TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.98K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ስለ ዩኒቨርሲቲዎች የተናገሩት...

"በዩኒቨርሲቲዎች ላይ እያገኘን ያለነው መረጃ ረብሻ የሚፈጥሩት፤ በብሄር የሚያጋጩት፤ ሰው በጩቤ የሚወጉት የተላኩ የተገዙ ሰዎች ናቸው። ያሰማራቸው የላካቸው ከጀርባቸው ያለ የተደራጀ ኃይል ነው። ይሄን የሚያደርጉት አማራ ክልል ያለውን ኦሮሞ በጩቤ ስንወጋው ኦሮሞ በሙሉ ያምጻል፤ በተመሳሳይ ኦሮሞ ክልል ያለው አማራ በጩቤ ሲወጋ አማራው በሙሉ ያምጻል በሚል የተሳሳተ ስልትና እቅድ ነው። የዚህ የሴራ ፖለቲካ ቀመር አባትና ባለቤት አለው። በዚህ ስሌታቸው ሕዝቡ አምጾ ወደ እርስ በእርስ መተላለቅ ይገባል ብለው ነው ያቀዱት። አንዳንዶች የዴሞክራሲ ምህዳሩ ይስፋ እየተባለ እያወቅን ዝም ያልናቸው ኃይሎች አሉ። በዚህ ዓመት የተቀመጠው አቅጣጫ ሕግ የግድ መከበር እንዳለበት ወስነናል። አሁን አንጻራዊ ሰላም አለ። ሆን ተብሎ እንዲበጠበጥ በሚፈልጉ ኃይሎች የሚመሩ ተልእኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አልፎ አልፎ ብልጭ ድርግም የሚሉ እንቅስቃሴዎች አሉ። በእነዚህ ላይም እርምጃ ይወሰዳል።"

#FDRE_Defense_Force

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDRE_Defense_Force

በአሚሶም ሴክተር 3 ለስድስተኛው ዙር ሰላም አስከባሪ ለአየር መንገድ ደህንነትና ለበረራ ክትትልና ቁጥጥር ኦፊሰር ሙያተኞች ስልጠና ተሠጠ፡፡ ስልጠናው የመንገደኞች ደህንነት ተጠብቆ ያለስጋት በረራቸውን እንዲያከናውኑ ለማድረግ ሲሆን በተለይም ከተሰማራንበት ግዳጅ አንፃር ለበረራ ደህንነት አስጊ የሆኑ ነገሮችን እንዴት መፈተሸና መቆጣጠር እንደሚቻልና በበረራ ወቅት የሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን መከላከልና የጉዳት መጠናቸውን መቀነስ እንዴት እንደሚቻል ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ስልጠናው ለ2 ሳምንታት እንደሚቆይም ከስልጠና ፕሮግራሙ ለመረዳት ተችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDRE_Defense_Force

ሴት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተልዕኮ የመፈፀም አቅማቸዉ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ!

ሴት የሰራዊት አባላቱ የተልዕኮ አፈፃፀም ብቃታቸዉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና አቅማቸዉ ይበልጥ ለማሳደግ ታከታይነት የለው የትምሕርትና ሥልጠና ተግባር በማከናወኑ ሁለንትናዊ ዝግጁነቱን የተሞላ እንዳደረገለት በ7ኛ ወጋገን ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የ2 ሞተራይዝድ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል መካሽ ጀበሬ ገለጹ፡፡

በመከላከያ ሠራዊቱ ዉስጥ የሴቶች ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደ ተቋም በከፍተኝ ትኩረት እየተሰራበት መሆኑን የጠቆሙት አዛዡ በብርጌዱ ዉስጥ የሚገኝ ሴት የሰራዊት አባላት እልሕና ወኔ በእጆጉ የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል። በህክምና በመገናኛና ኢንፎርሜሽን እንዲሁም በበርካታ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነዉ አኩሪ ዉጤት ያስመዘገቡ አባላት መኖራቸዉናን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDRE_Defense_Force

" በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራና ዳንጉር ወረዳዎች ከ3 ዓመታት በላይ ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ከ1 ሺ በላይ አመራሮችና አባላት በጉሙዝ ብሔረሰብ ዕርቀ ሰላም ባህል "ማንገማ" መሠረት #ትጥቃቸውን_አስረክበው_እርቅ_አካሂደዋል

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ የሆኑት ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ " በጉሙዝ ባህልና ወግ መሠረት በደም የተፃፈና የታሰረ ቃለ-መሃላ መፈፀሙ ታጣቂዎቹ ለሰላም ቁርጠኛ መሆናቸውን በተግባር ያስመሰከረ ነው " ብለዋል።

ለፈፀሙት ቃለ-መሃላም ሁሉም ተገዥ በመሆን ዘላቂ ሰላምን በማስፈን ቁርጠኝነቱን በተግባር ማሳየት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኮማንድ ፖስቱ በክልሉ ሌሎች ወረዳዎች የሚገኙ ህገወጥ ታጣቂዎችም የአፍራሽ ኃይሎችን ተልዕኮ ከማስፈፀም ተቆጥበው ቅድሚያ #ለሰላም ዕድል መስጠት እንደሚገባቸው ጥሪ አስተላልፏል።

#FDRE_Defense_Force

@tikvahethiopia
#GERD🇪🇹

" የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ፤ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ ፥ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌ/ጀኔራል ደስታ " ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መፈፀም በመቻሉ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብአቶች በሰላም ተጓጉዘው እንዲደርሱ እና ሰራተኞችም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል " ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ #3ኛውን_የውሃ_ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሌ/ጀኔራሉ " የግድቡ ግንባታ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ በትኩረት እየሰራ ነው " ብለዋል።

አክለውም " የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ ዕድገታችንን ለማደናቀፍ #ከሱዳን ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን እየተከታተለ ሴራቸውን እያከሽፈው ይገኛል ፤ በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ሲቪል አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ ግዳጁን በአስተማማኝ ለመወጣት ዝግጁነቱ የላቀ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#FDRE_Defense_Force🇪🇹

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia