TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" ኪዳን ሱር በቆስ ለውጢ " በሚል ለተሰየመው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ሲያነሳሱ የተገኙ የፓለቲካ ፓርቲ አባላት ታሰሩ።
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፣ ውድብ ናፅነት ትግራይ ፣ ባይቶና ዓባይ ትግራይ ፣ ዓረና ለሉኣላውነትና ለዴሞክራስና ፣ ዓሲምባ የተባሉ 5 ቱ የትግራይ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከጳጉሜን 2 እስከ 4 /2015 ዓ.ም በጥምር ለሚያካሂዱት ሰላማዊ የተቓውሞ ሰልፍ በመቐለ ከተማ በመኪና በመዞር በድምፅ ማጉልያ በመታገዘ እየቀሰቀሱ ሳሉ ነው አባላቱ የታሰሩት።
ነሃሴ 30 / 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 በፓሊስ የታሰሩት ገብረኣብ ወልዱና ብርሃነ ኣርኣያ ከሳልሳይ ወያነ ፣ ብርሃነ ዘመን ዮሃንስና ገብሩ ከባይቶና ፣ ጠዓመ ሓጎስና ኣፅብሃ ተኽለ ከውድብ ናፅነት ትግራይና እንዲሁም የድምፅ ማጉልያና መኪና ያካራዩና ባለሙያዎች መሆናቸ የአይን አማኞች አረጋግጠዋል።
ታሳሪዎቹ በቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ፓሊስ ጣብያ ይገኛሉ ብለዋል የአይን እማኞቹ።
የባይቶና ከፍተኛ አመራር አቶ ኪዳነ አመነ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው "... 'ኪዳን ንሱር ቦቆስ ለውጢ ' በሚል በወርሃ ጳጉሜን እንዲካሄድ ለጠራነው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ሲያነሳሱ የነበሩ አባሎቻችን መታሰራቸው ለክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አባሎቻችን ያለ ቅድመ ሁነት በአንድ ሰዓት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ደብዳቤ ፅፈናል ። " ብለዋል።
የመቐለ ከተማ አስተዳደር የተፎካካሪ ፓርቲዎቹ ጋዜጣዊ መግለጫ ተከትሎ ነሃሴ 25/2015 ዓ.ም ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ በኢፌዴሪ አዋጅ ቁጥር 3/1991 የተቀመጠ መብት ቢሆንም የተመረጠው ጊዜ አዲስ አመትና ሃይማኖታዊ በአላት የሚበዙበት በመሆኑ ለማስተናገድ እቸገራሎህ ብሎ ነበር።
የከተማው አስተዳደር ለተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ፀጥታ የማስከበር ግዴታና ሃላፊነት እንዳለበት በመጥቀስ ፤ ይሁን እንጂ በበዓሉ በሚኖረው የህዝብና የመኪና ሰፊ እንቅስቃሴ ምክንያት በሚፈጠር የስራ መደራረብ ምክንያት የቀረበውን ጥያቄ ማስፈፀም አልችልም በማለትም አክለዋል።
የተቋውሞ ሰልፉ የጠሩ 5 ቱ ተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የከተማ አስተዳደሩ ላወጣው መግለጫ በሰጡት ይፋዊ የፅሑፍ መግለጫ ስልፉ ለማድረግ የሚያግድ የህግ ማእቀፍ የለም በማለት መቀጠላቸው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መዘገቡ ይታወሳል።
@tikvahethiopia

#SafaricomEthiopia
በአዲሱ አመት በአዲስ ስልክ ማርሻችንን ወደ ስኬት! በ M-PESA እንክፈል በተመረጡ ስልኮች ላይ እስከ 20% ቅናሽ እናግኝ። በወሎሰፈር ፣ ቦሌ ፣ ጀሞ፣ መስቀል ፍላወር ወደሚገኙ የሳፋሪኮም ሱቆች እንዲሁም ሚሊኒየም አዳራሽ በሚገኘው ባዛር ጎራ በማለት ለአጭር ጊዜ የሚቆየው ቅናሽ እንጠቀም!
