱ አመልካቾችን በበየነ መረብ እንዲያመለክቱ እንዲሁም የፈተና ፕሮግራምና ተያያዥ መረጃዎችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽና ፖርታል፤ www.aau.edu.et እና https://portal.aau.et ብሎም ኦፊሺያል ቴሌግራም ቻናል፤ Testing_Center IER AAU እንዲያገኙ መረጃውን በትክክል እንዲደረሳቸው ፤
- በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ለፈተና ለመቀመጥና ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቷቸው ያለበት Test Admission Ticket (TAT) ይዘው መገኘት እንዳለባቸው፤ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestTaker)
- የመግቢያ ፈተናው በመላ ሀገሪቱ ባሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ በበየነ መረብ የሚሰጥ በመሆኑ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ኮምፒዩተር ያላቸው የመፈተኛ ማዕከላት Safe Exam Browser (SEB) ሶፍትዌር ተጭኖባቸው Corrective and Preventive Maintenance ተደርጎላቸው እንዲሁም Power Backup እንዲኖራቸው ተደርጎ አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ፤
- ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ኔትወርክ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ ይህንኑ የየዩኒቨርሲቲው አይሲቲ ዳይሬክተር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እንዲያስፈጽም መመሪያ እንዲሰጥ፤
- የመግቢያ ፈተናውን የትምህርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚያስተዳድሩት እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰጥ መሆኑ እንዲታወቅ፤
- የፈተናውን ውጤት ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱና በመጨረሻ መልሳቸውን ሲያስገቡ ወዲያውኑ ማየት የሚችሉ መሆኑን፤
- ተፈታኞች የፈተናውን ውጤት የሚያሳይ ሰርተፊኬት በወረቀት (Hard Copy) አትመው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ለመማር በሚያመለክቱበት ተቋም ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን፤
- የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን መሆኑን አሳውቋል።
(በዶ/ር ኤባ ሜጄና ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲች እና የግል ተቋማት የተላከውን ደብዳቤ ከላይ ይመልክቱ)

#እንቁጣጣሽ
የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፤ ከፍተኛ ሽልማቶችን እንደያዘ የገለፀው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ፊት መውጣቱን ገልጿል።
በዚህም ፦
- የ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1820259
- የ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1656546
- የ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 2118779
- የ4ኛ ዕጣ 3 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 0865504
- የ5ኛ ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1020830
- የ6ኛ ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1317686
- የ7ኛ ዕጣ 500,000 ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1903473 ሆኖ የወጣ ሲሆን የማስተዛዘኛ ዕጣ ቁጥርም 6 በመሆን መውጣቱን አሳውቋል።
(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮችን ከላይ ይመልከቱ)

#አማራ
ዋዜማው እና የአዲስ አመቱ አቀባበል በአማራ ክልል እንዴት ነው ?
በአማራ ክልል በቅርቡ ባጋጠመው ደም አፋሳሽ ግጭት ምክንያት የዘንድሮው አዲስ ዓመት አቀባበል ቀዝቃዛ እንደሆነ ነዋሪዎች እየገለፁ ናቸው።
ባለፉት ዓመታት የነበሩ የአዲስ ዓመት አቀባበሎችም ክልሉ ባስተናገደው አስከፊ ጦርነት ምክንያት ዜጎች በተሟላ ሰላም በዓሉን መቀበል እንዳልቻሉ የሚታወቅ ነው።
በዘንድሮው ዓመትም ባጋጠመው ጦርነት ሰላም በመራቁ የአዲስ አመት አቀባበሉ ጥላ ያጠላበት ነው።
የኢተርኔት አገልግሎት በክልሉ እንደተቋረጠ ነው።
ዛሬ ቃላቸውን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡ የክልሉ ነዋሪዎች የበዓሉ ድባብ ቀዝቃዛ ነው ብለዋል።
የደብረታቦር ከተማ ነዋሪ ፦
" በዓሉን በተመለከተ የተለየ ነገር በከተማው አይታይም።
የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት በመቋረጡም የመልካም ምኞት መልዕክቶችን መለዋወጥ አልቻልንም። "
የደንበጫ ከተማ ነዋሪ ፦
" አካባቢው እንስሳት የሚደልቡበት አካባቢ ነው። በነበረው አለመረጋጋት እንስሳት መድለብ አልቻሉም። ከሌላ ቦታ ሄዶ የእርድ እንስሳትንም መግዛት አልተቻለም።
አጋጣሚው በአዲሱ ዓመት አቀባበል ላይ አሉታዊ ጫና ፈጥሯል። "
ሌላ የዚሁ ከተማ ነዋሪ ፦
" የዓመት በዓሉን መድረስ የሚያመላክቱ ሙዚቃዎች አይሰሙም፣ ለእርድ እንስሳት የተዘጋጄ ሰው አላየሁም። "
የቢቸና ነዋሪ ፦
" ከዚህ ቀደም በነበሩ የበዓል ዝግጅቶች የእርድ እንስሳትን ቀደም ብለው ይገዙ ነበር።
አርሶ አደሩም ሆነ የእንስሳት ነጋዴው የደህንነት ስጋት ስላደረበት እንስሳቱን ወደ ገበያ ማውጣት አልቻለም። "
የደብረ ማርቆስ ነዋሪ ፦
" በጦርነት ቆፈን ሆኖ በዓል ማክበር አይቻልም። "
የፈረስ ቤት ከተማ ነዋሪ ፦
" ሁሉም ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ወደ ሥራ ባለመግባታቸው በአዲሱ ዓመት አከባበር ላይ ከፍተኛ ጫና ተፈጥሯል። "
ይህች ከተማ በቅርብ ብርቱ ውጊያ ያስተናገደች ናት።
የደሴ ከተማ ነዋሪ ፦
" ወቅታዊ ሁኔታው በበዓሉ ድምቀት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሯል። "
የባህርዳር ነዋሪዎች ፦
" የባሕር ዳር ከተማ የዓመት በዓል ድባቡ ብዙ ባይታይም የእንስሳት አቅርቦት አለ።
ካለፈው ዓመት ሲነፃፀር የዋጋ መጨመር ይታያል ብለዋል፡፡ "
የእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ነዋሪ ፦
" ሰሞኑን በዋለው ገበያ የእንስሳቱም ሆነ ሌሎች ለምግብ ፍጆታ የሚውሉ ሸቀጦች ዋጋ እጅግ ጨምሯል።
ምክንያቱም ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶች በሙሉ ባለመከፈታቸው ሸቀጦች እንደልብ እየገቡ ባለመሆናቸው ነው፡፡ "

" #የአማራ እና #የትግራይ ህዝቦች ዝም ብሎ ጆግራፊ አይደለም ያስተሳሰራቸው ፤ የጋራ ታሪክ አላቸው ፈለግንም አልፈለግንም አብሮ መኖራቸው አይቀርም " - አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ አዲሱን ዓመት አስመልክተው ከብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ (etv) ጋር ቃለምልልስ አድርገው ነበር።
በዚህ ቃለ ምልልሳቸው ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ በአዲሱ አመት 2016 ዓ/ም አስተዳደራቸው ፦
- የሰላም ጅምሩ እንዲጠናከር እንደሚሰራ ፤
- ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ እንደሚሰራ፤
- ከምንም በላይ በዜጎች አእምሮ ላይ የተፈጠረውን ስብራት ለመጠገን እንደሚሰራ፣
- የተቋረጡ የማህበራዊ አገልግሎቶች ለአብነት ትምህርት ፣ጤና አገልግሎቶች ከጦርነት በፊት ወደነበሩበት ለመመለስ ተስፋ ሠጪ እንቅስቃሴ ለማድረግ እንደሚሰራ፤
- ምርጫ ተድርጎ የሚመረጠው አስተዳደር በተሟላ መልኩ ትግራይን የሚያስተዳድረበት በፌዴሬሽኑ ውስጥ ትግራይ ያላትን ተሳትፎ የሚያረጋግጥ መንግሥት እንዲሆን የፖለቲካ ስራዎችን ለመስራት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
ምርጫ መቼ ነው ? ለሚለው ጥያቄ አቶ ጌታቸው " ዋናው መሬት ላይ ያለው እውነታ ነው። ምርጫ ብቻችንን አይደለም የምናደርገው ፤ የፌዴራል መንግሥቱ ፣ምርጫ ቦርድ በዚህ ጉዳይ ውስጥ መካከት አለባቸው ፤ የትግራይ የፖለቲካ ኃይሎች ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ምርጫ መሆን አለበት " ብለዋል።
አቶ ጌታቸው ምርጫ ስለሚደረግበት ቀን ቁርጥ ያለ ጊዜ አልተናግሩም።
የአማራና የትግራይ ህዝቦችን ግንኙነት በተመለከተ በአዲሱ አመት ስለታቀዱ እቅዶች ተጠየቀው ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ " ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ የሚጠየቅበትን ሁኔታ መመቻቸት አለበት ፤ ለዚህ ችግር የለብንም ብለን ብዙ ሰው በእኛ አካባቢ የችኮላ ነው የሚለውን እርምጃ ባህር ዳር ሄደን ያለንን የሰላም ፍላጎት ገልጸናል። ከዛ አንስተን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ ተፈናቃዮችን መመለስ ጀምረን ልዩነቶቻችንን በሰላማዊ መንገድ መፍታት የሚያስችል ነገር ውስጥ እንገባለን ብለን መንቀሳቀስ ጀምረን ነበር " ብለዋል።
ይህ እንቅስቃሴ በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም ያለቱ ፕሬዜዳንቱ " በሚፈለገው ፍጥነት አልሄደም ማለት አይሄድም ማለት አይደለም። እንዲሄድ መስራት አለብን ምክንያቱም የአማራ እና የትግራይ ህዝቦች ዝም ብሎ ጆግራፊ አይደለም ያስተሳሰራቸው ፤ የጋራ ታሪክ አላቸው ፈለግንም አልፈለግንም አብሮ መኖራቸው አይቀርም ፤ ቢረፍድ ይሻላል ፈፅሞ ከሚቀር እንደዚህ አይነት ነገር ስለዚህ እሱን (የተጀመረውን ግንኙነት) በአዲሱ አመት አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲሉ ተናግረዋል።
