TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቅማንት ጉዳይ🔝

የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቅላይ ምኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ የክልሉ መንግሥት እና የቅማንት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ተወያይተው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ሲሉ ይከሳሉ። የክልሉ መንግሥት በበኩሉ ኮሚቴውን ይወቅሳል። ጉዳዩ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን እና የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን ጭምር እያወዛገበ ነው።

የቅማንት እና የአማራ ሕዝቦች ተቀላቅለው በሚኖሩባቸው አካባቢዎች የተቀሰቀሰው #ቀውስ ዛሬም መፍትሔ አላገኘም። የአካባቢው ነዋሪዎች ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ የክልሉ መንግሥት እና የቅማንት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ተወያይተው ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል ሲሉ ይከሳሉ። የክልሉ መንግሥት በበኩሉ ኮሚቴውን ይወቅሳል። ጉዳዩ ከክልሉ ተሻግሮ አዲስ በተቋቋመው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና በትግራይ ክልላዊ መንግሥት መካከል ጭምር እያወዛገበ ነው።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tiivahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ! በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላብራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል በተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። ባለፉት 24 ሰዓት በአጠቃላይ ሰላሳ አራት (34) ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ…
ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ!

የአማራ ክልል 'የምዕራብ ጎንደር ዞን' ማህበራዊ ልማት መምሪያ በድንበር አካባቢ የሚደረገው የሠዎች ዝውውር #አፋጣኝ መፍትሄ ካልተሰጠው በስተቀር የኮሮና ቫይረስ በክልሉ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ከፍተኛ ህሙማን ሊመዘገብ እንደሚችል አስታውቋል።

የአማራ ክልል ባለስልጣናት እንዳሉት በአማካይ በቀን ከ100 እስከ 150 ሰዎች ድንበር #አቋርጠው ወደ ክልሉ ይገባሉ።

ለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከሚደረጉት ከነዚሁ ሰዎች መካከል በምርመራ ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ቁጥር ጥቂት የሚባል አይደለም።

የመምሪያ ኃላፊዋ ወ/ሮ ክሽን ወልዴ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ እንደገለፁት ዞኑ ከጎረቤት ሱዳን 400 ኪሎ ሜትር ይዋሰናል።

በዚህም በየቀኑ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰው ድንበር እያቋረጠ ወደ ዞኑ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ችግሩ 'ከአቅም በላይ' እየሆነ መምጣቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ክሽን ዞኑን፣ ክልሉንና አገሪቱን ከሚመጣው አስከፊ #ቀውስ ለመታደግ በየደርጃው ያለው አካል አፋጣኝ ትኩረትና ምላሽ እንዲሰጥ አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዳሉት ከሱዳንና ከጅቡቲ አካባቢዎች ድንበር አቋርጠው ከሚገቡ ሰዎች ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር ከፌደራል መንግስት ጋር በጋራ የምንፈታው ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ። * " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት…
" ... ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ እንመክራለን " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት

የአማራ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ " ሲል #አስጠነቀቀ

የክልሉ መንግሥት ፥ በአሁን ሰዓት የወልቃይት  ጠገዴ ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ ለረጅም ዓመታት በ " ህወሓት " በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረው የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተመለሰበት እንደሆነ ጠቁሟል።

ህዝቡም እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል ነው ብሏል።

" የፕሪቶሪያው የሠላም #ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም #በትምህርቱም_መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል " ሲል ገልጿል።

ክልሉ ፤ እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማር መብታቸው እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ገልጿል።

የትምህርት ስርዓቱን ሰበብ በማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ እንዳወጣ ጠቁሟል።

ይህም " ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም " ሲል ተችቷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ፥ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሀገራችንን እና ሁለቱን ክልሎች ወደ #ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር  እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን " ብሏል።

ሙሉ መግለጫ ፦ https://t.iss.one/tikvahethiopia/86444

@tikvahethiopia