የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጣቸው።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሰሪዎች ፌዴሬሽን በሚል ስያሜ የሀገሪቱ የሆቴል እና መሰል አገልግሎት ባለቤቶችን አባል አድርጎ ሲሰራ የነበረው አሁን ስያሜውን የኢትዮጵያ ሆቴል እና ቱሪዝም አሰሪዎች ፌዴሬሽን በማለት ሰይሟል።
የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ትላንት እና ዛሬ የተደረገ ሲሆን የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበትን በድጋሚ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጧዋል፡፡
ፌዴሬሽኑ አስራ አንድ የቦድር አባላትንም የመረጠ ሲሆን ፦
- ዶ/ር ፍትህ ወልደሰንበት - ፕሬዝደንት - ከሀዋሳ
- አቶ ሙሉጌታ ቢያዝን - ተም/ ፕሬዝደንት - ከባህር ዳር
- አቶ ቴዎድሮስ ደበላ - ም/ ፕሬዝደንት - ከጅማ
- አቶ ዘውዱ በላይ - ዋና ጸሀፊ - ከቢሾፍቱ ሆነው ተመርጠዋል።
ከዚህ በተጨማኢ አቶ ወርቁ ታምራት (ከባህር ዳር) ፣ አቶ ሳሙኤል ታፈሰ (ከአዲስ አበባ) ፣ አቶ አየነው ሀብቴ (አርባምንጭ)፣ አቶ አለማየሁ ድንቁ (ከሀረር)፣ ኢንጂ መሀመድ አህመድ (ከጅማ) ፣ ወ/ሮ ሂሩት ጸጋዬ (ከድሬዳዋ) የቦርድ አመራር ሆነው ተመርጠዋል።
አቶ ዩሀንስ ወልደጊዮርጊሰ (ከላሊበላ) የሂሳብ ሹም ሆነዋል።
በፌዴሬሽኑ ህገ ደንብ መሰረት ለዘርፉ ባደረጉት አስተዋጽዎ እና በፈጠሩት የሥራ ዕድል የፌዴሬሽኑ የበላይ ጠባቂ እና የክብር አባላትንም ሰይሟል።
በዚህም ፦
👉 ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ - የበላይ ጠባቂ - ከሀይሌ ሆቴሎች
👉 አቶ ጀማል አህመድ - የክብር አባል - ከሸራተን ሆቴሎች
👉 አቶ ታዲዎስ ጌታቸው - የክብር አባል ከኩሪፍቱ ሆቴሎች
👉 አቶ በላይን ክንዴ - የክብር አባል - ከኢትዮጵያ ሆቴሎች
👉 ወ/ሮ ጸደይ አስራት - የክብር አባል - ከካልዲስ ካፌ እና ሬስቶራንት
👉 አቶ ትዕዛዙ ኮሬ - ከዮድ አቢሲኒያ የባህል ማዕከል እና ሆቴሎች
👉 አቶ በቀለ ሞላን (ቤተሰቦቻቸው) - የምግዜም የክብር አባል ያደረገ ሲሆን በትላንት ውሎውም የሀገሪቱ የሆቴል እና ቱሪዝም ዘርፍ ያለውን አቅም፤ ያለበትን ተግዳራቶች እንዲሁም ያሉትን መልካም አጋጣሚዎች ከሀገር አቀፍ ደረጃ በማስጠናት የቀረብ ሲሆን የፌዴሬሽኑም የቀጣይ አምስት አመታት የሚሰራበትን ስትራቴጂክ ፕላን ቀርቦ በመንግስት ከፍተኛ ሀላፊዎች በአባላቱ እና በባለድርሻ አካላት አስገምግሞ ጉባኤው አጽድቆታል፡፡
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update
" ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ ሰልፉን እንደምናካሂደው ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን " - ሶስቱ ፓርቲዎች
ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ ፣ ትግራይ ውድብ ናፅነት ትግራይ ለመቐለ ከተማ አስተዳደር ምላሽ ሰጡ።
ፓርቲዎቹ ፤ በቀን 24 ቀን 2015 ዓ.ም በትግራይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት " ኪዳን ንሱር ቦቆስ ለውጢ " በሚል መሪ ቃል ከጳጉሜን 2 እስከ 4 /2015 ዓ.ም በመቐለ ሮማናት አደባባይ ለሚያካሂዱት ሰላማዊ ሰልፍ የከተማ አስተዳደሩ እንዲያውቀውና አስፈላጊውን ፀጥታ የማስከበር ስራ እንዲሰራ ደብዳቤ ልከው እንደነበር አስታውሰዋል።
የከተማው አስተዳደር የተላከውን ጥያቄ አስመልክቶ የላከውን ደብዳቤ ደርሷቸው በሚገባ መመርመራቸውን ገልጸዋል።
ፓርቲዎቹ በደብዳቤው ላይ እንደተገለፀው " በሰልፉ የፀጥታ ስራ ማስከበር ተፈጥሮአዊ ግዴታችሁ መሆኑ መቀበላችሁ ወስደነዋል " ብለዋል።
" ይሁን እንጂ ሰላማዊ ሰልፉ በስመ በዓልና የፀጥታ አስከባሪ ቁጥር ማነስ ' ማስፈፀም አንችልም ' ማለታችሁ ውድቅና የማንቀበለው ነው " ሲሉ አሳውቀዋል።
ፓርቲዎቹ " ሰላማዊውና ለውጢ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ እንደምናካሂደው ልናረጋግጥላችሁ " እንፈልጋለን ብለዋል።
አክለውም ፤ " በበኩላችን የበዓል ግዚያት ያላችሁት በተለምዶ ይሁን ብለን ፤ ህዝባችን የተለመደውን በዓል ማክበር ካቆመ ሦስት አመት እንደሆነው ፤ በዓል ማክበር ይቅርና በህልውና ጥያቄ ውስጥ እንደሚገኝ ፤ በማያባራ ጥፋት እንጂ ፤ እንደ የስርአቱ ተጠቃሚ አካላት ተመችቶት እንዳልሆነ እንረዳለን " ሲሉ ገልጸዋል።
በመሆኑም " የፀጥታ ስራ እንድታከናውኑና ትኩረታችሁን ደግሞ ከሰርአቱ ከሚሰነዝር ጥቃት ህዝቡ መታደግ መሆን እንዳለበት ደግመን እንገልፃለን " ብለዋል።
መረጃው የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።
Via @TikvahEthiopiaTigrigna

