አዲሱ ዓመት 2016 ፦
- ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤
- ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ #ፍትሕ የሚገኝበት፤
- ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤
- ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤
- ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤
- ወጥተን የማንቀርበት፤
- በአጠቃላይ ሀገራችን ከጫፍ እስከጫፍ ሰላም እና ተስፋ የሚነግስበት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።
የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ ፣ የሚወዱትን ከአጠገባቸው የተነጠቁ ወገኖችን በማፅናናት ፣ የታመሙትን በመጠየቅ ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።
መልካም አዲስ ዓመት !
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
Tikvah Family
#ኢትዮጵያ2016
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ ዓመት 2016 ፦ - ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤ - ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ #ፍትሕ የሚገኝበት፤ - ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤ - ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤ - ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤…
#ኢትዮጵያ2016
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲሱን 2016 ዓ/ም አንድ ብላ ጀምራለች።
ዓመቱ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የፍትህ ፣ ከችግሮቻችን የምንላቀቅበት እንዲሆን የመላ የኢትዮጵያውያን ምኞት ነው።
አሁንም በኢትዮጵያ የሚወዱትን የተነጠቁ፣ በግፍ ከቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ብርድ እና ፀሀይ የሚፈራረቅባቸው ፣ የነበራቸውን ንብረት እና ሃብት በጦርነት እና በግጭት አጥተው የሰው እጅ ጠባቂ የሆኑ ፣ በየወቅቱ በሚፈጠሩ ችግሮች ሰበብ በጅምላ ታስረው የሚገኙ፣ በኑሮ ውድነት ክፉኛ እየተሰቃዩ ያሉ ወገኖች እጅግ በርካታ ናቸው።
አዲሱ ዓመት ፍትሕ እና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ፤ የተበደለ የሚካስበት ፤ የእርስ በእርስ መግባባት እውን የሚሆንበት ፤ የህዝብ ድምፅ የሚሰማበት ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ ላለው ኑሮ መረጋጋት የሚፈጠርበት እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል።
ይህን አዲስ ዓመት ያለፉ ችግሮቻችን ሁሉ የሚታረሙበት ፣ ለጥፋት የዳረጉን ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት፣ ለችግሮቻችን ሁሉ ተነጋግረን መፍትሄ የምናበጅበት፣ የተበደሉትን የምናፅናናበት፣ እንደ አንዲት የኢትዮጵያ ልጆች እርስ በእርስ ከጥላቻ ርቀን ለእድገታችን የምንሰራበት እንዲሆን እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀም ይገባል።
