TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#MoE

" የመውጫ ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና ወስዶ መቀጠል እንዲችል የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ እየተዘጋጀ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

250 ሺ ለሚጠጉ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመጪው #ሐምሌ_ወር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እየተጠናቀቅ እንደሚገኝ በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና ብቃት ማሻሻያ ዴስክ ኃላፊ ሰይድ መሐመድ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለመስጠት ከመንግሥት እና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅርበት እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የመውጫ ፈተናውን ወስደው ማለፍ ያልቻሉ ተማሪዎች ደጋግመው መፈተን የሚችሉበት ዕድል መኖሩን ኃላፊው አመልክተዋል።

ፈተናውን በተደጋጋሚ ወስዶ ማለፍ ያልቻለ ተማሪ ከዲግሪ በታች ባሉ ደረጃዎች ምዘና ወስዶ መቀጠል እንዲችል የሚያደርግ የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ በትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በመዘጋጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።

ይሁን እንጂ ተፈታኙ ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዝግጁ ነኝ ብሎ ባሰበ ጊዜ ፈተናውን መውሰድና ማለፍ ከቻለ የዲግሪ ማረጋገጫ ማግኘት እንደሚችል ገልጸዋል።

የመውጫ ፈተናው በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ ያመለከቱት ኃላፊው፤ ለዚህ ያመች ዘንድም የሶፍትዌር ማዘጋጀትን ጨምሮ ፈተናውን በስኬት መስጠት የሚያስችሉ ሥራዎች በመሠራት ላይ ናቸው ብለዋል።

ተማሪዎች ዋናውን ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ሞዴል ፈተናዎች እንደሚወስዱ ጠቅሰዋል፡፡ 

#ኢፕድ

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።

ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።

ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።

በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።

መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች መታሰራቸው ተገለፀ። እንዚህ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት ፦ - ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ - ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ - ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የተውጣጣ ግብረ-ኃይል ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ ከቆየ በኃላ ነው ተብሏል። ተጠርጣሪዎቹ ፤ ተገልጋዮች በመደበኛ…
" ... ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " - አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ

ከሰሞኑ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ታምሩ ግንበቶ አዋልሶ ጨምሮ 42 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች ከሙስናና ሕገወጥ ተግባር ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ማዋላቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛል።

#የግል አስተያየታቸውን ካጋሩት ውስጥ የቀድሞ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ሱሌማን ደደፎ አንዱ ናቸው።

አምባሳደር ሱሌማን ፤ የተወሰደው እርምጃ የዘገየ ቢሆንም የይበል የሚያሰኝ ነው ብለዋል።

ነገር ግን ይህ ብቻውን በቂ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

" እነዚህ ሰዎች ዘርግተው የሚጠቀሙበትና በበርካታ ደላሎች የሚሠራበት ሕገወጡ የድርጅቱ #ኦንላይን_ሲስተም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ ፕሮፌሽናል በሆኑ የሙያ ተቋማት በአዲስ መልክ መልማት ይኖርበታል " ብለዋል።

አምባደሩ ፤ " ዛሬም የኢትዮጵያ ፓስፖርት በበርካታ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የባሕረ ሰላጤው ሀገራት በደላሎች ሱቆች ውስጥ በይፋ በመቸብቸብ ላይ ይገኛል  " ሲል ገልጸዋል።

" ዜጎቻችን ፓስፖርታቸውን ለማሳደስ እስከ 60,000 ብር የሚጠየቁበት፣ ከቪዛና ከፓስፓርት እድሳት እያንዳንዱ አገልግሎት ጠያቂ $100 ዶላር ላልታወቀ ግለሰብ ወይም ተቋም የሚከፍልበት አሠራር ዛሬም ስላለ በሥራ ላይ ያለው የኦንላይን ሲስተም scrap ተደርጎ በአዲስ መተካት ይኖርበታል። " ብለዋል።

ኦንላይን የቪዛ ጥያቄ አሁንም ሁለት ሦስት ጊዜ ካልተከፈለበት መልስ እንደማይሰጥ ይታወቃል ሲሉም አክለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፤ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ፤ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ብለዋል።

" ካሉን ቁልፍ የደህነት ተቋማት መካከል የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መ/ቤት ምን ዓይነት ውርደት/ውድቀት ውስጥ እንደከተተን አይተናል። " ያሉት አምባሳደሩ " ተቋሙ ብቻውን ለዚህ አልበቃም፤ የባሰም እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም፣ በየዕለቱ የምናየውና የምንሰማው ጉዳይ ስለሆነ። " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ በሕጋዊ መንገድ ለማደስ ሁለት ሚሊዮን ብር ጉቦ የሚጠየቅበት አገር ውስጥ መሆናችንን ስናስብ እጅግ በጣም እንደነግጣለን "ም ብለዋል።

" መንግሥት ብዙ ቅድሚያ የሚሰጣቸው (Priorities) ቢኖሩትም የሥልጣን ብልግናና የአስተዳደር በደሎች፣ በተለይም ሌብነት አሁን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው ጉዳዮች መካከል መሆን ይኖርባቸዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህም ኢሚግሬሽን ብቻውን እንዳልበሰበሰ ታውቆ ከክልል እስከ ፌዴራል ያሉት ሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በጥብቅ መፈተሽ አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ፊዚክስ፣
ኬሚስትሪ፣
ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣
ሒሳብ፣
ታሪክ፣
ጂኦግራፊ፣
ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

የ2016 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና መቼ ሊሰጥ ታቅዷል ?

