TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

ባህላዊ ሕክምናን ከዘመናዊ ሕክምና ጋር በማቀናጀት ለኮሮና ቫይረስ መድኃኒት ለማግኘት የምርምር ሥራ እየሠራ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የምርምር ሂደቱ ተስፋ ያለው መሆኑንም ነው የጤና ሚኒስቴር የገለጸው።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ኮቪድ-19 አየር ወለድ ወረርሽኝ አይደለም!" - WHO

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) አየር ወለድ ወረርሽኝ እንደሆነ ተደርጎ የሚገለፀው የሀሰት መረጃ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት በድጋሚ አስታውቋል።

ኮቪድ-19 ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በቫይረሱ የተጠቃ ሰው በሚስልበት፣ በሚያስነጥስበት አልያም በሚናገርበት ወቅት እንደሆነም ነው ድርጅቱ የገለፀው።

ከወረርሽኙ ራስን መከላከል የሚቻለው በሰዎች መካከል ርቀትን ቢያንስ በአንድ ሜትር በማስፋት፣ በተደጋጋሚ እጅን በሳሙና ቢያንስ ለ20 ሰከንዶች አሽቶ በመታጠብ፣ አልኮል ባላቸው ሳኒታይዘሮች እጅን በማፅዳት እና ፊትን በእጅ ባለመንካት ነው።

#etv #WHO
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ሀገር አቀፍ መረጃዎች፦

- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሥራ እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል።

- ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመግታት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በተጨማሪ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ማኔጅመንት፣ አመራር እና ሠራተኞች ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ለተመሳሳይ አላማ አበርክተዋል።

- የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14, 000 ሰራተኞቹን በጊዚያዊነት ከስራ አሰናብቷል። ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።

- መከላከያ ሰራዊት ነገ በአዲስ አበባ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ይበትናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በማርሽ ባንድ የታጀበ የማንቂያ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡

- አልማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

#DW #etv #EliasMeseret #fbc #ena
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ለምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱ የጀምዓ ሶላት እንደማይኖር የገለጹት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ምእመናን በዓሉን በየቤታቸው #እንዲያከብሩት አሳስበዋል፡፡

ምእመናን የኢድ አል-ፊጥር በዓል የተራቡትን በማጉረስ ፣ የተጠሙትን በማጠጣት በአጠቃላይ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ 62 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

በአገሪቱ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 494 ሰዎች ውስጥ 304 ሰዎች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ፣ በተለይ በልደታ እና በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች የቫይረሱ ስርጭት ይበልጥ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

ከልደታ ክ/ከተማ 104 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ፣ ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ደግሞ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 28 መድረሱ ነው የተገለጸው፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በተስፋፋባቸው ክ/ከተሞች የእንቅስቃሴ #እገዳ ሊደረግ እንደሚችል ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን ፤ ከክልሎች ደግሞ 'ከጋምቤላ ክልል' ውጪ በሁሉም ክልሎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች መኖራቸውን ዶ/ር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse #DrAbiyAhemed

በኮቪድ-19 የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት እናት ልጇን በሰላም ተገላገለች!

በኮሮና ቫይረስ ተይዛ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ኢትዮጵያዊት ነብሰ ጡር እናት በሰላም መገላገሏን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድም በሆስፒታሉ ዛሬ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ ስጦታ አበርክተዋል።

የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው እንደገለጹት በሆስፒታሉ ሕክምና ላይ የምትገኝ አንዲት ነብሰ ጡር እናት ከትናንት በስትያ ልጇን በቀዶ ህክምና በሰላም ተገላግላላች። "በአሁኑ ወቅትም ህጻኑና ወላጅ እናት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቫይረሱ ለተያዙ ሰዎች ማገገሚያነት እያገለገለ ባለው በዚሁ ሆስፒታል ዛሬ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለእመጫቷ የተለያዩ ስጦታዎችን ማበርከታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተፅእኖ መቋቋምን አስመልክቶ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰዱ ፦

- እስካሁን ያለው በቫይረሱ የተያዘ ሰው ቁጥር 2,156 ቢሆንም 17,500 ለሚሆኑ በቫይረሱ የተጠቁ ዜጎችን ለማከም የሚችል 54 የማከሚያ ተቋማት ተዘጋጅተዋል።

- የበሽታው ምልክት ለታየባቸው 30 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች እስኪ መረመሩ ድረስ ለይቶ ማቆያ ስፍራ ተዘጋጅቷል።

- ከውጭ ለሚመጡ 45 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች ለይቶ ማቆያ የሚሆን ስፍራ ተዘጋጅቷል።

- በ3 ወር ጊዜ ከ31 በላይ ላቦራቶሪ ተቋቁሟል፤ ይህ ቁጥር በሰኔ እና ሐምሌ ወር የሚጨምር ይሆናል። ሐምሌ ወር ላይ በቀን ከ14 ሺህ በላይ ሰዎችን የመመርመር አቅም ላይ ይደረሳል።

- በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የላብራቶሪ አቅም መገንባት ተችሏል ፤ ለሁሉም ክልሎችም ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ በጥሬ ገንዘብ ተመድቧል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በ2013 የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለኢቲቪ ገልጸዋል።

የቀጣዩ ዓመት ትምህርት ምዝገባ ከነገ ነሐሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት እና በግል ትምህርት ቤቶች እንደሚጀመር የገለጹት ሚኒስትሩ፣ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ምዝገባ እንዲያከናውኑ ተፈቅዷል ብለዋል።

የበሽታው ሁኔታ እየተስፈፋ ቢሆንም የትምህርት ዝግጅት እና እንቅስቃሴ መጀመር አስፈላጊ ሆኑ መገኘቱን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

ወደ መማር ማስተማር ተግባር በሚገባበት ወቅት ለተማሪዎች ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር እንደሚሠራ ገልጸው፣ ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ እና መሰል አቅርቦቶችን ከባላድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለማቅረብ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እንዳይከሰት ተማሪዎች ማስክ በማድረግ፣ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ እና እጅን በመታጠብ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉት ተማሪዎች በ2012 የትምህርት ዘመን በ2ኛ ሴሚስተር ያለፋቸውን ትምህርቶች ማካካሻ ለመስጠት መታሰቡንም ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል #etv

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ዛሬ ኢትዮጵያ ሳላመጠቀችው ሁለተኛዋ ሳተላይት ፦

• የሳተላይቷ ስም ET-Smart-RSS

• ET-Smart-RSS እንደ ETRSS-1 የመጠቀችው ከቻይና ነው።

• ሳተላይቷ ከቻይና የመጠቀችው ኢትዮጵያ ለዚህ የሚሆን መሠረተ-ልማት የሌላት በመሆኑ ነው።

• ET-Smart-RSS ሳተላይት ስትሠራ የመጀመሪያውን ዲዛይን ሠርቶ የላከው ESSI ነው።

• ET-Smart-RSS ተግባር የመሬት ምልከታ ሆኖ የምስል ጥራቷ ግን ከመጀመሪያዋ በእጅጉ የተሻለ ነው።

• ET-Smart-RSS ናኖ ሳተላይት እና የዘመኑን የረቀቀ ቴክኖሎጂ የያዘች ናት። የመጀመሪያዋ ETRSS-1 ማይክሮ ሳተላይት ናት።

• የመጀመሪያዋ እና የዛሬዋ ሳተላይት አንድ ላይ ሲጣመሩ የተሻለ የመሬት ምልከታ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል። ESSTI የሁለቱን ምስሎች በማቀናጀት ይቀበላል።

በሌላ መረጃ ፦

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ካመጠቀቻቸው የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች በተጨማሪ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ውስጥ ሌሎች ሶስት ሳተላይቶች ለማምጠቅ ዕቅድ ይዛለች።

ከእነዚህ ሶስት ሳተላይቶች መካከል አንደኛው የኮሙዩኒኬሽን እና ብሮድካስቲግን ሳተላይት ነው።

ይህ ሳተላይት የስልክ ፣ የኢንተርኔት አገልግሎትን፣ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ጨምሮ ለመገናኛ አገልግሎት የሚውል ነው።

ሌላኛው ደግሞ እስከ 0.5 ሜትር የሚሆን የምስል ጥራቱ ከፍተኛ የሆነ የመሬት ምልከታ ሳተላይት እንደሚሆን ተገልጿል።

#DrYeshrunAlemayehu
#EthiopiaSpaceScienceandTechnology
#etv

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ ዛሬ እየተመረቀ ነው። በ231 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምስ እንዳሉት ለፋብሪካው ግንባታ 231 ሚሊየን…
#Update

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በ231 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ መርቀው በይፋ ስራውን አስጀምረዋል።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናት እና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት መገኘታቸውን ከ #etv የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ፤ ምንም ያህል #ጫና ቢደረግ የህዳሴውን ግድብ እንዳሳካነው የባህር በሩም በተመሳሳይ ይሳካል አሉ። አምባሳደር ሬድዋን፤ " የህዳሴውን ግድብ ያሳካነው ተጨብጭቦልን ሳይሆን ከቅርብም ከሩቅም እየተላጋን፣ የሥጋት ከበሮ እየተደለቀ፣  ዛቻና ማስፈራሪያ በምድርም በአየርም ልምምድ እያስገመገመብን ፣ ሁሉንም ዓይነት ጫና…
#ኢትዮጵያ

" ስለ ስምምነቱ ቀድሞውኑ የሚመለከታቸው ሀገራት እና ተቋማት እውቅናው ነበራቸው ፤ ግን አላዋቂ ለመምሰል ጥረት እያደረጉ ነው " - አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሬድዋን ሁሴን ስለ ኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ የመግባቢያ ስምምነት ምን አሉ ?

