TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Kenya #USA

የጎረቤት ኬንያ ፕሬዜዳንት በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛሉ።

እ.ኤ.አ ከ2008 ወዲህ ወይም ከ16 ዓመት በኃላ ነው ዋይት ሃውስ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ መሪ በዚህ ደረጃ ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኘው።

አሜሪካን እየጎበኙ የሚገኙት ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከፍ ያለ አቀባበል እና ከፍተኛ የቀድሞና የአሁን ባለስልጣናት በተገኙበት ልዩ እራት ግብዣ እንደተደረገላቸው ታውቋል።

ከፕሬዜዳንት ጆ ባይደንና ከሌሎች ባለልሰጣናት ጋር ተገናኝተው የሁለትዮሽ ውይይት ያደረጉም ሲሆን ሁነኛ ስምምነቶችም ከአሜሪካ መንግሥት ጋር መፈራረማቸው ተሰምቷል።

ሩቶ ከቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ባራክ ኦባማ ጋርም ተገናኝነትው መክረዋል።

በሌላ በኩል ፥ ኬንያ የሀገሪቱን የጸጥታ ስራዎች እና የሰላም ማስከበር ተልእኮዎቿን ለማሳደግ 16 በአሜሪካ የተሰሩ እጅግ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ልትቀበል እንደሆነ " ሲትዝን ቲቪ " ዘግቧል።

ይህ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በዋሽንግተን ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ለኬንያ ካበረከቱት መልካም ነገሮች አንዱ ነው ተብሏል።

ሂሊኮፕተሮቹ እ.ኤ.አ ከ2024 እስከ 2025 መጨረሻ ናይሮቢ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ዋይት ሀውስ አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ ኬንያ በመስከረም ወር 150 " M1117 " የታጠቁ እጅግ ዘመናዊ የደህንነት ተሽከርካሪዎችን ትቀበላለች።

More ➡️ @thiqahEth

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#USA #kenya

የጎረቤታችን ሀገር ኬንያን ፕሬዜዳንት ዊሊያም ሩቶን ተቀብለው እያስተናገዱ ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኬንያን ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት መካከል የመጀመሪያዋ #የNATO_አባል_ያልሆነች (non-NATO) ዋና አጋር ሀገር እንደምታደርጋት ቃል መግባታቸው ተነግሯል።

@tikvahethiopia
#USA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ያለመ አዲስ እና መጠነ ሰፊ ፕሬዝዳንታዊ ትዕዛዝ ዛሬ ይፋ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።

ውሳኔው የአሜሪካ ኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት በየዕለቱ ከሚመለከቱት በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተጥገኝነት ጠያቂዎች ቁጥር በላይ አመልካቾች የሚቀርቡ ከሆነ ጥያቄያቸውን ሳይመለከቱ በቀጥታ ከአገር እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል ሥልጣን ይሰጣል።

ይህም ድንበር ላይ ያሉ ባለሥልጣናት አሜሪካ የሚገቡ #ስደተኞች ቁጥርን እንዲገድቡ እንደሚያስችላቸው ተነግሯል።

ፕሬዝዳንት ባይደን ሥልጣን ላይ በቆዩባቸው ባለፉት 4 ዓመታት ውስጥ ከ6.4 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች በሕገ ወጥ መንገድ ወደ አሜሪካ ለመግባት እንደሞከሩ ተነግሯል።

ይህም እስካሁን ከታየው ከፍተኛው ነው።

የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ፤ ባይደን አሁን ላይ በ1952 የወጣውን በአሜሪካ ጥገኝነት የማግኘት ሥርዓትን ለመገደብ የሚያስችለውን ሕግ ለመጠቀም እያሰቡ እንደሆነ ዘግበዋል።

212 (ኤፍ) በመባል የሚታወቀው ሕግ ወደ አሜሪካ የሚገቡ የውጭ ዜጎች " ለአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም አስጊ የሚሆኑ ከሆነ " ፕሬዝዳንቱ " እንዳይገቡ ማገድ "  የሚያስችለው ነው።

#BBC
#USA #Immigration

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update (ቅዳሜ ሰኔ 29/2016 ዓ/ም) ስለ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ታጋች ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ ? በታጣቂዎች ስለታገቱ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲውን ፣ የግቢው የወንጌላውያን ተማሪዎች ህብረት እና የታጋች ቤተሰብን ምን አዲስ አለ ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬም ጥያቄ አቅርቧል። የታጋች ቤተሰቦች አጋቾቹ ወደ 20 የሚሆኑ ታጋቾችን ከትላንት ጀምሮ ወደ ማያውቁትና ጫካ በበዛበት…
አሜሪካ ምን አለች ?