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ከዚህ ቀደም ሰጥተው በነበረ ማብራሪያ ፤ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት ወር ላይ እንዲሰጥ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

ሚኒስትሩ ፤ የዚህ ዓመት ፈተና ድብልቅ / ሃይብሪድ መሆኑንም በወቅቱ ገልጸው ነበር።

ድብልቅ ፈተና ማለት ግማሹ #ኦንላይን (የኢንተርኔት ችግር የሌለባቸው አካባቢዎች) ፤ የኢንተርኔት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ከዚህ ቀደም ሲሰጥ በነበረበት አካሄድ #በወረቀት ለመስጠት ነው እቅዱ።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ ሰጥተውት በነበረው ማብራሪያ ትምህርት ሚኒስቴር ምንም እንኳን የመግዛት አቅም ባይኖረውም ለፈተናው የሚሆኑ #ታብሌቶችን ከመንግሥት ተቋማት ጋር በመነጋገር ለፈተናው ጊዜ በመውሰድ ፈተናውን በድብልቅ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።

የ2016 ዓ/ም ፈተና ድብልቅ በሆነ መንገድ እንዲሰጥ የሶፍትዌር ስራው መጠናቀቁንም ይፋ አድርገው ነበር።

የዘንድሮው ምዝገባ በኦንላይን እንደሚሆን ተፈታኞች በአካል ተገኝተው ፎቶ እንዲነሱ እንደሚደረግ እና በዚህ ረገድ ቁጥጥሩ ጠበቅ እያለ እንደሚሄድ ሚኒስትሩ ከወራት በፊት መግለፃቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ መዘገቡ አይዘነጋም።

#ምንጭ@tikvahuniversity (ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ)

#ድብዳቤው ፦ ከክልል የትምህርት ቢሮዎች የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ከ3500 ዶላር እስከ 10 ሺ ዶላር የሚያሸልመው ለግብርና መሻሻል የሚረዱ የቴክኖሎጂ ውድድር መጀመሩን " አዩቲ ኢትዮጵያ ቻሌንጅ " ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ሄፈር ኢንተርናሽናል የውድድሩ አዘጋጅ ባሳወቀው መሠረት፣ የውድድሩ ዓላማ የአርሶ አደሮች ምርታማነትን መጨመር የሚያስችሉ፣ ድካም የሚቀንሱ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሀሳብ ማቅረብ ነው።

ወድድሩ ሲካሄድ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ የሚወዳደሩት ከ18 - 30 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑና ተገልጿል።

የፈጠራ ሀሳባቸውን በ #ኦንላይን ማስገባት እንዳለባቸው ተመላክቷል።

የውድድሩ አሸናፊዎች በምን መልኩ ይለያሉ ?

➡️ ተወዳዳሪዎቹ ከሚያቀርቧቸው የቴክኖሎጂ ሀሳቦች 30ዎቹ በዳኞች ይመርጣሉ፣
➡️ ዳኞች በተገኙበት 30ዎቹ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ፣
➡️ ከ30ዎቹ 10 ሀሳቦችን ዳኞች ይመርጣሉ፣
➡️ 10ሩ ተወዳዳሪዎች ለ10 ቀናት ይሰለጥናሉ፣
➡️ ከስልጠናው በኋላ የመጨረሻ የ3 ተወዳዳሪዎች ሀሳብ ይመረጣል።

የሽልማት አሰጣጡ በምን መልኩ ነው ?

1ኛ ለወጣው 10 ሺህ ዶላር፣

2ኛ ለወጣው 6 ሺህ 500 ዶላር፣

3ኛ ለወጣው ሀሳብ ደግሞ 3 ሺህ 500 ዶላር የሥራ ማስጀመሪያ እና የማበረታቻ ሽልማት ይደረግላቸዋል።

ከዚህ ቀደም በተካሄዱት 2 ውድድሮች የተለያዩ የግብርና ዘርፍ ላይ ያተኮሩ አጠቃላይ 12 የፈጠራ ቴክኖሎጂዎች ተግባር ላይ መዋላቸው ተነግሯል።

ማመልከቻ ፦ https://ayute-ethiopia.et/apply-here/

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@TikvahEthiopia