TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " 4 ሚሊዮን ብር ለማስለቀቂያ ከፍለናል ሰነዱ በእጄ አለ፤ ከለቀቋቸው በኃላ ድጋሜ በመያዝ 6 ሚሊዮን ብር ጠይቀዋል " - ቀጣሪ ድርጅቱ ወደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ በግል ድርጅት ተመልምለው ወደ ስፍራው በአማራ ክልል፣ በምስቅው ጎጃም ፣ ጎዛመን በኩል አቋርጠው ሲጓዙ የካቲት 18/2016 ዓ/ም " በፋኖ ታጣቂዎች " ታገቱ የተባሉ ሠራተኞች እስካሁን ከእገታ አልተለቀቁም ሲል…
#Update

" ታጋቾቹ ተለቀው በሰላም #አዲስ_አበባ ገብተዋል " - የጋርዱላ ዞን አስተዳደር

" ለማስለቀቂያ መጀመሪያ ከከፈልነው 4 ሚሊዮን ብር በተጨማሪ በእያንዳንዱ መኪና (4 መኪናዎች) 500 ሺህ ብር ከፍለናል " - ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን

" አንድም ገንዘብ አልተቀበልንም " - ፋኖ ማርሸት ፀሀይ

በአማራ ክልል ፣ ምስራቅ ጎጃም ታግተዋል የተባሉ የቀን ሰራተኞች ከእገታው ተለቀው በሰላም አዲስ አበባ መግባታቸው ተነግሯል።

የጋርዱላ ዞን አስተዳደር ፤ " በኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሐይቅ የሚያርፍበት ስፍራን ለመመንጠር ከዞኑ 246 ተመልምለው ሲጓዙ የነበሩና በአማራ ክልል የታገቱ ሠላማዊ ዜግች ተለቀዋል " ብሏል።

ታጋቾቹ ትላትን ምሽት መለቀቃቸውን ያሳወቀው የዞኑ አስተዳደር ዛሬ በሠላም ተጉዘው አዲስ አበባ መድረሳቸውን አሳውቋል።

ወደ ህዳሴው ግድብ ለደን ምንጣሮ ስራ ሲሄዱ የታገቱት 272 ሰራተኞች እንደሆኑ ገልጾ የነበረው ቀጣሪ ድርጅቱ ኒኮቲካ ኮንስትራሽን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጠው ቃል ታጋቾች መለቀቃቸውን አረጋግጧል።

የተለቀቁት ግን 271 ሰራተኞች እንደሆኑና 1 ሰው ሾልኮ መጥፋቱን ነገር ግን ከቤተሰብ ጋር መደዋወሉን አመልክቷል።

ድርጅቱ በመጀመሪያ #ለማስለቀቂያ 4 ሚሊዮን ብር ከፍሎ እንደነበር ተለቀው ሲሄዱ አማኑኤል አካባቢ ድጋሚ በሌላ የቡድኑ ክንፍ ተይዘው ለማስለቀቂያ 6 ሚሊዮን ብር መጠየቁን በኃልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር ተከፍሎ ሰራተኞቹ መለቃቃቸውን አሳውቋል።

' የአማራ ፋኖ ምስራቅ ጎጃም ቃል አቀባይ ' ፋኖ ማርሸት ፀሀይ " ' ሰራተኞች ' የተባሉት ወደ ብርሸለቆ ሲያመሩ የነበሩ ምልምል ወታደሮች ናቸው ፤ ይመሯቸው የነበሩትም ማዕረግ ያላቸው ወታደሮች ነበሩ ፤ ምርኮኞች እንጂ ታጋቾች አይደሉም፤ ቁጥራቸውም 246 ነው " ብለው ነበር።

ትላንትና በሰጡት ቃል ፤ የግለሰቦቹን መለቀቀ አረጋግጠው ፤ " የተለቀቁት 240 ናቸው። አንድም ብር አልተቀበልንም " ብለዋል።

"ልጆቹን እንዲረከበን የቀይ መስቀል ማህበረን ጠይቀን ቀርቷል ፤ ሊቀበለንም አልቻለም። እኛ ከልጆቹ ጋር ባደረግነው ስምምነት የትራንስፖርት ወጪያቸውን ብንሸፍን በቀጥታ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደሚሄዱ ስለተነጋገርን እነሱም ስላመኑበት ወደ ቤተሰቦቻቸው ሸኝተናቸዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፤ " ፋኖ ገንዘብ አይቀበልም። ገንዘብ መቀበል ብንፈልግ ኖሮ እኮ ከሁሉም እንቀበል ነበር። ከአንዱ ተቀብለን ከአንዱ የማንቀበልበት ምክንያት የለም። በስነስርዓት ለመከላከያ ስልጠና የሚመጡ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ገንዘብ ተጠይቀናል ወደ ሚል ስም ማጥፋት ገብተዋል ምክንያቱም አላማቸው ስለተስተጓጎለ " ብለዋል።

" ገንዘብ ከማንም አልጠየቅንም " የሚሉት ማርሸት " እንደውም ለተሽከርካሪ ነዳጅ ሞልተናል፣ የሹፌሮች አበል ሰጥተናል እውነቱ ይሄ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ኒኮቲካ ኮንስትራክሽን ግን ታግተው የነበሩ ሰራተኞች ለማስቅለቅ በቅድሚያ 4 ሚሊያን ብር በሶስት ሰዎች ስም የገባበት ማስረጃ በእጁ እንዳለና በቀመጠልም በእያንዳንዱ መኪና 500 ሺህ ብር በድምሩ 6 ሚሊዮን ብር መክፈሉን አሳውቋል።

የጋርዱላ ዞን እንዳሳወቀው 246 ታጋቾች ተለቀው ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል። ታጋቾቹ እንዲለቀቁ የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች፣ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ፣ የአማራ ክልል የመንግስት አካላት በየደረጃው ያሉ ኃላፊዎች የሃይማኖት ተቋማት ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ጋር በመተባበር ትልቅ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ ከጋርዱላ ዞን ኮሚኒኬሽን እንዲሁም ከቪኦኤ ሬድዮ ማግኘቱን ይገልጻል።

@tikvahethiopia