TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለሚመለከተው አካል‼️

የአምና ወይም 2010 #የወርቅ_ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች እስካሁን ስኮላርሺፕ እንዳላገኙ ለTIKVAH-ETHIOPIA በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የወርቅ ሜዳሚያ ተሸላሚ ተመራቂዎቹ እንዳሉት፦ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ ቃል በገቡልን መሰረት ውጪ ሀገር scholarship እንደ ሚሰጠን በሁሉም የሚዲያ የተነገረ ነበር። ፕሬዘዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ በበኩላቸዉ የውጪ ሐገር scholarship ባይሳካ ሐገር ውስጥ ታገኛላቹ ተብለን ነበር። ነገር ግን እስከ አሁን ምንም ነገር የለም። በተለያየ ሚዲያ እንዳገኘን ሲወራ ነበር። በተደጋጋሚ ትምርት ሚኒስቴር Dr. ጥላዬን እና ዶክተር #ሳሙኤልን ብንጠይቅም #መልስ ሊሠጡን አልቻሉም።" ብለዋል። ብዛታቸው 395 አካባቢ እንደሚሆን የተናገሩት ተመራቂዎቹ የሚመለከተው የመንግስት አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሙዱላ⬆️በከምባታና ጠምባሮ ዞን ጠምባሮ ወረዳ ሙዱላ ከተማ በዛሬው ዕለት ህዝባዊ ሰልፍ ተደርጓል። የሰልፉ አስተባባሪ ኮምቴ እንደተናገረው ሰልፉ ደኢህዴን የጠምባሮን ልዩ ወረዳ የመሆን የዘመናት ጥያቄን በቸልታ በማለፉና ህዝቡም ላለፉት 15 ዓመታት ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ሲጠይቀው የኖረ መሠረታዊ ጥያቄው በመሆኑ ለህዝብ ጥያቄ አስፈላጊው #መልስ ሊሰጥ ይገባል በማለት መሆኑ ተገልጿል። ሰልፉ ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን የሰልፉ ተካፋዮች ነግረውናል።

ምንጭ፦ ሀ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስራ አቁመዋል...የኢንተርንሺፕ ተማሪዎች!!

ለጥያቄዎቻችን ተገቢ #መልስ ይሰጠን ያሉ #የአርሲ_ዩኒቨርሲቲ የህክምና ኢንተርንሺፕ ተማሪዎች ስራ አቁመዋል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩኛል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ተመዝቢዎች ፦ " ... በ14ኛው ዙር የዕጣ አወጣጥ የከተማ አስተዳደሩ ቤቶች በቴክኖሎጂ ሆነ በማኑዋል ዕጣ የማውጣት ሂደቶች በሚፈጠሩ ችግሮች ሊወጣለት ከሚገባው ባለእድለኛ ወጪ ለሌላ ለማይመለከተው አካል እንዳይተላለፉ የሄደበትን ርቀት እናደንቃለን፡፡ ነገር ግን ይህ ቁርጠኝነት በባለ3 መኝታ 2005 ዓ.ም የ20/80 ተመዝቢዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ እንዲገለጽ እንፈልጋለን፡፡…
#መልስ_ያላገኘው_ጥያቄ

የ2005 የ20/80 የባለ 3 መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ቆጣቢዎች ባለፈው ሙሉ በሙሉ የተሰረዘው ዕጣ ሳይወጣ የእነሱ ጉዳይ ላይ የአ/አ ከተማ አስተዳደር ግልፅ የሆነ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው በድጋሚ አሳሰቡ።

የጋራ መኖሪያ ቤት ይደርሰናል ብለው እየቆጠቡ ያሉ ወገኖች አለን ስላሏቸው ጥያቄዎች ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ማሳወቃችን አይዘነጋም።

" ዛሬም ድረስ ግልፅ የሆነ ማብራሪያ የሚሰጠን አጥተናል " ያሉት ነዋሪዎቹ " ከልጆቻችን ምግብ ቀንሰን፣ በቤት ክራይ እየተሰቃየንና እየተማረርን ላለፉት 9 ዓመታት ቆጥበን ስለምን በዕጣው ልንካተት እንዳልቻልን በግልፅ ሊነገረን ይገባል " ብለዋል።

የቀጣዩ የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከመውጣቱ በፊትም መፍትሄ እንዲፈለግላቸው ጠይቀዋል።

የ2005 ዓ/ም 20/80 ለባለ 3 መኝታ ቆጣቢዎቹ ፤ " #ቤቶቹ_የትገቡ ? ፣ #ተስፋ_አድርገን_ነበር#13ኛው_ዙር_ላይ_97_አልቋል_ብላችሁን_አልነበር?! ፤ #ባለ3_መኝታ_ኦዲት_ይደረግ#ፍትህ_እንሻለን! "በሚሉ እና በሌሎች ሀሽታጎች በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ በመሰባሰብ ጥያቄያቸው መልስ እንዲያገኝ ዘመቻ እያካሄዱ መሆኑን ገልፀዋል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/72439?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/72244?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/72384?single
https://t.iss.one/tikvahethiopia/72271

@tikvahethiopia