#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether

#ኢትዮጵያ
አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ተጠየቀ።
ጥያቄውን ያቀረቡት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ነው።
እነዚህ ድርጅቶች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ነውጥ አዘል ግጭቶች የተቀሰቀሱት / የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባሕል በመኖሩ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።
ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉንም የማኅበረሰብ አካላት የሚያሳትፍ አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ (የሰላም ኮንቬንሽን) ተመቻችቶ የአጭር ጊዜ፣ የመካከለኛ ጊዜ እና የረዥም ጊዜ ግጭትን የመከላከል፣ የመፍታት እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች የሚጠናከሩበት አገራዊ ፍኖተ ካርታ እንዲዘጋጅ ይፋዊ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በተጨማሪ የሲቨል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ ፤ ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት እንዲሰፍን አበክረው ጠይቀዋል።
ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ (victim centered) የተጠያቂነት ስርዓት መስፈን በሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እና በግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ፍትሕ የሚሰጥ ከመሆኑም ባሻገር፥ የበቀል እዙሪትን ለመግታት እና ለፍትሕ ተቋማት ተዓማኒነትም ዋልታ እንደሆነ ገልጸዋን።
- ለነውጥ አዘል ግጭቶች መንስዔ የሆኑ፣
- ሕዝባዊ እና ብሔራዊ ጥቅምን የሚጎዱ እና ሕጋዊ መሠረት የሌላቸው ውሳኔዎችን ያሳለፉ፣
- በነውጥ አዘል ግጭቶች ውስጥ በመሳተፍ ንፁኃንን ያጠቁ፣
- የጥላቻ ንግግሮችን እና ግጭት ቀስቃሽ ንግግሮችን በአደባባይ ያደረጉ እና ንፁኃንን ለጥቃት ያጋለጡ አካላት በነጻ እና ገለልተኛ የፍትሐዊ የምርመራ እና የዳኝነት ሒደት ተጠያቂ እንዲደረጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ በሐቀኝነት እና ሕዝባዊ ተቀባይነት ባለው መንገድ ወደ ተግባር እንዲገባና በሒደቱም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እና ዓለም ዐቀፍ ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች እንዲሳተፉ ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቶቹ የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም ዘንድ ጠይቀዋል።
" የጥላቻ ንግግሮች እና ግጭት ቆስቋሽ መልዕክቶች ነውጥ አዘል ግጭቶችን የሚያዋልዱ እና የሚያፋፍሙ መሆናቸውን ባለፉት ዓመታት አስተውለናል " ያሉ ሲሆን " የፖለቲካ ልኂቃን፣ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የብዙኃን መገናኛተቋማት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አቀንቃኞች እና ሌሎችም የተዛቡ መረጃዎችን ከማሰራጨት፣ ብሎም ሕዝብን በጅምላ ከሚፈርጁ ወይም ግጭቶችን ከሚቆሰቁሱ እና ከሚያባብሱ የቋንቋ አጠቃቀሞች እና መልዕከቶች ራሳቸውን እንዲቆጥቡ " አሳስበዋል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)
#TikvahFamilyAA

#ኢትዮጵያ አገር ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች ተጠየቀ። ጥያቄውን ያቀረቡት 35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ነው። እነዚህ ድርጅቶች ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ብዙዎቹ ነውጥ አዘል ግጭቶች የተቀሰቀሱት / የተባባሱት ውጥረቶችን በፖለቲካዊ ንግግር እና ምክክር ሳይሆን በኃይል የመፍታት የቆየ ባሕል በመኖሩ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል። …
የአዲስ አመት የሰላም ጥሪ !