" ለገንዘብ ተብሎ ተማሪዎች እና ንጹሃንን ማገት ሊቆም ይገባል " - አሜሪካ

አሜሪካ አዲስ አበባ ባሉት አምባሳደሯ ኢርቪን ማሲንጋ በኩል ባወጣችው አጭር መግለጫ  ፥ " ለገንዘብ ተብሎ ተማሪ እና ንጸሃንን ማገት ሊቆም ይገባል " ብላለች።

አምባሳደር ማሲንጋ ፦

" ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተደጋጋሚ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች እየተፈጸሙ ያሉ እገታዎች የተራዘመ ግጭት ወንጀለኞችን እንዳደፋፈረ ፤ የህግ የበላይነትንም እንዳዳከመው ያሳያል።

ለገንዘብ ሲባል በተማሪዎች እና ንጹሃን ላይ የሚፈጸም እገታ ሊቆም ይገባዋል። ባሳለፍነው ሳምንት ከ100 ተማሪዎች እና መንገደኞች ለገንዘብ ሲባል ታግተዋል። "


በባለፈው ሳምንት አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆኑ ሌሎች መንገደኞችን ጨምሮ " ገብረ ጉራቻ " ላይ መታገታቸው ይታወሳል።

#USA
#Ethiopia

@tikvahethiopia
#USA

ከግድያ የተረፉት የቀድሞው ፕሬዜዳንት ትረምፕ !

የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትረምፕ ለቀጣዩ ምርጫ ፔንሰልቬኒያ፣ ባትለር ውስጥ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ እያሉ ከሕዝቡ መካከል በተተኮሰ ጥይት ደም በደም ሆነው ከመድረኩ ሲወርዱ ታይተዋል።

ትረምፕ የድንበር አቋራጮች ቁጥር ምን ያህል እንደደረሰ ለማሳየት ሲጋብዙ እና የቁጥር ማሳያ ደውል መደወል ሲጀምር ከሕዝቡ መካከል የተኩስ ድምጽ የተሰማው።

ከዚያም ትረምፕ ቀኝ እጃቸውን ወደ አንገታቸው ሲልኩ ታይተዋል።

ወዲያውኑ ፊታቸው ላይ ደም ሲወርድ ታይቷል።

ትረምፕ ተኩሱ ከተሰማበት አቅጣጫ በኩል ራሳቸውን ለመከለል ወደ ታች ሲሸሹ እና የደኅንነት ሠራተኞች በፍጥነት ወደ መድረኩ ሲሮጡ ታይተዋል።

በዚህ ሰዓትም የሕዝቡ ጩኸት ይሰማ ነበር።

ትረምፕ ቀና ብለው እጃቸውን ወደላይ ሲያነሱ በምርጫ ቅስቀሳው ላይ የነበረው ሕዝብ ጩኸት ከፍ ብሎ ተሰምቷል።

የ "ሴክሬት ሰርቪስ " የሕግ አስከባሪዎች ትራምፕ በፍጥነት ከመድረክ እንዲወርዱ አድርገዋል።

ትራምፕ የግድያ ሙከራው ከተደረገባቸው በኃላ ወደ ሆስፒታል ተወስደው እርዳታ ከተደረገላቸው በኃላ ኒው ጀርዚ ተመልሰዋል።

ያለ ምንም የሰው ድጋፍ እራሳቸው እየተራመዱ ከአውሮፕላን ሲወርዱ ታይተዋል።

" ደህና " መሆናቸውም ታውቋል።

የግድያ ሙከራውን የፈጸመው ግለሰብ በአሜሪካ ሴክሬት ሰርቪስ ደኅንነት አባላት መገደሉን ተሰምቷል።

ከተጠርጣሪው በተጨማሪ ሁለት ሰዎች በተኩስ ልውውጡ መገደላቸውን እና ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ መቁሰላቸው ተገልጿል። #VOA #CNN

