TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ራያ አላማጣ⬇️


በራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ አንስተው አደባባይ ከወጡ ሰዎች መሀከል ሶስቱ #መሞታቸው ተሰማ፡፡

የራያ አላማጣ የከተማው አስተዳደር አስተዳዳሪ አቶ ሀብቶም ወረታ ዛሬ ለሸገር FM 102.1 እንደተናገሩት፣ የማንነት ጥያቄን መሰረት በማድረግ በተነሳው ተቃውሞ በፀጥታ ሀይሉና በነዋሪው መሀል #ግጭት መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

ትናንትና እሁድ የማንነት ጥያቄ እና የመልካም አስተዳደር ጎድሏል ያሉ የራያ አላማጣ ወጣቶች በከተማዋ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ለወራት የዘለቀው የራያ የማንነት ጥያቄ ጉዳይን በቅጡ ለመፍታት ለምን ከሚመለከታቸው ጋር አልተወያያችሁምና አልፈታችሁም ያልናቸው የከተማው አስተዳዳሪ ጥያቄው የጥቂቶች ነው ብለዋል፡፡

የራያ አላማጣ የማንነት ጥያቄ ላለፉት ወራት በሰፊው ከመደመጥ አንስቶ `የራያን ህዝብ እናድን” የሚሉ ዘመቻዎችና ሰልፈኞች በርክተዋል፡፡

በትናንትናው እለት በራያ አላማጣ ከተማ ለሰልፍ የወጡ ወጣቶች የሞቱት ከክልሉ ልዩ ሀይል ጋር በተፈጠረው ግጭት መሆኑንም አቶ ሀብቶም ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በካሊፎርንያ መዝናኛ ቤት ውስጥ በተከፈተ ተኩስ የፖሊስ ባልደረባን ጨምሮ #በትንሹ አስራ ሁለት ሰዎች #መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

የካሊፎርንያ ፖሊስ እንዳስታወቀው ትላንት ምሽት ቦርደር ላይን ባር ላይ በተከፈተ ተኩስ ከሞቱት አስራ ሁለት ሰዎች በተጨማሪ አስር ግለሰቦች ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል፡፡

ጥቃቱን እንደፈፅመ የተጠረጠረው ግለሰብ በመዝናኛ ቤት ውስጥ ሞቶ የተገኘ ሲሆን እስካሁን ስለማንነቱ ተጨማሪ መረጃ አለማግኘቱን ፖሊስ ተናግሯል፡፡

ተጠርጣሪው አውቶማቲክ መሳሪያ መጠቀሙን የአይን እማኞችን ጠቅሶ ፓሊስ አስታውቋል፡፡

በመዝናኛ ቤቱ ውስጥ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች እንደነበሩ የፖሊስ ቃል አቀባዩ ኤሪክ ቤሹ ጠቁመዋል፡፡

ተጠርጣሪው በመዝናኛ ቤቱ የተኩስ እሩምታውን ከከፈተ በኋላ በስተመጨረሻ እራሱን ሳያጠፋ እንዳልቀረ ፖሊስ ተናግሯል፡፡

ተኩሱን ተከትሎ በርካቶች መስኮት በመዝለል ለማምለጥ የሞከሩ ሲሆን ሌሎች መጸዳጃ ቤት በመደበቅ ህይወታቸውን አትርፈዋል ነው የተባለው፡፡

ምንጭ፦ ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በታንዛኒያ 14 ኢትዮጵያዊያን መኪና ውስጥ ተፋፍገው #መሞታቸው ተሰምቷል፡፡ ሟቾቹ በዛምቢያ ወይም በማላዊ በኩል አቋርጠው ደቡብ አፍሪካ ለመግባት ያለሙ ስደተኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጧል፡፡

Via~wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ቅዝቃዜ እስካሁን ቢያንስ ስምንት ሰዎች #መሞታቸው ተገለጸ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ሜድ ዌስት የተከሰተው ቅዝቃዜ በአስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አደገኛ ነው፡፡ አደገኛና ገዳይ በተባለው ቅዝቃዜ አንድ ተማሪ ከኮሌጅ ውጭ ሞቶ የተገኘ ሲሆን ሌሎች ስድስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡ ከሟቾቹ በተጨማሪ በቅዝቃዜው ክፉኛ የተጎዱ ነዋሪዎች የሚገኙ ሲሆን በሆስፒታሎች እንክብካቤና ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡ቅዝቃዜው በተከሰተባቸው የአሜሪካ ግዛቶች ከፍተኛና አደጋ አድራሽ በረዶ በአገሪቱ መጣል መጀመሩም የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡ በአብዛኛው የአሜሪካ ግዛት ቅዝቃዜው ከዜሮ በታች ሲሆን ዘጠኝ ሚሊዮን የአሜሪካ ነዋሪ ከአስራ ሰባት ሴንቴግሬድ በታች የሆነ ቅዝቃዜ በማስተናገድ ላይ ይገኛል፡፡ እንደ አሜሪካ ሜትሮሎጂ ዘገባ የአሜሪካዋ ሶስተኛ ከተማ ቺካጎ በታሪኳ ከፍተኛ የሆነውም ኔጌቴቭ 32 ቅዝቃዜ ዛሬ እንደምታስተናግድ አመልክቷል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETH ማጠቃለያ🗞ጥር 23/2011 ዓ.ም.

ከትራንስፓርት ሚንስቴርና ከሌሎች ሚንስቴር መስሪያ ቤቶች የተወጣጣው የሉኡካን ቡድን የጅቡቲ ወደብን ጎብኝቷል።
.
.
ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ በምዕራብ እንዲሁም ምሥራቅ ጉጂ በኢትዮጵያ መከላከያ ኃይልና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች መካከል በታካሄደ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉን በርካቶች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተናግረዋል።
.
.
ከአመት በፊት ሳውዲ አረቢያ ጀምራው የነበረውን መጠነ ሰፊ የፀረ-ሙስና ዘመቻ እንዳጠናቀቀች አስታውቃለች፡፡ የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት 100 ቢሊዮን ዶላር በጥሬ ገንዘብ እና በቁስ መልክ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ሰዎች መሰብሰቡን አስታውቋል።
.
.
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር በቅርቡ የፀደቀውን #የስደተኞች_አዋጅ በመቃወም ነገ በጋምቤላ ከተማ ሊደረግ ለታሰበው የተቃውሞ ሰልፍ ፈቃድ #ከልክሏል
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለ6 ሺህ ነጋዴዎች ግብር ሰርዣለሁ ብሏል፡፡ ግብር ስረዛው ከ2003 እስከ 2010 ዓ.ም ባለው ጊዜ ከፍተኛ የግብር ተመን ተጥሎባቸው አቤቱታ ሲያቀርቡ የቆዩትን ነጋዴዎች ያካትታል፡፡
.
.
4ኛው የህዝብና ቤት ቆጠራ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምሮ ይካሄዳል።
.
.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህግን ተከትለው የሚሰሩ የሪል ስቴት አልሚዎችን እንደሚደግፍ ነገር ግን ህገወጥ የሆኑት ላይ #ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
.
.
በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ በጫነው አሸዋ ላይ 31 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
.
.
በቴፒ ከተማ ከትንላንት ጀምሮ ዳግም #ያገረሸው #አለመረጋጋት ዛሬም ቀጥሏል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ ውሏል። ከተማዋ በፀጥታ ሃይሎች በከፍተኛ ደረጃ እየተጠበቀች ነው።
.
.
ዛሬ በስራ ላይ የሚውለውን የነዳጅ ዋጋ መጨመር ተከትሎ ምንም አይነት #የትራንስፖርት_ታሪፍ  ጭማሪ #እንደማይኖር የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል።
.
.
ጅቡቲ በተካሄደው 15ኛው የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይ የተካፈሉ የኢትዮጵያ ልዑካን ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያይተዋል።
.
.
በኦሮሚያ ክልል ለመንግስት ሰራተኞች #አዲስ የስራ ምደባ እየካሄደ መሆኑን የክልሉ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አስታውቋል።
.
.
#ኮማንድ_ፖስቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 3 ወረዳዎች ላይ በቁጥጥር ስር ካዋላቸዉ 528 ተጠርጣሪዎች 440 የሚሆኑትን በነፃ አሰናብቷል።
.
.
የአዋሽ ወልድያ ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጀክት የመጀመሪያው ምዕራፍ የሆነው ከአዋሽ እስከ ኮምቦልቻ ያለው 270 ኪሎ ሜትር የባቡር መንገድ ግንባታ 97 በመቶ #መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ገልጿል።
.
.
በሱማሌ ክልል ከምሽቱ 4 ሰዓት ጀምሮ ሰዓት ዕላፊ ገደብ ተጥሏል፡፡ የአደባባይ ስብሰባም ተከልክሏል፡፡
.
.
#ቴዎድሮስ_አዲሱ(ቴዲ ማንጁስ) በ80 ሺህ ብር ዋስ ቢፈቀድለትም #በሙስና_ወንጀል ተጠርጥሮ በእስር ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።
.
.
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ለሚያልፉ ዐለም ዐቀፍ መንገደኞች #የነጻ ጉብኝት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡
.
.
የኢትዮጵያ ሚዲያ ካውንስል፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ዘርፍ ማህበር እና #የሰላም_ሚኒስቴር በጋራ በመሆን የሰላም ሚዲያ ህብረት ትስሰር ለመፍጠር የሚያስችል ውይይት ዛሬ ማምሻውን አካሂደዋል።
.
.
የሐረሪ ክልል የሰላምና ጸጥታ ሁኔታ #መሻሻል ማሳየቱን የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ጉዳይ ቢሮ  አስታውቋል።
.
.
#ብሄሬን መሰረት ተደርጎ ጥቃት ተፈፅሞብኛል በሚል በሀሰት የሽንት መሽኛ #ብልቱን በፋሻና ፕላስተር በመጠቅለል ግጭት ለመቀስቀስ የሞከረው ግለስብ ድሬ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።
.
.
በአዲስ አበባ ከተማ በዳቦ ላይ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ አግባብነት የሌለውና ህብረተሰቡን ያላማከለ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
.
.
በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላውያን አንድ #ኢትዮጵያዊ በእስራኤል ፖሊስ መገደሉን በመቃወም ቴላቪቭ ውስጥ ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል።
.
.
በአሜሪካ በተከሰተው ከፍተኛ ቅዝቃዜ እስካሁን ቢያንስ ስምንት ሰዎች #መሞታቸው ተገለጸ፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው በአሜሪካ ሜድ ዌስት የተከሰተው ቅዝቃዜ በአስር አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አደገኛ ነው፡፡
.
.
ምንጭ፦ etv፣ የጀርመን ራድዮ፣ ኢ.ፕ.ድ.፣ ዋዜማ ራድዮ፣ fbc፣ ኢዜአ፣ bbc፣ VOA፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
.
.
ሰላም እደሩ!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
#TikvahEthiopia #ቲክቫህኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኮንግ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በተከሰተ የባቡር #መገልበጥ አደጋ በትንሹ 24 ሰዎች #መሞታቸው ተሰምቷል። ከሟቾች መካከል አብዛኛዎቸ ህጻናት ናቸው ተብሏል። በካሳይ ገዛት በደረሰው አደጋ ከ30 በላይ ሰዎችም አካላዊ ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው የተጠቆመው። የእቃ ማጓጓዣ ባቡሩ ሰዎችንም አሳፍሮ ሲጓዝ አደጋው የደረሰ ሲሆን በርካታ ተሳቢዎቹ ወደ ወንዝ መግባታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