35 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለ2016 ዓ/ም አዲስ ዓመት ባስተላለፉት የ " ሰላም ጥሪ " ፦
- አገር አቀፍ የሰላም መድረክ ይመቻች
- ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት ይስፈን
- ፆታዊ ጥቃቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጣቸው
- የተጋላጭ እና ግፉአን ጥበቃ ማዕቀፍ ይዘርጋ
- ሕዝባዊ ተሳትፎ ይረጋገጥ
- የቅድመ ግጭት መጠቆሚያ እና መከላከያ ስርዓት (Early warning System) ይኑር
- የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሳይስተጓጎል ይቀጥል
- የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም
- የሲቪክ ምኅዳሩ ጥበቃ ይደረግለት
- ባለድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ይወጡ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
ጥሪያቸውን ያቀረቡት ዛሬ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሰጡት ይፋዊ መግለጫ ነው።
35ቱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አዲስ አበባ ተመሳሳይ " የሰላም ጥሪ " ለማቅረብ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጡ ከመንግስት መጣን ባሉ አካላት መከልከላቸውና መግለጫቸውን በኦንላይን ለመስጠት መገደዳቸው ይታወሳል።
ዛሬ የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ከላይ ያንብቡ።

ዓሲምባ የተባለው የፓለቲካ ፓርቲ " ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ " በሚል መፈክር ጳጉሜን 2 /2015 ዓ.ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ራሱን ማግለሉ አስታወቀ።
ፓርቲው ይህንን ያሳወቀው በሊቀመንበሩ አቶ ዶሪ አስገዶምና በፓርቲው በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨው መረጃ አማካኝነት ነው።
" የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ እንደሆነ የሚመለከታቸው አካላት በማስረጃ አስደግፈው አስረድተውናል " ያሉት ሊቀመንበሩ " ህግ ይከበር እያልን ህግ መጣስ ህዝባችንን ስለማይመጥን ከተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ራሳችን ለማግለል ወስነናል። ሁሉም ከህግ በታች ነው " ብለዋል።
መረጃው ከመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል የተላከ ነው።

#Update ዓሲምባ የተባለው የፓለቲካ ፓርቲ " ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ " በሚል መፈክር ጳጉሜን 2 /2015 ዓ.ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ራሱን ማግለሉ አስታወቀ። ፓርቲው ይህንን ያሳወቀው በሊቀመንበሩ አቶ ዶሪ አስገዶምና በፓርቲው በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨው መረጃ አማካኝነት ነው። " የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ እንደሆነ…
#Update
ጳጉሜን 2/2015 ዓ/ም በ5 የፓለቲካ ፓርቲዎች በመቐለ እንዲካሄድ ከተጠራው የተቋውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ፓሊስ የፓርቲ አባላት እና አመራሮችን በህግ ቁጥጥር ስር ማዋል መቀጠሉን የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
በዚሁ መሰረት፦
- የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር ሃያሉ ጎዲፋይ ፣
- የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ.ር ደጀን በርሀ ፣
- የባይቶና ዓባይ ትግራይ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርሀ ጳጉሜን 1/2015 ዓ.ም ረፋድ 4:00 ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቀዋል።
ነሃሴ 30 / 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ላይ ገብረኣብ ወልዱና ብርሃነ ኣርኣያ ከሳልሳይ ወያነ ፣ ብርሃነ ዘመን ዮሃንስና ገብሩ ከባይቶና ፣ ጠዓመ ሓጎስና ኣፅብሃ ተኽለ ከውድብ ናፅነት ትግራይና እንዲሁም የድምፅ ማጉያያና መኪና ያካራዩና ባለሙያዎች ፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወቃል።
መረጃው የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል ነው።
More : @tikvahethiopiatigrigna