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል። አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው…
#USA

በትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ የሚያሳዩ ቪድዮዎች ወጥተዋል።

የግድያ ሙከራ ያደረገው ቶማስ ማቲው ክሮክስ የተባለው የ20 ዓመት ወጣት ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ከሚደረጉበት ስፍራ ውጭ ላይ ካለ አንድ ጣራ ላይ ተኝቶ ትራምፕን ለመግደል በተደጋጋሚ ሲተኩስ ታይቷል።

ብዙ ሳይቆይ በሴክሬት ሰርቪስ የስናይፐር ተኳሾች ተመቶ ተገድሏል።

የተለያዩ የአይን እማኞች ለቴሌቪዥን ጣቢያዎች በሰጠቱ ቃል ፥ የግድያ ሙከራ ያደረገው ወጣት ጣራ ላይ ሲወጣና ከአንዱ ጣራ ወደሌላኛው ጣራ ሲሄድ በኋላም ተኝቶ ትራምፕ ላይ ሲተኩስ መመልከታቸውን ተናግረዋል።

ድርጊቱ ከመፈጸሙ በፊት ጣራ ላይ መሳሪያ የያዘ ሰው እንዳለ ለፖሊስ አባላት ጥቆማ ሰጥተው እንደነበር ጠቁመዋል።

የግድያ ሙከራው እስኪደረግ ድረስ ጥቆማቸው ለምን ችላ እንደተባለ ግራ እንዳጋባቸው ተናግረዋል።

አንዳንድ የደህንነት ባለሞያዎች ሁሉም ጣራዎች ላይ ለምን የሴክሬት ሰርቪስ ሰዎች እንዳልነበሩ እና በሰዓቱ የነበረው የደህንነት ስራው ምርመራ እንዳሚፈልግ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ " ሴክሬት ሰርቪስ " ዋነኛ ስራው የአሁን እና ቀድሞ ፕሬዜዳንቶችን ደህንነት ማስጠበቅ ነው።

በሀገሪቱ በአሁን ወይም በቀድሞ ፕሬዜዳንቶች ላይ የግድያ ሙከራ ሲደረግ የአሁኑ ከ43 ዓመታት በኋላ ነው።

ከ43 ዓመታት በፊት ሮናልድ ሬገን በተሞከረባቸው ግድያ ክፉኛ ተጎድተው ለጥቂት ነበር ከሞት ያመለጡት።

#USA
#DonaldTrump

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቪድዮ : የቀድሞ የአሜሪካ ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የግድያው ሙከራ በተደረገባቸው ወቅት እሳቸው ቅስቀሳ ከሚያደርጉበት ስፍራ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ጣሪያ ላይ የነበሩ የ " ሴክሬት ሰርቪስ " የስናይፐር ተኳሾች የግድያ ሙከራውን ባደረገው ሰው ላይ ምላሽ ሲሰጡ ታይተዋል። አንድ ተቀርጾ በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ ቪድዮ ሁለት የሴክሬት ሰርቪስ ስናይፐር ተኳሾች በፍጥነት ኢላማ አድርገው የግድያ ሙከራ ባደረገው…
#USA

የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ እጩነታቸው ትላንት ተቀብለዋል።

ከቅዳሜው የግድያ ሙከራ በኋላ ሪፐብሊካኖች ለዶናልድ ትራምፕ ጠንካራ ድጋፋቸውን ከምን ጊዜውም በላይ አሳይተዋል። 

" የሁሉም አሜሪካውያን ፕሬዝዳንት እሆናለሁ " ያሉት ዶናልድ ትራምፕ ፦

- በሀገር ውስጥ ሕገወጥ ስደተኞችን ማባረር፣

- ኢኮኖሚውን ማሳደግ

- ግብር መቀነስን በዋና ግብነት አስቀምጠዋል።


በውጪ ግንኙነታቸውም የጋዛና የዩክሬይንን ግጭት መፍትኄ ከመስጠት ጀምረው ዓለምን ካጣችው ሰላም ጋር እንደሚያስታርቋት ቃል ገብተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳሉ የዴሞክራቶች ፓርቲን በመወከል ተወዳድረው የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚደንት የነበሩት ባራክ ዖባማ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እጩ የኋይት ሐውስ ተወዳዳሪ መሆናቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ባራክ ኦባማ ሁሉ የቀድሞዋ የምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲም ሥጋታቸውን ገልጠዋል። #DW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ክብሯት እና ክብሯን የዩክሬን ፕሬዝዳንት ፑቲን ! " - ጆ ባይደን በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዴሞክራት ፓርቲያቸውን ወክለው ይወዳደራሉ ተብለው የሚጠበቁት ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን የጤናቸው ነገር አሳሳቢ ነው እየተባለ ነው። " እርጅናም ተጫጭኗቸዋል፣ በትልልቅ መድረኮች የሚነገሯቸውን ነገሮች እየሳቱ ነው ፤ ስለዚህ ምክትላቸው ይተኳቸውና ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ይፎካከሩ " የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩ የፓርቲው…
#USA

" ካማላ ሃሪስ ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ ድጋፍ እሰጣለሁ " - ባይደን

ፕሬዜዳንት ጆ ባይደም ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋ አሳውቀዋል።

ባይደን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሳቸውን ከምርጫው እንዲያገሉ ጫና ሲደረግባቸው እንደነበእ ይታወሳል።

ዛሬ ምሽት " ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ጥቅም ሲባል ራሴን ከ2024 ፕሬዝዳንተዊ የምርጫ ፉክክር አውጥቻለው " ሲሉ በይፋ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን፤ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ የዴሞክራቶች ዕጩ ሆነው በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ እንዲቀርቡ ድጋፍ ሰጥተል።

" እኔን ተክተው ካማላ ሃሪስ ለፕሬዝዳንት እንዲወዳደሩ እፈልጋለሁ " ብለዋል።

ከቀናት በፊት የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ትራምፕ የሪፐብሊካን ፓርቲ ዕጩነታቸውን በይፋ መቀበላቸው አይዘነጋም

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA " ካማላ ሃሪስ ዕጩ ሆነው እንዲቀርቡ ድጋፍ እሰጣለሁ " - ባይደን ፕሬዜዳንት ጆ ባይደም ከአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ራሳቸውን ማግለላቸውን በይፋ አሳውቀዋል። ባይደን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሳቸውን ከምርጫው እንዲያገሉ ጫና ሲደረግባቸው እንደነበእ ይታወሳል። ዛሬ ምሽት " ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ጥቅም ሲባል ራሴን ከ2024 ፕሬዝዳንተዊ የምርጫ ፉክክር አውጥቻለው " ሲሉ በይፋ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት…
#USA

ፕሬዝዳንት ባይደን ምን አሉ ?

- ዲሞክራቶች ሆይ ዕጩነቱን (የፕሬዜዳንት ምርጫ) ላለመቀበል ወስኛለሁ።

- ሙሉ በሙሉ አቅሜን በቀረችውን የፕሬዜዳንትነት ኃላፊነቴ ላይ ትኩረት አድርጌ እሰራለሁ።

- እ.ኤ.አ. በ2020 ላይ የፓርቲው ዕጩ ሆኜ ስቀርብ የመጀመሪያው ውሳኔዬ ካማላ ሃሪስን ምክትል ፕሬዝደንት አድርጎ መምረጥ ነበር እናም ውሳኔዬ እጅግ በጣም ምርጥ ነበር።

- ዛሬ ደግሞ ካማላ ሀሪስ በዚህ ዓመት የፓርቲያችን ዕጩ እንዲሆኑ ሙሉ ድጋፌን እሰጣለሁ።

- ዴሞክራቶች - አንድ ላይ ለመሰባሰብና  ትራምፕን ለማሸነፍ ጊዜው አሁን ነው።

ትራምፕ ምን አሉ ?