#Hawassa
በሀዋሳ የውርርድ / ቤቲንግ ቤቶች እየታሸጉ ነው ፤ ለምን ?
በሀዋሳ ከተማ የስፖርት ዉርርድ ወይም ቤቲንግ ቤቶች አየታሸጉ መሆኑ ተሰምቷል።
በከተማዉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መበራከታቸዉ የሚነገርላቸዉ የስፖርት ዉርርድ ቤቶች ምንም እንኳን ህጋዊ ግብር ከፋይ ሆነዉ ወደስራ ቢገቡም ከሰሞኑ በሀዋሳ ከተማ የመታሸግ እጣ እንደገጠማቸው አሳውቀዋል።
ይህን ተከትሎ ቤታቸዉ የተዘጋባቸዉን ቅሬታ አቅራቢዎችና የከተማውን የጸጥታ አካላት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሀዋሳ ቤተሰብ ሪፖርተር አነጋግሯል።
ቤታቸው ተዘግቶ ከስራ ዉጭ መሆናቸዉ አግባብ አለመሆኑንና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለዉን የንግድ ቤት መዝጋት አግባብ አለመሆኑን የገለፁት አስተያየታቸውን የገለጹልን አካላት ቤታቸው ለመዘጋቱ የቀረበላቸው ምክኒያት እርስበርስ እንደሚጋጭ ገልጸዋል።
በመጀመሪያ ቤቱን ሊዘጉ የመጡት አካላት " ስራችሁ ቁማር ነው " እንዳሏቸው የገለጹት አስተያየት ሰጭዎች ቆይቶ ላነሱት ጥያቄ ደግሞ " ጉዳዩ ከግብር ጋር የተያያዘ መሆኑንና የሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከፌዴራል ገቢዎች ጋር እያደረገ ያለዉን ንግግር ሲጨርስ ቤታችሁ ይከፈታል " መባሉን ገልጸዋል።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አስተያየታቸዉን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ በበኩላቸዉ " ጉዳዩ ከግብር ባለፈ የጸጥታ ችግርን ከመቆጣጠር " ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል።
ከማህበረሰቡ ጋር በነበራቸዉ የዉይይት መድረክ የስፖርት ውርርድ ማካሄጃ አካባቢዎች የችግሮ ቀጠና እየሆኑ መምጣታቸዉ እንደተገለጸላቸው የሚናገሩት ኢንስፔክተሩ የሰሞኑ አሰሳም ህጋዊነታቸዉን ከማረጋገጥ በዘለለ የጸጥታ ችግሩን ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን አመላክተዋል።
የቤቶቹ ህጋዊነትና የግብር ጉዳይ በፌደራልና ሲዳማ ክልል ገቢዎች ቢሮ በኩል ውይይት ተደርጎበት የታሸጉ ቤቶች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደስራ እንደሚመለሱ የፖሊስ አዛዡ መግለፃቸውን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የሀዋሳ ቤተሰብ ዘግቧል።