አዲሱን ዓመት በማስመልከተም አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ እና በውጭ ላለው ዳያስፖራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ጌታቸው ፤ " ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊያውቀው የሚገባው ፤ ግጭት አንድ አካባቢ ስላለ cheer ማድረግ ይቁም። አንድ አካባቢ ያለ ግጭት የሁላችንም ግጭት መሆኑን እንረዳ፤ አንድ አካባቢ ያለ ጥፋት የሁሉም ጥፋት ነው ብለን እንቀበል ፤ መንግሥት ወደልማት ጎኑ ለመሄድ የሚያደርገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ነገር ካለ ልማት ነው የሚያዋጣን የሚለው ድምፅ ጎልቶ እንዲወጣ ለማድረግ የሚያስችል እገዛ ይደረግ " ብለዋል።
" ዳያስፖራ ማጋጋል ፣ ማጋጋል ፣ ማጋጋል መሆን የለበትም ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ግጭትን ከማጋጋል ስለሰላም መስበክ የሁሉም ድምፅ መሆን መቻል አለበት፤ እነ እገሌን ካላንበረከክን እነ እገሌን ካላሸነፍን ሞተን እንገኛለን የሚል አስተሳሰብ ሁላችንንም ወደ ጥፋት የሚወስድ እንጂ አንዱን የሚጠቅም አይደለም " ሲሉ አስገንዝበዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#USA የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 3 ድረስ በኬንያ እና በኢትዮጵያ ቆይታ እንደሚያደርጉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል። በናይኖቢ እንዲሁም በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከሀገራቱ ባለስልጣናት፣ ከአፍሪካ ህብረት፣ ከልማት ድርጅት ባለስልጣን እና ሌሎች ዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ይነጋገራሉ ተብሏል። ሐመር በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ፣ በአማራና…
#Update
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ አዲስ አበባ ይገኛሉ።
የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ ይገኛሉ።
አምባሳደር ሐመር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አርጋ የመከሩ ሲሆን ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋርም ተገናኘተው መምክራቸው ታውቋል።
የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ከአምባሳደር ምስጋኑ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያና የአሜሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም ቀጣናዊ፣ አኅጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።
ከትግራይ ጊዜዊ አስተዳዳሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር በነበራቸው ቆይታ የጋራ ጉዳዮችን በማንሳት የመከሩ ሲሆን የፕሪቶሪያው ስምምነትን ሙሉ ተግባራዊነትን በተመለከተ ተነጋግረዋል።
አቶ ጌታቸው ውይይቱን በተመለከተ ባሰራጩት መልዕክት ፤ " የጋራ ጉዳዮችን አንስተን ተወያይተናል ፤ በተለይም የፕሪቶሪያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን እንዲሁም ደግሞ በኢትዮጵያ እና በቀጠናው መረጋጋት ላይ በጋራ ለመስራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጠናል " ብለዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት ሐመር በአዲስ አበባ በሚያደርጉት ቆይታ፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች በድርድር እንዲቋጩ እና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳይደርስ እና ከለላ እንዲያገኙ ግፊት እንደሚያደርጉ ማሳወቁ ይታወሳል።

#ሊቢያ
በምስራቃዊ ሊቢያ የምትገኘውን " ዴርና " ከተማን በመታው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እና ጎርፍ ምክንያት 2000 የሚደርሱ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛሉ።
7000 ሰዎችም የገቡበት አይታወቅም ተብሏል።
በቤንጋዚ የሚገኘው የቀይ ጨረቃ ኃላፊ ካይስ ፋከሪ እንደተናገሩት " ዳንኤል " በተባለው አውሎ ንፋስ በዴርና ከተማ ባደረሰው ጥፋት ቢያንስ 150 ሰዎችን ሞተዋል።
በከተማዋ ሁለት ግድቦች መደርመሳቸውም ተነግሯል።
ከቀናት በፊት በሌላኛዋ የአፍሪካ ሀገር #ሞሮኮ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ2000 በላይ ሰዎች ሞተዋል።