" ኢትዮጵያ ከባህር በር ጋር በተያያዘ ዕድል ያላት የሚመስለው ከሰሜን በኩል ነበር።

ሁሉም ሰው ስለ ባህር በር ሲወራ ቀይ ባህር ነው፤ ስለ ባህር ሲወራ ኤርትራ ነው ፤ ስለ ባህር ከተወራ አሰብ ነው። ይሄን አሁን ለመገልበጥ የሚያችል አዲስ አቅጣጫ ነው የወሰድነው።

ኢትዮጵያ ዙሪያዋ እድሎች አሏት፣ ዙሪያዋ ያሉ እድሎችን መጠቀም የሚያስችል አቅምም አላት፤ መጋራት የሚያስችል በጎ ፍላጎትም መነሻም አላት።

በአንድ ወይ በሌላ መንገድ ኢትዮጵያ አንድ የሆነ የባህር በር ሊኖራት ይገባል በሆነ መንገድ የሚለው ብዙዎች እየገዙት የመጣ ነው።

አትጋጩ፣ ችግር አትፍጠሩ፣ በሰላማዊ መንገድ የሚመጣበትን መንገድ በትዕግስት ሂዱ ነው እንጂ የሚለው ኢትዮጵያ unfair የሆነ ነገር እየፈለገች ነው የሚል ብዙ ምልከታ የለም።

ኢትዮጵያ ፍላጎቷን፣ ያላት concern ትክክል ነው፣ የህዝብ እግደቷም ትክክል ነው፣ ኢኮኖሚዋም ትክክል ነው ፣ የቀጠናው ችግር ትክክል ነው በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ በአውንታዊነት ሚና ልጫወት ማለቷ ተገቢ ነው የሚለውን አጀንዳ ማድረግ ተችሏል።

... ይሄንን ፊርማ (ከሶማሌላንድ ጋር) እስክንፈርም ድረስ በUN ተቋማትም፣ በአንዳድን ትላልቅ ሀገሮች መረጃዎችም ፣ በእኛ Think tank በሚባሉ NGOዎችም ይሰራ የነበረው ጥናት የኢትዮጵያ መንግሥት ወይ ኤርትራን ይወራል፣ ወይ ደግሞ ሶማሌላንድን በአውዳል ግዛት በኩል ረብሻ ፈጥሮ ቀጠናውን ያተራምሳል የሚል ጥናት ነበር ሲሰራ የነበረው።

በዚህ ላይ draft ቀርቦ የቀረበው draft official ከመሆኑ በፊት የተመለሰ draft እናውቃለን። ይሄንን እነማን እንደሚሰሩት እናውቃለን፣ እሱ ውስጥ #ኢትዮጵያውያን እንዳሉበትም እናውቃለን። ስለዚህ ትላልቆቹ ሀገራት የሳቱት ነገር ፤ እኛም ባገኘናቸው ቁጥር ጦርነት አንፈልግም ውጊያ አንፈልግም ሲባል ' አይ መዋጋታችሁማ አይቀርም አናምናችሁም ' የሚባል ነው ጭቅጭቁ ከዋሽንግተን እስከ ሌሎቹ ድረስ ፤ ስለዚህ በዚህ ሊዋጉ ነው ብለው ሲገምቱ በዚህ በኩል በሰላም መጣን አልተገመትንም ግን ያልተገመትነው ለበጎ ነው።

... መንግሥት ፍላጎቱን ይፋ ካደረገበት ጊዜ ጀምሮ ለጎረቤት ሀገሮች ፣ በአጠቃላይ ለምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ከአንዴም ሁለት ጊዜ envoy ተልኳል። የማያውቁት ነገር ቢኖር ሙሳቤሂ መቼ እንደሚመጣ (ወደ አዲስ አበባ) እና እዚህ ውስጥ የሼር ጉዳይና የእውቅና ጉዳይ MoU ውስጥ እንደሚካተት አያውቁም። ስለዚህ ከሞላ ጎደል አሰብ አካባቢ የምንከራተት አድርገው ስለወሰዱ ይሄን ጉዳይ ትርጉም አልሰጡትም።

አሁን አፍጥ ሲመጣ ነው ሰው የደነገጠው እንጂ የአብዛኛው ሰው ፍርሃት #በአሰብ በኩል ችግር ትፈጥራላችሁ ፣ ስለዚህ እጃችን ላይ በቂ ችግር አለ የዩክሬን አለ የጋዛ አለ፣ ከምትጨምሩብን በሰላማዊ መንገድ አድርጉትና በሰከነ መንገድ እኛም እናግዛችኃለን የሚል ነውና የpredictability deficit የተነሳበት angle ትክክል አይመስለኝም።

ስለ ጉዳዩ ለእያንዳንዱ ለሚመለከተው መንግሥት አስረድተናል። "

#AmbassadorRedwanHussien #etv

@tikvahethiopia