#STEMpower #VISA #TikvahEthiopia
ስቴም ፓወር፣ ቪዛና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመተባበር ሲያዘጋጁት የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ስቴም ፓወር (STEMpower) ፣ ቪዛ (Visa) እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ (TIKVAH-ETH) በጋራ በመሆን ሲያዘጋጁት የቆዩትና በአስር ዙር የተሰጠው የስራ ፈጠራ እና መሰረታዊ የፋይናንስ ክህሎት ስልጠና ተገባዷል።
ላለፉት ሦስት ዓመታት በአስር ዙር ሲሰጥ በነበረው በዚህ ሥልጠና በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል 16,400 ሰልጣኞች ስልጠናውን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። ይህም በዘርፉ ያለውን ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየ ነበር።
በዚህ ሥልጠና፥ 2,420 በሰልጣኞች ያሰለጠኑ ሲሆን ሥልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ከጨረሱ ሰልጣኞች ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ጀማሪ ቢዝነሶችን በራሳቸው ጀምረው ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል።
በዚህ ፕሮጀክት ከሥልጠናው ባሻገር ነፃ የቢዝነስ ማማከር እና ለፕሮቶ ታይፕ መስሪያ የሚሆን የማሽነሪ እና ጥሬ እቃ ለሰልጣኞች ሲያቀርብ ቆይቷል።
በዚህ አጋጣሚ ወጣቶችን በስፋት ተጠቃሚ ባደረገውና ለውጥ መፍጠር በቻለው በዚህ ፕሮጀክት ላይ የተሳተፉ አጋር አካላትን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሊያመሰግን ይወዳል።

#እንድታውቁት
በአዲስ አበባ ከተማ የከባድ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀሻ ፍቃድ ከጳጉሜን 6 /2015 እስከ መስከረም 15 / 2016 ዓ/ም እንደማይሰጥ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች አንዱ የከባድ ተሽከርካሪ መንቀሳቀሻ ፈቃድ ሲሆን ይህ ፍቃድ ከጳጉሜን 6 እስከ መስከረም 15 /2016 ዓ/ም ድረስ እንደማይሰጥ አሳውቋል።
ኤጀንሲው አገልግሎቱን እንደማይሰጥ ያሳወቀው ከዚህ ቀደም የነበረውን አሰራር በተሻለ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ በማሰብ መሆኑን አስረድቷል።
ተገልጋዮች ይህን አውቀው ካላስፈላጊ እንግልት እንዲድኑ ኤጀንሲው አሳስቧል።

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎቹን ጠራ።
ዩኒቨርሲቲው የ2015 የትምህርት ዘመን ተመራቂ ተማሪዎች ከመስከረም 3-6/2016 ዓ.ም ወደ ግቢ እንዲገቡ በዛሬው ዕለት ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።
የተማሪዎች የምረቃ ጊዜ መስከረም 26 / 2016 ዓ.ም መሆኑንም አሳውቋል።
ምንጭ፦ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