በቅበት የሆነው ምንድነው ?
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፤ በስልጤ ዞን ውስጥ " ቅበት ከተማ " የሰው ህይወትን የቀጠፈ አለመረጋጋት መከሰቱን ለማውቅ ተችሏል።
ጉዳዩን በተመለከተ ምን ተባለ ?
የእስልምና ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ የሚዲያ ምንጮች እንደገለፁት ከሆነ የችግሩ መነሻ " ተደርጓል በተባለ መተት / ድግምት ምክንያት የልጆች ጤና እየታወከ ፣ ከትምህርት ገበታቸውም እንዲርቁ እየሆነ ነው " የሚል ነው።
ይህንን መሰል ጉዳይ ከዚህ ቀደምም በቅበት ከተማ ሲስተዋል የነበረ ነው የሚሉት የአካባቢው የእስልምና እምነት ተከታዮች በዚህም ምክንያት በ2015 ከ260 በላይ ተማሪዎች ቤታቸው እንዲውሉ ሆነዋል ሲሉ ጠቁመዋል።
ከሰሞኑን ደግሞ በቅበት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመመዝገብ የሄዱ ተማሪዎች እራሳቸውን ስተው መውደቃቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት በከተማው የሱቅ ባለቤቶች ፣ የስራ ቦታ ያላቸው ሰዎች እና ወጣቶች ለዚህ ችግር መፍትሄ ነው በሚል በተለያዩ ቦታዎች ሞንታርቦ በሚባለው የድምፅ ማጉያ " ቁርዓን " በመክፈት ተከስቷል ያሉትን በሽታ ለመከላከል በሚሞክሩበት ወቅት የፀጥታ ኃይሎች ሞንታርቦዎችን መሰብሰብ መጀመራቸውና ወጣትና አባቶችን መደብደብ መጀመራቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት ግጭት ተፈጥሮ የ1 ሰው ህይወት ጠፍቷል፤ በርካታ ወጣቶችም ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። በከተማው ውስጥ የሚገኝ " አብድልአዚዝ መስጂድ " መጎዳቱንም ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።
በከተማው ከተፈጠረው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ግን የኦርቶዶክስ አማኞች ላይ ትንኮሳና ጥቃት መፈፀሙን የሐዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት አሳውቋል።
የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መላከ ሕይወት ንጉሴ ባወቀ ለቤተክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን በሰጡት ማብራሪያ ፤ በከተማይቱ ሃይማኖትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተፈፅሟል ብለዋል።
" ከሁለት ወራት በፊት ጀምሮ በአካባቢው ስላለው ጉዳይ ስንከታተል ነበር ፤ ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ አንዳንድ ትንኮሳዎች ነበሩ። ' የሙስሊም ልጆች ይወድቃሉ ' በሚል እነ እከሌ ደግመውባቸው ነው ፤ እንዲህ ተደርጎባቸው ነው በሚል ለኦርቶዶክሳዊነት እና ለትምህርቷ የማይመጥን ነገር እየሠጡ ካህናትን እየወንጀሉ ከጀርባ ሌላ ተልዕኮ ያላቸው ሰዎች እንዲህ ሲያደርጉ ቆይተዋል " ብለዋል።
" ልጆች ይወድቃሉ፣ ታመውብናል፣ ይሄን ያደረጉት ኦርቶዶክሶች ናቸው። ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ፣ ባጃጅ የሚነዱ እነሱ ናቸው እየተባለ ማጥቃት፣ በሞተራቸው ሰው እንዳይገለገል ማድረግ ፣ ከጎረቤት መለየት ፣ ማግለል ሲደረግ ነበር በዚህም በብፁዕ አባታችን ፍቃድ ከዞኑ ፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ጋር ተወያየን ሀዋሳም ደብዳቤ አስገብተናል ይህን ነገር ተከታትለው እንዲያስቆሙ ጠይቀናል " ብለዋል።
" በኃላም ጉዳዩ ይበርዳል ብለን ስንጠብቅ ሞንታርቦ በየበራቸው አቁመው የመፈወሻ ትምህርት ነው ፀሎት ነው ብለው ነገር ግን የስድብ ፣ ኦርቶዶክስን የሚያጥላላ ፣ ሃይማኖትን የሚያንቋሽሽ ብዙ ነገር ማድረግ ጀመሩ ፣ ግለሰቦችንም እየያዙ መደብደብ ሲጀምሩ ነው የፀጥታ ኃይል ገብቶ ሞንታርቦውን አንሱ ልዩነት የሚፈጥር ነው ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ ነው ፣ ድብደባውንም አቁሙ ብሎ ወደ እርምጃ ሲገባ ነው ለምን ይሄን ተባልን ብለው መንገድ መዝጋት የጀመሩት። መንገዱን ለማስከፈት የፀጥታ ኃይል ሲሞክር ወደ ፀጥታ ኃይሉ ጥቃት ተጀምሮ ነበር " ሲሉ ተናግረዋል።
" የነበረው የፖሊስ ኃይል ጥቂት ስለነበር እነሱ ዞር ሲሉ ወደ ምዕመናን ቤት ጥቃት ተሰንዝሮ 13 ቤቶች እና ንብረቶቻቸው መኖሪያ፣ ሆቴል፣ ሱቅ ተሰብረው ተዘርፈው ተቃጥለዋል ፤ ፈርሰዋል። ይሄን ለምን አስቆማችሁ በሚልም የአመራሮችን ቤቶች የማፍረስ እና የማቃጠል ተግባር ተፈፅሟል " ብለዋል።
ይህ ሁኔታ ወደ ቤተክርስቲያን እንዳይመጣ የሰዎችም ህይወት እንዳይጠፋ ስጋት ስላለ የፌዴራልም ሆነ የክልል መንግሥት ከለላ እንዲያደርጉ መጠየቁን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
የቅበት ከተማ አስተዳደር ምን አለ ?