ሁሌም አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር የሚነገር ምኞት እና የተስፋ ቃላት መሬት ላይ ካልዋለ ትርጉም አልባ ነውና ሁሉም ለሚናገረውና ለሚገባው ቃል መታመንና መፅናት አለበት።

#Update የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጳጉሜን 2 /ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠርተውት መንግስት ሳይፈቅድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማነሳሳትና በመሳተፍ ምክንያት በቁጥጥር ሰር ያዋላቸውን እፈታ መሆኑን ገልጿል። የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፤ " ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ጨምሮ የፓለቲካ ፓርቲ ሊቃነ መናብርትና ጋዜጠኛ ገና አልተፈቱም " ብለዋል። ከመቐለ ከተማ ፓሊስ የተገኘ መረጃ እንደሚያስረዳው ፦…
#Mekelle
" በአምባገነን ስርአት ምክንያት መብታችን እንዲቀማ እንፈቅድም " - አቶ ዓምዶም ገ/ስላሴ
በትግራይ መቐለ ከተማ " ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ " በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜን 2/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሊካሄድ ከተጠራው ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያዘዘ በቁጥጥር ስር የነበሩ የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ ሊቃነመናብትና ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ መለቀቃቸው ታውቋል።
የዓረና ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገ/ስላሴ ፣ የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ/ር ደጀን መዝገበ ፣ የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ሊቀመንበርና ከፍተኛ አመራር አቶ ሃያሉ ጎዲፋይና አቶ ዓብለሎም ገ/ሚካኤል ፣ የብሄራዊ ባይቶና ዓባይ ትግራይ አስተባባሪዎች አቶ ኪዳነ አመነና ክብሮም በርሀ ጳጉሜን 6/2015 ዓ.ም ከተለቀቁት መካከል ናቸው።
እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፍ በተጠራበት ሮማናት አደባባይ ተገኝቶ በፓሊስ ተድብድቦ በቁጥጥር ስር የቆየው ጋዜጠኛ ተሻገር ፅጋብም ተለቋል።
የዓረና ሊቀመንበር አቶ ዓምዶም ገ/ስላሴ ለአሜሪካ ድምፅ እንዳሉት እሳቸው ጨምሮ 150 የሰልፉ ተሳታፊዎች መታሰራቸው ፤ ዓርብ ጳጉሜ 3 /2015 ዓ.ም 6 የአራት ተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ፍርድ ቤት ቀርበው በ10 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ቢወሰንም ፤ ፓሊስ ፍቃደኛ ባለመሆኑ እስከ ጳጉሜን 6 /2015 ዓ.ም መታሰራቸው ገልፀዋል።
" ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ ፤ ግርፋትና እስራቱ ፣ አልፎም ከፍርድ ቤትና ዳኛ በላይ መሆን የመሰለ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው የተፈፀመው " ያሉት አቶ ዓንዶም ፤ " በአምባገነን ስርአት ምክንያት መብታችን እንዲቀማ እንፈቅድም ፤ መብታችን መስዋእትነት ጭምር በመከፈል እናረጋግጣለን ፤ ቀጣይ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ ህዝባዊ ስብሰባዎች ሌሎች ፓለቲካዊ እንቀስቃሴዎች በማካሄድ ህዝቡ የዴሞክራሲያዊ መብት ባለቤት እስኪሆን ድረስ እንታገላለን " ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲካሄድ አልፈቀድኩም ካለው የጳጉሜን 2 ቱ ሰልፍ ጋር በተሳሰረ ከተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር የታሰሩት 49 እንደሆኑ የጠቀሱት የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ፤ ባልተፈቀደው ሰልፍ የተፈጠረው ግርግር ፓሊስ በ20 ደቂቃ በማይሞላ ግዜ እንደተቆጣጠረው መግለፃቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።
More - @tikvahethiopiaTigrigna

Photo
#Update
በሊቢያ ባጋጠመው የጎርፍ አደጋ የሟቾች ቁጥር ወደ 5000 ሺህ ሳይጠጋ እንደማይቀር እየተነገረ ነው።
10 ሺህ ሰዎችም ያሉበት አይታወቅም ተብሏል።
የሊቢያ ቀይ ጨረቃ እስካሁን ባለው 2,084 ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።
በሊቢያ የሚገኘው ቀይ መስቀል በበኩሉ የገቡበት የማይታወቁ ሰዎች 10 ሺህ ደርሰዋል ሲል አሳውቋል።
መቀመጫውን በ ' ምስራቃዊ ሊቢያ ' ያደረገው አስተዳደር በአደጋው 5000 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ገልጿል።
100 ሺህ ነዋሪ ባላት ደርና ከተማ ውስጥ የነበሩ ሁለት ግድቦች እና አራት ድልድዮች ከተደረመሱ በኋላ በከተማዋ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በውሃ ተውጣለች ብሏል።
" የሰዎች አስክሬን በየቦታው ወድቆ ይገኛል " ሲል ገልጿል።
የከተማዋ ሩብ ክፍል ሙሉ በሙሉ ጠፍቷልም ብሏል።
በከተማይቱ የሞቱ ሰዎች በጅምላ እየተቀበሩ እንደሆነ ተሰምቷል።

የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ
የአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከግራር የጠቢባን መናኸርያ እንዲሁም ከUSAID ጋር በመተባበር የዘወትሯ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል። ይህ አውደርዕይ በሚካኤል ጸጋዬ ዋና አዘጋጅነት የቀረበ ነው።
የመጀመርያ ዙር ቆይታውን በባህርዳር፣ ሁለተኛ ማረፊያውን ድሬዳዋን ያደረገው አውደርዕዩ በብዙዎች ተወዳጅነትን አትርፏል። በቀጣይ ጉዞውን ወደ ሀዋሳ የሚያደርግ ይሆናል።
ከመስከረም 3 - 7/2016 በሀዋሳ ሴንትራል ሆቴል በ15 የፎቶግራፍ ባለሙያዎች የተዘጋጁት የፎቶግራፍ ስብስቦች የሚቀርቡ ሲሆን ከአውደርዕዩ ባለፈ ነጻ የፎቶግራፍ ስልጠናን ጨምሮ የጥይቄና መልስ ግዜዎች ከፎቶግራፍ ባለሙያዎቹ ጋር ተዘጋጅተዋል።
በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! የአንድነታችንን ውበት በጋራ እናድንቅ!

የቅመም ናና ስማርት ስልክን በሚገርም ዋጋ! ወደ ሳፋሪኮም ሱቆች ጎራ ብለን የጉግል መተግበሪያዎች ያሉትን የቅመም ናና ስልክ እንግዛ!
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር የዲጂታል መታወቂያ ስርዓትን በትምህርት ተቋማት መደበኛ የተማሪዎች መለያ አድርጎ ለመተግበር መወሰኑን ገልጿል።
የተማሪዎች ዲጂታል መታወቂያ ጥቅም ላይ መዋሉ የተማሪዎችን ማንነት በወጥነት መለየት የሚያስችል ስርዓት እንዲኖር ያደርጋል ብሏል።
ይህም ዲጂታል መታወቂያ በሁሉም የትምህርት ተቋማት አበይት የማንነት ማረጋገጫ ስርዓት ሆኖ እንዲያገለግል የሚያስችል እንዲሁም የአሰራር ድግግሞሽን በመቀነስ እና በተማሪዎች የትምህርት ሰነዶች መካከል አንድነት እና ቅንጅትን የሚያጠናክር ነው ሲል ገልጿል።
ከዚህም ባለፈ የግል መረጃን የማስቀመጥ እና የመጠቀም ደህንነትን በእጅጉ እንዲጨምር የውሂብ ጥበቃን እንዲረጋገጥ ፣ ማንኛውም አይነት ጥሰቶችን ለመቀነስን ያግዛል ብሏል።
