TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

" ምክክሩ በመንግሥትም ሆነ በሌላ የውጭ አካላት እንዲጠመዘዝና እንዲመራ አንፈቅድም " - ፕ/ር መስፍን አርአያ

ብዙዎች ከምንም በላይ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ያመጣል ብለው ተስፋ የጣሉበት አገራዊ የምክክር መድረኮች በቀጣይ ዓመት ሕዳር ወር እንደሚጀምሩ ይፋ ሆኗል።

አገራዊ የምክክር መድረኮች ሕዳር ወር (2015 ዓ/ም) እንደሚጀመሩ ይፋ ያደረጉት የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ናቸው።

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ አገራዊ ምክክሩ የቅድመ-ዝግጅት ፣ ዝግጅት፣ ምክክር እንዲሁም የትግበራና ክትትል የተሰኙ 4 ምዕራፎች እንዳሉት ጠቁመዋል።

እስካሁን ባለው ሂደት የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑን ተናግረዋል።

ከቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች መካከል ዋነኛ የሆነው የእቅድ ሥራ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ተጠናቆ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና ግምገማ እንደሚደረግበት ገልፀዋል።

የዝግጅት ምዕራፎች ደግሞ የተሳታፊ ልየታና ሥልጠና እንዲሁም ለአገራዊ መግባባት የተሻሉ አጀንዳዎችን መለየት የሚሉ ጉዳዮችን ያካተተ እንደሆነ ገልጸዋል።

በተያዘው ክረምት የዝግጅት ምዕራፎች ተጠናቀው በመጭው ዓመት ህዳር ወር ላይ የምክክር መድረኮች እንደሚጀመሩ ነው ይፋ ያደረጉት።

ፕ/ር መስፍን የውይይት አጀንዳ የሚቀረጸው ከታችኛው ኅብረተሰብ ክፍል ፍላጎት እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ #ገለልተኛ_የሕዝብ_ወኪሎች በተገቢው መልኩ ይለያሉ ብለዋል።

" ምክክሩ በመንግሥትም ሆነ በሌላ የውጭ አካላት እንዲጠመዘዝና እንዲመራ አንፈቅድም " ያሉት ፕሮፌሰር ማስፍን " #ከውስጥና #ከውጭ ያሉ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ምክክሩ ግቡን እንዲመታ እንሰራለን " ብለዋል።

ምንጭ፦ telegra.ph/ENA-05-14

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የትምህርት ሚኒስቴር በዋናነት ለተገኘው ውጤት የኔ ውድቀት ነው ብሎ ኃላፊነቱን ሊወስድ ይገባል " - ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የትምህርት ሚኒስቴር ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት መመዝገብ ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በጥናት ለይቶ እንዲያቀርብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጠየቀ። በይህ የተጠየቀው በምክር ቤቱ የሰዉ ኃብት ልማት፣ ሥራ…
ለተማሪዎች መውደቅ ማነው ተጠያቂው ?

በህ/ተ/ም/ ቤት የሰዉ ኃብት ልማት ፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ፦

" ... ትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊነቱን ወደራሱ መውሰድ አለበት በምንልበት ጊዜ ፤ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የክልል ትምህርት ቢሮዎችን የሚመሩና እስከ ወረዳ እስከታች ድረስ እንዲሁም የትምህርት አመራሩ በትምህርት ቤት ደረጃ ምን ያህል Shock ሆነዋል ?

ተማሪው እና ወላጁ ብቻ ነው እንጂ ይሄንን እዳ የተሸከመው ሁሉም ባለበት እየሄደ ነው ማንም ኃላፊነት እየወሰደ አይደለም።

ምንድነው እየተወሰደ ያለው እርምጃ ? የትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች፣ ከዛም እስከ ታች ያሉ ዳይሬክተሮች ሁሉም በነበረበት ቀጥሏል። በቃ ተማሪ አለፈ አላለፈ ጉዳያቸው አይደለም፤ ምንም አይቀነስባቸውም ምንም ማስጠንቀቂያ የለም ተማሪ አላሳለፈ አሳለፈ ጉዳዩ አይደለም።

እንዲህ አይነት ሁኔታ ውስጥ መቀጠል አለብን ወይ ? አይደለም ይሄንን ቢያንስ ተጠያቂነት መኖር አለበት ብሎ የሆነ ነገር ማድረግ ያለበት ትምህርት ሚኒስቴር እና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የሚሰሩ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የቢሮ ኃላፊዎች ናቸው። "

ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተጨማሪ ምን አሉ?

- በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ96 በመቶ በላይ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና በላይ ይማምጣት አለማቻላቸው እንዲሁ እንደኖርማል የሚወሰድ አይደለም።

- ይሄን ያህል ተማሪ አለማለፉ እንድምታው ቀላል አይደለም።

- በዚህ ነገር ተጠያቂ የሚሆነው " ሁሉም ነው " የሚለው ነገር አይቸጋሪ ነው። ተጠያቂው everybody ነው ከተባለ nobody ነው ማለት ነው።

- " ሁሉም ተጠያቂ ነው " ማለት እነማናቸው ሁሉም ? ሁሉም የሚለው መፍትሄ አያመጣም። ወላጅ የራሱ ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ትምህርት ቢሮ በየደረጃ ከሆነ ያግባባናል።

- በሀገር ደረጃ አስፈፃሚዎች (እንደ ገንዘብ፣ ጤና...ሚኒስቴሮች) የተደራጁት በራሳቸው ተልዕኮ አኳያ በመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ተልዕኮ ይሄ የኔ ውድቀት ነው ብሎ መውሰድ አለበት።

- ትምህርት ሚኒስቴር ውድቀቱ የኔነው ብሎ ሲወስድ በስሩ ያሉ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ቢሮዎችን ጨምሮ ነው።

- እነዚህ ተማሪዎች ከታች ጀምሮ 50 በመቶና በላይ እያመጡ ነው እዚህ የደረሱት ይህ የሚያሳየው ከታች ጀምሮ የምዘና ስርዓቱ ችግር እንዳለበት ነው። የትምህርት አሰጣጡም ችግር አለበት። አንዳንዶቹ እራሳቸው የማያውቁት እንዲያስተምሩ ይደረጋል፤ አንዳንዶች ደግሞ ኮሌጅ ሳይገቡ፣ ዲፕሎማ ዲግሪ ሳይኖራቸው የሀሰት ማስረጃ አሰርተው ዓመታት ሲያስተምሩ የቆዩ መኖራቸንም በሚዲያ ሰምተናል። ስለዚህ አጠቃላይ ስርዓቱ መፈተሽ አለበት።

- ከታች ጀምሮ ብቁዎች ብቻ ለ12ኛ ክፍል እንዲቀመጡ እያደረግን ነው ?

- ኩረጃ ስላስቀረን ነው ተማሪው የወደቀው የሚለው ሁሉንም ላያስምን ይችላል። በተወሰነ ደረጃ እውነት ነው።

- ተማሪዎች ለምን እንደወደቁ ይጠና። #ገለልተኛ ምሁራን የተካተቱበት ጥናት ይደረግና በዋናነት ተማሪዎች ለምን እንደወደቁ ይታወቅ፤ ሌሎችም ምክንያቶች ካሉ ይጠና።  እንዴት ይሄን ማስተካከል እንደሚቻል መፍትሄ ይመላከት። ያለዛ መፍትሄ አይገኝም።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ስለ ገለልተኛ ጥናት ምን አሉ ?

" ገለልተኛ ጥናት ቢደረግ ለተባለው፤ ይሄ ተቋም (ፓርላማው) ገለልተኛ ስለሆነ ከተቻለ ነፃ የምሁራን ኮሚቴ አቋቁሞ ጥናቱን ለምን አያደርግም ? "

ዶ/ር ነገሪ ፤ ፓርላማው በጥናቱ ሰው ማሳተፍ እንደሚቻል ነገር ግን በባላይነት ኮሚቴ አቋቁሞ ለመስራት ከአሰራር አኳያ ተገቢ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ጥናቱ ለሚኒስቴሩም ግብዓት ይሆናል ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" በተለያዩ አጋጣሚዎች ለእስር እና ለእንግልት ቢዳረግም የበቀል ሰው አልነበረም " - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከፍተኛ አመራር አቶ ጃዋር መሀመድ በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምን አሉ ? " የትኛው እጅ ነው ጨክኖ በቴ ኡርጌሳን በለሊት ከእንቅልፋቸው አስነስቶ የሚረሽነው ? እንዴትስ በቴን የሚያውቅ ሆዱ አስችሎት አይኑ እያያ  ሊገድለው ቻለ ? ወገኖች ይህ ምን ይባላል…
#Update

በአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ አፋጣኝ፣ ገለልተኛና ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጥሪ አቀረበ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ፥ " ኮሚሽኑ ከተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ፓርቲ አባል በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር ተያይዞ ወንጀለኞቹ በህግ እንዲጠየቁ በሁለቱም በኦሮሚያ ክልል እና በኢትዮጵያ ፌዴራል ባለስልጣናት #አፋጣኝ#ገለልተኛ እና #ሙሉ_ምርመራ እንዲደረግ ይጠይቃል " ብለዋል።

አቶ በቴ ኡርጌሳ ትላንት ማክሰኞ ለሊት በትውልድ ከተማቸው መቂ ካረፉበት ሆቴል እንዲወጡ ተደርገው ተገድለው አስክሬናቸው መንገድ ላይ ተገኝቷል።

@tikvahethiopia