አስተዳደሩ ባወጣው መግለጫ ፤ በህዝቡ መካከል ያለውን የዘመናት አብሮነትና አንድነት ሊሸረሽሩና ሊያቃቅሩ የሚችሉ ፀብ አጫሪ ጉዳዮች አልፎ አልፎ እየተከሰቱ ነው ብሏል።
ከትላንት በስቲያ የተፈጠረውን ችግር " የሀይማኖት መልክ " ለመስያዝ ጥረት ቢደረግም በሃይመኖት አባቶችና በሀገር ሽማግሌዎች፤ በወጣቶችና በፀጥታ አካላት ትብብር ሰላምና መረጋጋት ለመፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
ግጭቱ የአካባቢውንና የስልጤ ህዝብ የዘመናት እሴት የማይገልፅ ነው ብሏል።
በሌላ በኩል ፤ ግጭት የሚፈጥሩ አካላትን ለይቶ በማውገዝ ፤ ጉዳዩ እንዲባባስና ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲሄድ ሩቅ ሆነው በተሳሳተ መንገድ እያራገቡ ያሉ አካላትን ህዝቡ ሊታገላቸው ይገባል ብሏል።
በተፈጠረው አለመግባባት የአንድ / 1 ሰው ህይወት ማለፉን ያረጋገጠው የከተማው አስተዳደር 3 ሰዎች በቅበት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና 6 ሰዎች በወራቤ ኮ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል ብሏል።
በተፈጠረው ግጭት በንብረት ላይም ውድመት መድረሱን ገልጷል።
ነዋሪዎች ባደረጉት ርብርብ አለመግባባቱ ሰፍቶ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ አስተዋዕፆ ማበርከታቸውን ጠቁሟል።
አጠቃላይ በተፈጠረው ጉዳዩ ዙሪያ የቅበት ነዋሪዎች ተቀራርቦ በመወያየት ለመፍትሄው በጋራ ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጥሪ አቅርቧል።

ስለ መምህራን ጥያቄ ምን ተባለ ?
የዩኒቨርሲቲ መምህራንን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ " በጥሩ ሁኔታ እየተሠራ " መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ሥራ አስፈጻሚዎች መግለጻቸውን የማኅበሩ አመራሮች ተናገሩ፡፡
አመራሮቹ ይህን ያሳወቁት ትላንትና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በመምህራን እና በሀገር ጉዳይ ከተወያዩ በኃላ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።
የማህበሩ ፕሬዜዳንት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፤ እንደተለመደው አሠራር የአጠቃላይ ትምህርት መምህራን በሚሠሩበት አካባቢ የመኖሪያ ቦታ የማግኘት አሠራሩ የሚቀጥል ሆኖ የዩኒቨርሲቲ መምህራንን መኖሪያ ቤት በሚመለከት ግን ውይይት እየተደረገበትና ጥሩ ምላሽ ሊገኝ እንደሚችል እንደተረዱ ተናግረዋል፡፡
" የዩኒቨርሲቲ መምህራን የቤት ጥያቄን በሚመለከት ከዚህ በፊት የተነሳ ጉዳይ አለ፡፡ ውይይት እየተደረገበት ሲሆን ዕልባት እንዲያገኝ እየተሠራበት እንደሆነ ነው የተገለጸልን " ሲሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ስላገኙት ምላሽ አስረድተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲ መምህራን ከዚህ በፊት ሲያነሱት ስለነበረው #የደመወዝ ጥያቄን በሚመለከት ማኅበሩ አንደኛው ይዞት የሄደው ጉዳይና የተወያየበት ሲሆን ጠ/ሚኒስትሩ ለደመወዝና መሰል ጥያቄዎች በየደረጃው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንዳደረጉባቸው እንደነገሯቸው ገልጸዋል፡፡
የደመወዝ ጭማሪውን በሚመለከት፣ የኑሮ ውድነትን በአጠቃላይ የማቅለል ሥራ እንደሚሠራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹላቸው፣ ይህንንም ለማስተካከል ጥረት እንደሚያደርጉ በውይይታቸው ላይ እንደተነሳ ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
የማኅበሩ አመራሮችም ስለ ደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ ቁርጥ ያለ ምላሽ ለማግኘት ጠብቀው እንዳልሄዱም ተናግረዋል፡፡
" ማናችንም ደመወዝን በሚመለከት ‹ከዛሬ ጀምሮ ይህን ያህል ጨምረናል› የሚል መልስ አንጠብቅም፡፡ ችግሩ እንዳለና ትኩረት ተሰጥቶ መንግሥት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲፈጽም ነው ያነሳነው " ሲሉ የማህበሩ ፕሬዜዳንት ገልጸዋል።
የማኅበሩ አመራሮች ከመምህራን ጥያቄዎች በተጨማሪ ፦
- የሙያ ጥያቄና የመምህርነት ሙያ ምንነትን በሚመለከት፣
- የት/ቤቶች አቅምና ግብዓት ፣
- ለመምህራን ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠርን በሚመለከት
- ማህበሩ ለመገንባት ስላቀደው ህንፃና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።