የብሔራዊ መታወቂያ መርሃ ግብር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋራ ባደረገው ስምምነት እስከ አሁን 640 ሺህ ተማሪዎች ብሔራዊ መለያ ቁጥር ማግኘታቸው ይፋ ተደርጓል።

ፈረንሳይ iPhone 12ን አገደች።
ፈረንሳይ iPhone / አይፎን 12 ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ አዘዘች።
ትናንት መስከረም 1/2016 ዓ.ም. የሬዲዮ ሞገዶችን የሚቆጣጠረው አካል አይፎን 12 ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው ብሏል።
ተቋሙ ስልክ አምራቹ አፕል ችግሩን በሚያደርጋቸው ማሻሻያዎች በአስቸኳይ የማይቀርፍ ከሆነ በመላው አገሪቷ ተሽጠው የሚገኙ አይፎን 12 ስልኮችን ለመሰብሰብ እገደዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።
የፈረንሳዩ የሬዲዮ ሞገዶች ተቆጣጣሪ ድረጅት ይህን ይበል እንጂ የዓለም ጤና ድርጅት ስልኮች የሚያመነጩት የራዲዬሽን መጠን በሰው ልጆች ጤና ላይ እክል እንደሚፈጥር ምንም ማረጋገጫ የለም ብሏል።
አይፎን 12 ከ3 ዓመታት በፊት እአአ መስከረም 2020 ላይ ለገበያ የቀረበ ሲሆን በመላው ዓለም በከፍተኛ መጠን ከተሸጡ የአፕል ምርቶች መካከል አንዱ ነው።
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በተቋሙ ውሳኔ እንደማይስማማ ገልጿል።
አፕል ለቢቢሲ በሰጠው ምላሽ በራሱ ላብራቶሪ እና ገለልተኛ በሆነ ሦስተኛ ወገን ቤተ-ሙከራ የተገኙ ወጤቶች አይፎን 12 የሚያመነጨው ጨረራ በጤና ላይ ጉዳት እንደማያስከትል እና ከደረጃ በላይ እንዳልሆነ የሚያሳዩ ማረጋገጫዎችን ለመንግሥታት ተቆጣጣሪዎች አቅርቤያለሁ ብሏል።
ግዙፉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አምራቹ ጨምሮም አይፎን 12 የጨረራ መጠኑ በሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያስከትል በመላው ዓለም ባሉ ተቆጣጣሪዎች እውቅና ያለው ምርት ነው ሲል አሳውቋል።
የፈረንሳዩ የሬዲዮ ሞገዶች ተቆጣጣሪ ድርጅት አይፎን 12 በኪስ ውስጥ ሲቀመጥ በአውሮፓ ኅብረት በአንድ ኪሎ ግራም ውስጥ መኖር ከሚኖርበት ስፔስፊክ አብሶርፕሽን ሬት 5.74 ዋትስ በላይ ነው ሲል አሳውቋል።
በሌላ አይፎንን በሚመለከት መረጃ " አይፎን 15 " ለገበያ ቀርቧል።
አፕል አዲሱን ምርቱን ይፋ ያደረገው በዩኤስቢ ሲ ታይፕ ቻርጅ ማድረጊያ ነው። የአውሮፓ ሕብረት የአፕል ምርቶች ቻርጅ የሚደረጉበት ቀዳዳ መቀየር አለበት ማለቱን ተከትሎ አዲስ ገመድ ይዞ ብቅ ያለው።
አይፎን 15 እና 15 ፕላስ ምርቶች ስክሪናቸው የጠራ፣ ካሜራቸው የተሻሻለ ሲሆኑ አይፎን 15 ፕሮ እና ፕሮ ማክስ ደግሞ ከታይታኒየም የተሠራ ገላ ያላቸው በመሆናቸው ጥንካሬያቸው ከፍ ያለ ነው።
ፕሮ እና ፕሮ ማክስ ‘አክሽን በተን’ የተባለ አዲስ ቴክኖሎጂ ይዘዋል። ለወትሮው ስልክ ‘ሳይለንት’ ለማድረግ የሚረዳው ቴክኖሎጂ አሁን የተለያዩ ተግባራትን እንዲፈፅም ሆኖ ተሠርቷል።
ነገር ግን የቴክኖሎጂ አዋቂዎች አዲሶቹ የአፕል ምርቶች በጣም ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ አዲስ ነገር አልያዙም ብለዋል። በዚህም ምክንያት ተጠቃሚዎች ረብጣ ዶላር አውጥተው ይገዛሉ ወይ ? ብለው እንዲጠይቁ ሆነዋል።
በዩናይትድ ኪንግደም አይፎን 15 ፕሮ ዋጋው 999 ፓውንድ ነው ፤ በአሜሪካ አይፎን 15 ፕሮ በ128 GB በ$999 ለገበያ የቀረበ ሲሆን አይፎን ፕሮማክስ በ256 GB በ$1199 ነው ለገበያ የቀረበው።
መረጀው ከቢቢሲ እና አፕል ሃብ የተገኘ ነው።