የሰራዊቱ ተሽከርካሪዎች ሰሌዳ እየተቀየረ መሆኑ ተነግሯል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አዲስ የተሸከርካሪ ሰሌዳ በማዘጋጀት በአገልግሎት ላይ እያዋለ መሆኑን አሳውቋል።
ሰራዊቱ ከዚህ ቀደም ሲጠቀምበት የነበረውን የተሸከርካሪ ሰሌዳ በአዲስ ሠሌዳ የቀየረ ሲሆን ከነሃሴ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሸከርካሪዎች ላይ በመለጠፍ አገልግሎት መጀመሩ ተገልጿል።
በአጭር ጊዜ ውስጥ ለሁሉም የተቋሙ ተሸከርካሪዎች አዲስ ሰሌዳ እንደሚደርስ ይፋ ሆናል።
የሰሌዳ / ታርጋ ቅያሪ የተደረገው በተለያየ ምክንያት የተቋሙ በርካታ ሰሌዳዎች ከተቋሙ እውቅና ወጪ በሌሎች እጅ በመገኘቱ ነው ተብሏል።
በመሆንም እነዚህ ከተቋሙ እውቅና ውጭ በሌሎች እጅ የገቡ ሰሌዳዎች ለህገ-ወጥ ተግባር እንዳይውሉ ለመከላከል ታሳቢ ተደርጎ ሰሌዳው መቀሩን ሚኒስቴሩ አስረድቷል።
የተቀየሩት ሰሌዳዎች የሠራዊቱን ተልዕኮ እና ግዳጅ መነሻ አድርጎ በሚሰጡት አገልግሎት መሰረት #በኮድ ተለይተው የተዘጋጁ ናቸው ተብሏል። #EPA

" የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን ይሰጣል " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ
ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን #በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች በ #ኦንላይን እንደሚሰጥ አሳውቋል።
ይህን ያሳወቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።
ሚኒስትሩ ፤ በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን አሳውቀዋል።
ለዚህም ተግባራዊነት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን ጠቁመዋል።
ፕ/ር ብርሃኑ ፤ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እንደሚሰጥ ጠቁመው የኢንተርኔት አገልግሎት ባለባቸው አካባቢዎች ፈተናው በኦንላይን እንደሚሰጥም ገልጸዋል።
በሌላ በኩል ፤ ከአዲሱ የትምህርት ስርዓት ጋር በተያያዘ በመጽሐፍት ሕትመትና ስርጭት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሰራ ነው በዋል።
በመጀመሪያና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የመጽሐፍት እጥረት ማጋጠሙን የጠቆሙት ሚኒስትሩ ፤ ችግሩ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እንዳያጋጥም ቀደም ብሎ ጨረታ በማውጣት መጽሐፍትን በወቅቱ ለማድረስ እየተሠራ ነው ብለዋል።
መጽሐፍት እስከ መስከረም ወር መጨረሻ ድረስ እንደሚቀርቡ የትምህርት ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡

#itel_Mobile
የዘመነ የካሜራ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ብሎም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የሚደገፈው አዲሱ አይቴል S23+ ሞዴል አስደናቂ በሆነ መልኩ ማንኛውንም አይነት ፎቶ በየትኛውም ጊዜ ማንሳት የሚያስችል ብቃት ያለው ድንቅ ስልክ ሲሆን የፊትለፊት 32ሜጋ ፒክስል እና ዋናው የኃላ ካሜራ 50ሜጋ ፒክስል ካሜራ ያካተተ ነው ። itel S23+ የሚያስደንቁ ፎቶዎችን በዝቅተኛ ብርሀን ውስጥም ቢሆን በጥራት እና ቀለማትን ቁልጭ አድርጎ ማንሳት የሚያስችል አቅም አለው ።
አይቴል ሞባይል
#ItelMobile #ItelEthiopia #S23+
Follow Us : Facebook Instagram