TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢትዮጵያ ኢንተርኔትን መዝጋቷ በቀን 4.5 ሚሊዮን ዶላር ያሳጣታል ብሏል- ኔት ብሎክስ የተሰኘው የሀገራትን ኤንተርኔት መቋረጥ የሚከታተለው ዐለም ዐቀፍ ድርጅት፡፡ ከቅዳሜ ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የተቋረጠው ኢንተርኔት ሙሉ በሙሉ አልተለቀቀም፡፡ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የንግግር ነጻነትን የሚያበረታቱ እርምጃዎችን መውሰድ በጀመሩ ልክ በዐመቱ ኢንተርኔት ማቋረጣቸውን እንደሚያወግዙት የድርጅቱ ዋና ሃላፊ አልፕ ቶከር ለአልጀዚራ ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በሰሞኑ የባለ ሥልጣናት ግድያ በቂ መረጃ አግኝተው ሐዘናቸውን መግለጽ ሲገባቸው፣ የመረጃ ምንጮችን መዝጋት ክብራቸውን ማሳጣት ነው ሲሉም አክለዋል፡፡

Via #wazema
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ኤታማዞር ሹሙ ጀኔራል ሰዓረ መኮንን ከተገደሉ በኋላ ተጨማሪ ሃይል ወደ ቦታው ሲያመራ ከሁለት የታጠቁ ሰዎች #ተኩስ እንደተከፈተበት ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ዜና ምንጩ መረጃውን ያሰፈረው ወደ ጀኔራሉ ቤት ሁኔታውን ለመቆጣጠር ከሄዱት ጸጥታ ሃይሎች መካከል አንደኛውን ባልደረባ ጠቅሶ ነው፡፡ የጀኔራሉ አጃቢ ጀኔራሉን #እንደገደለ አንደኛው ባካባቢው ቆሞ በሚጠብቀው መኪና ተሳፍሮ አምልጧል፤ ሌላኛው በተተኮሰበት ጥይት ከቆሰለ በኋላ በራሱ አንገት ላይ ተኩሶ ራሱን ለማጥፋት ቢሞክርም በጸጥታ ሃይሎች ቁጥጥር ስር ውሏል-ብሏል ዘገባው አክሎ፡፡

Via #wazema
🗞ሰኔ 20/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትናንቱ የሊቢያው አየር ጥቃት ከሞቱት ስደተኞች መካከል አንዷ ከሱማሌ ክልል የሄደች #ኢትዮጵያዊት ሱማሌ መሆኗን የሐርጌሳው ዜና ምንጭ ሆርን ዲፕሎማት ዘግቧል፡፡ ስደተኛዋ ለህልፈት የተዳረገችው በድብደባው ሳቢያ የግምብ ፍርስራሽ ተጭኗት መሆኑን አስከሬን የሚለዩ አካላት ገልጸዋል ተብሏል፡፡ በጥቃቱ እስካሁን 53 ስደተኞች እንደሞቱ ተረጋግጧል፡፡

Via #wazema
🗞ቀን ሰኔ 28/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ ኤሊያስ የታሰረው ቅዳሜ ማታ እንደሆነ ነው የተሰማው፤ ከታሳሪው ጋር ባለፉት 2 ቀናት የተያዙ 14 ተጠርጣሪዎችን ፖሊስ ዛሬ ጧት ፍርድ ቤት ባቀረባቸው ጊዜ #በሽብር ወንጀል እንደሚከሳቸው መግለጡን አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል፡፡ ችሎቱ ለሐምሌ 29 ቀጥሯል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ከባለ ሥልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ ነው፡፡

Via #አዲስ_ስታንዳርድ/#wazema/
🗞ቀን ሃምሌ 1/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ቦይንግ ኩባንያ በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ በደረሱት አውሮፕላን አደጋዎች ሕይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች 100 ሚሊዮን ዶላር ካሳ መድቤያለሁ ቢልም ባለ ጉዳዮቹ ግን ስለ ካሳው የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል፡፡ ቦይንግ እነማንን ለካሳው እንደሚመርጥም አልታወቀም፡፡ ካሳይ ከፋዮቹ ከአየር መንገዶቹ ሳይሆን የአውሮፕላኑ አምራች መሆኑም ያልተለመደ ነው- ብሏል ሮይተርስ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ስለ ካሳው ምንም መረጃ የለንም ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያና ኬንያ መንግሥታትም ከቦይንግ ጋር ስለ ጉዳዩ አልተነጋገሩም፡፡ አውሮፕላኑ የተከሰከሰባቸው ሰፊ ማሳዎች ባለቤት አርሶ አደሮችም ማሳዎቻቸው እስካሁን ታጥረው ያሉ ሲሆን ካሳ ስለመፈቀዱ በይፋ የሰሙት ነገር የለም፡፡

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሜሪካ

በደቡብና ሱማሌ ክልሎች፣ በምዕራብ ኦሮሚያና የኦሮሚያ-ቤንሻንጉል አዋሳኝ ቦታዎች የጸጥታ ስጋት መኖሩን ጠቅሶ ዜጎቹ ወደተጠቀሱት ቦታዎች እንዳይጓዙ የአሜሪካ ኢምባሲ ትናንት አስጠንቅቋል፡፡ ምስራቅ ሐረርጌና ጉጅ ዞኖችም በስጋት ቀጠናነት ተካተዋል፡፡ በተለይ በሱማሌ ክልል የብጥብጥ፣ የሽብር፣ የሃይል እገታና የፈንጂ ሥጋት አለ ብሏል፡፡ በኤርትራ ድንበርም ተመሳሳይ ስጋት እንዳለ ገልጧል፡፡ የእንግሊዝና ካናዳ ኢምባሲዎችም በድረ ገጾቻቸው ተመሳሳይ የጉዞ ማስጠንቀቂያዎችን አውጥተዋል፡፡ ሱማሌ ክልል ግን መረጃው ጊዜው ያለፈበት መሆኑን ጠቅሶ ኢምባሲው ማስጠንቀቂያውን እንዲያነሳ መጠየቁን፣ የርዕሰ መስተዳድሩ የሜዲያና ኮምኒኬሽን አማካሪ ሞሐመድ ኦላድ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
📸ኤርትራ የግዳጅ ብሄራዊ #ወታደራዊ_አግልግሎት የጀመረችበትን 25ኛ ዐመት የብር እዮቤልዩ በዓል ትላንት አክብራለች፡፡ በዓሉ #በሳዋ_ወታደራዊ ማሰልጠኛ ነው በወታደራዊ ስነ ሥርዓት የተከበረው፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በክብረ በዓሉ ተገኝተው ነበር።

Via #wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
IS ፊቱን ወደኢትዮጵያ እያዞረ ነው!

በሱማሊያ የሚንቀሳቀሱ የእስላሚክ ስቴት (#አይኤስ) ታጣቂዎች ፊታቸውን ወደ ኢትዮጵያ እያዞሩ ነው - ሲል ዘግቧል እንግሊዝኛው ቪኦኤ፡፡ አይኤስ የጂሃድ መልዕክቶችን በአማርኛ ቋንቋ የማሰራጨት ዕቅድም አለው፡፡ ጂሃዲስቶቹ የሀገሪቱን ብሄር ግጭቶችና ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በመጠቀም፣ ዐላማቸውን ወደ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለማስረጽ ጥረት እደረጉ ነው- ብሏል የአፍሪካ ቀንድ ጸጥታ ተንታኙ ማት ብራይደን፡፡ ቡድኑ ከ2 ዐመት በፊት ባሰራጨው የፕሮፓጋንዳ ቪዲዮ መልዕት አንድ አማርኛ ተናጋሪ ጂሃዲስት አቅርቦ ነበር፡፡ ቡድኑ አሁን 8 ኢትዮጵያዊያን ጂሃዲስቶች እንዳሉት ይታመናል፡፡ ቡድኑ ከአልሸባብ ተደጋጋሚ ጥቃት ይደርስበታል፡፡

Via #VOA/#wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ጉባዔ ተቀምጧል፡፡ በዛሬው የጉባዔው ውሎ የመንግሥት ሃላፊዎች መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡

Via #WAZEMA

•ከሰሞኑን ከሲኖዶሱ ጋር በተገናኘ በፌስቡክ ብዙ #ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጨ ስለሆነ TIKVAH-ETH በታማኝ ሚዲያዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ብቻ የሚሰማውን መረጃ ያጋራል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሮይተርስ ምርመራ ሪፖርት :

ሮተርስ ዛሬ ይፋ ባደረገው የምርመራ ሪፖርቱ የማይካድራ ጭፍጨፋን የሕወሃት ኃይሎች እንደጀመሩት ገልጿል።

አማራ ተወላጆችን የጨፈጨፉት ሻምበል ካሳዬ መኻሪ የተባለ የሕወሃት አባል ያደራጃቸው ሚሊሻዎች እንደሆኑ ከምስክሮች አንደበት መስማቱን ሮይተርስ አሳውቋል።

ሚሊሻዎች እንዲሁም የከተማዋ ፖሊስ አባላት የአማራዎችን መኖሪያ ቀበሌዎች በመክበብ በገጀራ እና ጥይት በጅምላ እንደጨፈጨፉ ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡

የአማራ ክልል ልዩ ኃይሎች እና መከላከያ ሠራዊት ወደ ከተማዋ የገቡት ከጭፍጨፋው በኋላ እንደሆነ ሪፖርቱ ይገልጿል።

የሮይተርስ ሪፖርት የአማራ ክልል ታጣቂዎች በትግራይ ተወላጆች ላይ የበቀል ርምጃ መውሰዳቸውን ጠቅሷል፡፡

የሮይተርስ የምርመራ ሪፖርት👇
https://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-conflict-expulsions/ #Wazema

@tikvahethiopia