TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA #Ethiopia አሜሪካ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ያለቻቸው የፋኖ ኃይሎች " ውይይትን አልቀበልም " ማለታቸውን በመግለጽ ይህ " ለራሳቸውም አይጠቅማቸውም " አለች። ሀገሪቱ ይህን ያለችው በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር በሆኑት ኢርቪን ማሲንጋ አማካኝነት ነው። አምባሳደሩ ፤ " በአማራ ክልል ውስጥ ውጊያ እያደረጉ የሚገኙት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ኃይሎች ' ውይይትን አንቀበልም…
#የአሜሪካ_አቋም!

" ግጭት የኢትዮጵያውያንን #ስቃይ_ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም " - አሜሪካ

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ አሜሪካ ስለ ኢትዮጵያ ያላትን ፖሊሲ በተመለከተ ምን አሉ ?

- በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን ሊያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን ማክበር አለባቸው።

- የታጠቁ ቡድኖች ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በአመፅ ለማሳካት እየገፉ ናቸው ፤ መንግስትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ አለው። ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶች እንዲቀጥሉ አድርጓል።

- ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መሆኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ማየቱ እጅግ ያሳዝናል።

- የተፈጸሙ ጥፋቶች እውነተኛና ግልጽ የሽግግር ፍትሕ ሒደት በተከተለ የተጠያቂነት አሰራር በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል።

- ሽፍታዎች፣ የታጠቁ ቡድኖች፣ አንዳንዴም የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች፤ በህይወት የመኖር፣ የሰብዓዊ ክብርን፣ መከበርን በመሰሉ መብቶች ላይ ያለምንም ተጠያቂነት ጥሰቶች ይፈጽማሉ።

- በጦርነት እና ግጭት ወቅት እንኳ የሰብዓዊ መብቶች ሊረሱ አይገባም።

- ሁሉም ሀገር ራሱን የመከላከል ህጋዊ መብት አለው፤ ሆኖም ሀገራት ራሳቸውን የሚከላከሉበት መንገድ ያለምንም ጥርጥር የወደፊት ግጭቶችን አካሄድ የሚወስን ነው።

- ሀገር የመከላከያ መንገዶቹ በዛሬው እና በወደፊቱ የማህብረሰብ ትስስር ላይ ይበልጡኑ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው።

- የታጠቁ ወገኖች የፖለቲካ ግባቸውን ከውይይት ይልቅ በግጭት ለማሳካት ሲሞክሩ፤ ለሚፈጸሙ በደሎች ሁኔታዎች የተመቻቹ ይሆናሉ።

- በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት እራሳቸውን ' ፋኖ ' ብለው የሚጠሩ ታጣቂ ቡድኖች ንግግር / ድርድር አንቀበልም ማለታቸው እራሳቸውን ነው የሚጎዳቸው። በአማራ ያሉ በርካታ ሰዎች " የቆሙለት ዓላማ ፍትሃዊ ነው " የሚል እምነት/አላቸው ይህንኑ መከራከሪያቸውን ከግጭት ይልቅ በውይይት ማቅረብ አለባቸው።

- በአማራ ክልል ውጊያዎች የሚቀጥሉ ከሆነ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች እንዳለው በውጤቱ የሚሰቃዩት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው።  

- ህወሓት በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ መቆጠብ አለበት።

- የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ኃይሎች በድርድር ተስፋ ሳይቆርጡ መተማመን ለመገንባት የሰላም ውይይትን ሊቀጥሉ ይገባል።

- ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች ትገኛለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት መቆጠብ አለበት። በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ ነው፤ ያን ተፈጻሚ ማድረግ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ ይችላል።

- ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት ሊፈጸም ይገባል።

- ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ስቃይ ምክንያት ከመሆን መገታት አለባቸው።

- የታጣቁ ኃይሎች ት/ቤቶችን፣ ጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ ማቆም አለባቸው። የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት ሊኖር ይገባል። ይህም ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ማድረግን ይጨምራል።

- ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የለውም። ውይይት ትኩረት ሊደረግበት ይገባል።

- ምንም እንኳን ፍጹም ሊሆን ባይችልም፣ ሁሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት ይገባል።

#USEmbassyAddisAbaba
#VOA
#EthiopiaInsider

@tikvahethiopia