TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በነዚህ ወጣቶች ያለጊዜ ሕልፈት የተሰማኝን ሐዘን ገልፃለሁ "  - ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ

ከትላንት በስቲያ ታህሳስ 10 /2015 በመዲናችን አዲስ አበባ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኛ አብራው የምትኖረውን እጮኛውን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኃላ እራሱን ከ13ኛ ፎቶ ወርውሮ (መገናኛ አምቼ ፊት ለፊት ባለዉ የፌደራል ዳኞች መኖሪያ ጊቢ) ህይወቱን ማጥፋቱ በርካቶችን አሳዝኗል የመዲናይቱም መነጋገሪያ ሆኗል።

ዳኛው ትንሳኤ በላነህ የሚባል ሲሆን በዕለቱ እራሱን ከ13 ፎቅ ላይ ወርውሮ ከማጥፋቱ በፊት አብራዉ የምትኖረዉን እጮኛውን ህይወት አጥፍቷል።

ህይወቱ ከማለፉ ከሰዓታት በፊትም በ " ፌስቡክ ገፁ " ላይ ፅፎታል የተባለ አንድ መልዕክትም በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ የብዙሃን መነጋገሪያ ሆኗል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕ/ት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ ፤ ክስተቱ በጣም አሳዛኝ መሆኑን ገልፀዋል።

" ባልተጠበቀ ሁኔታ እጮኛቸውን በመግደል ራሳቸውን ያጠፉት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዳኛ ተንሳይ በላይነህ ሞት በጣም አሳዛኝ ነው " ያሉት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ፤ " ዳኛው #መደበኛ_ያልሆነ ጠባይ ያሳዩ እንደነበረ ይህ ሁኔታ ከተከሰተ በኃላ ተጠቁሟል " ሲሉ ገልፀዋል።

" የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት መደበኛ ሥራ መሥራት የሚችሉ ሰዎች ሥራቸውን እያከናወኑ አንዳንድ ጊዜ የአእምሮ ጤንነት ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ፤ " ያሉት የጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዜዳንቷ " እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ሲታዩ እገዛ ሊያደርግ ለሚችል ክፍል ማሳወቅ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

በወጣቶቹ ያለጊዜ ሕልፈት ሐዘን እንደተሰማቸው የገለፁት ወ/ሮ መዓዛ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

@tikvahethiopia