Via ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ባህርዳር #ጎንደር

ባህር ዳር ከተማ ከትላንት ለሊት ጀምሮ ዝምታ ሰፍኖባት እንደምትገኝና ዛሬ የሟቾች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም እንደነበር ነዋሪዎቿ ተናግሩ።

ባለፉት ቀናት በከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ስትናጥ የነበረችው ባህር ዳር ከተማ ከለሊት ጀምሮ ፀጥ ብላ መዋሏን ነዋሪዎች መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ በባህር ዳር በግጭቱ የሞቱ ሰዎች ስርዓተ ቀብር ሲፈፀም መዋሉን ነዋሪዎቹ አመልክተዋል።

ትላንት በቀበሌ 13 ፣ 14 እና 16 በነበረ ውጊያ በርካታ ሰዎች #መሞታቸው እና #መጎዳታቸው ተነግሯል። እነዚሁ ሟቾች ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ በተለያዩ ስፍራዎች ሲፈፀም ውሏል።

ነዋሪዎቹ በጦርነቱ ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈው አብዛኞቹ ከጦርነቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ሰዎች መሆናቸውን ገልጽዋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት (AFP) ያነጋገራቸው ሁለት ዶክተሮች በውጊያው ሰላማዊ ሰዎች ስለመገደላቸው ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፤ የባህር ዳር ነዋሪዎች ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ሬድዮ በሰጡት ቃል ከከተማው ማረሚያ ቤት 2 ሺህ የሚጠጉ ታራሚዎች ሲወጡ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

በጎንደር ዳግሞ ዛሬ ከሰሞኑን የተሻለ መረጋጋት እንዳለ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የመንግሥት ጦር በከተማው ውስጥ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን የተደረደሩ ድንጋዮችን ሲያነሱ መዋላቸውን ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

@tikvahethiopia