የሪፐብሊካኑ ዕጩ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የባይደን ከዕጩነት እራሳቸውን ማግለል በሰሙ ጊዜ ብዙም ሳይቆዩ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

°  ጆ ባይደን ሲጀምርም ለፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ብቁ አልነበሩ። ለማገልገል ብቁ አይደሉ። በጭራሽ ሆነውም አያውቁም።

° ዶክተራቸውን እና ሚዲያውን ጨምሮ በዙሪያያቸው ያሉት ሁሉ ፕሬዝዳንት የመሆን ብቃት እንደሌላቸው ያውቃሉ፣ እናም አልነበሩም።

° በፕሬዝዳንቱ ምክንያት በጣም ተሰቃይተናል። ነገር ግን ያደረሰውን ጉዳት በፍጥነት እናስተካክላለን። አሜሪካን እንደገና ታላቅ አናድርጋታለን።

° በሀገራችን ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም መጥፎው ፕሬዝዳንት ናቸው።

° ፕሬዜዳንት ጆ ባይደንን ከማሽነፍ ይልቅ ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሀሪስን ማሸነፍ በጣም ቀላል ነው።

@tikvahethiopia
#USA

አሜሪካ በአስገድዶ መድፈር ጥፋተኛ የተባለን ወንጀለኛ በመርዝ ገደለች፡፡

አሜሪካ በአስገድዶ ደፋሪዎች ላይ ከባድ ቅጣት ከሚያስተላልፉ ሀገራት መካከል አንዷ ናት፡፡

ሎራን ኮል የተባለው አሜሪካዊ የ57 ዓመት እድሜ ያለው ሲሆን በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

ይህ ወንጀለኛ የሞት ፍርድ የተላለፈበት ሲሆን በዛሬው ዕለት ታስሮ በነበረበት ፍሎሪዳ ማረሚያ ቤት ገዳይ መርዝ በመርፌ ከተወጋ በኋላ ህይወቱ አልፏል።

ግለሰቡ የገዛ እህቱን በመድፈር ወንጀል ከተመሰረተበት ክስ በተጨማሪም የፍሎሪዳ ዩንቨርሲቲ የሆነ የ18 ዓመት ወጣት ግድያም ተከሶ ጥፋተኛ ተብሏል፡፡

አሜሪካ የተያዘው 2024 ዓመት ከገባ ጊዜ ጀምሮ 13 ሰዎች ላይ የሞት ፍርድ የፈጸመች ሲሆን ይህም ሀገሪቱ የሞት ፍርድ በብዛት ከሚፈጸምባቸው የዓለማችን ሀገራት መካከል ከፍተኛዋ አድርጓታል፡፡

አሜሪካ ካሏትግዛቶች ውስጥ 23ቱ የሞት ፍርድን የሚፈጽሙ ሲሆን ቀሪዎቹ 7 ግዛቶች ደግሞ የሞት ፍርዶችን ወደ እድሜ ልክ እስር ይቀይራሉ፡፡

እንደ ዓለም አቀፉ የስነ ህዝብ ፖፑሌሽን ሪቪው ጥናት ከሆነ በዓለም ላይ ካሉ ጠቅላላ ሴቶች መካከል 35 በመቶ ያህሉ ለጾታዊ ጥቃት የተጋለጡ ናቸው፡፡

ይሁንና ጥቃቱን ከሚፈጽሙት ውስጥ 10 በመቶዎቹ ብቻ ህግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሲሰጣቸው ቀሪዎቹ በብዙ ምክንያቶች ተገቢውን ፍትህ አያገኙም፡፡

ከአሜሪካ በተጨማሪም ጥብቅ ህግ ያላቸው ሀገራት ፦
- ሳውዲ አረቢያ፣
-  ቻይና፣
- ደቡብ ኮሪያ፣
- ቸክ ሪፐብሊክ፣
- ሰሜን ኮሪያ እና ፓኪስታን ዋነኞቹ ናቸው።

መረጃውን ሮይተርስን ዋቢ በማድረግ ያጋራው አል አይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia