TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

ወባ (Malaria)

" በኢትዮጵያ ተከታታይ በሆኑ ጦርነቶች፣ መፈናቀሎች እንዲሁም ሌሎች ወረርሽኞች ሳቢያ በባለፉት 2 ዓመታት ላይ ተመስርቶ  በወጣ ሪፖርት የወባ በሽታ ቁጥር ከ150%-120% ጭማሪ አሳይቷል " - #WHO Ethiopia

ወባ ተላላፊ በሽታዎች ከሚባሉት መካከል አንዱ ሲሆን የሚተላለፈውም  Plasmodium በሚባል የፕሮተዞአ ዓይነት በሴቷ አኖፊለስ የወባ ትንኝ አማካኝነት ነው።

- የወባ ትንኝ ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታ ላይ በብዛት ትራባለች።

- የወባ በሽታ አምጪ ተህዋሲያን ብዙ በመሆናቸው የሚያስከትሉት ችግር አንዱ ከአንዱ ይለያያል። ለሞት የሚዳርጉ አሉ፤ቀለል ያለ ህመም የሚያስከትሉም አሉ። በኛ ሀገር ሁለቱም ይገኛሉ። በዋናነት የከፋ ችግር የሚያስከትሉት P.falciparum እና p.vaivax ተብለው የሚጠሩት ናቸው።

▫️P.falciparum የተባለው በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገሮች ላይ በስፋትም በገዳይነትም ብዙውን ድርሻ ይወስዳል፡፡

-ለወባ በሽታ ማንኛውም ሊጋለጥ ይችላል::የወባ በሽታ ከተላላፊ በሽታዎች በገዳይነቱ ወደር የሌለው ነው።በተለይ በህፃናት፣ ነብሰ ጡር እናቶችና አረጋዊያን ላይ ሲከሰት የገዳይነት ጉልበት ያገኛል።

ምልክቶቹ ፦
▪️ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት ፣ ማንቀጥቀጥ
▪️ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
▪️ሆድ ህመም፣ማስታወክ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ
▪️ራስ ምታት፣ሰውነትን ጥምቅ ሚያደርግ ላብ

- ወባ አብዛኛውን የሰውነት ክፍል ያጠቃል። የከፋ ከሚሆንባቸው አንዱ አንጎልን ሲያጠቃ ነው። በተለምዶ የጭንቅላት ወባ (Cerebral malaria) ተብሎ ይጠራል።

- ሌላው ወባ የኩላሊት መድከምን ሲያስከትል ነው። አንዳንዴ የኩላሊት እጥበት የሚያስፈልጋቸው ደረጃም ላይ ይደርሳል።

- የልብና የሳንብ ችግር በማስከተል ለሞት የመዳረግ አቅም አለው። በተጨማሪም የደም ማነስ ያስከትላል።

* መከላከያ መንገዶች

የወባ ትንኝ ንክሻን በመከላከል፤ የመራባት አቅሟን በማስቆም፣ ቅድመ መከላከል መድሐኒት በመውሰድ መከላከል ይቻላል።

- በወባ በሽታ በብዛት ተጠቂ በሆኑ ቦታዎች ላይ የቤት ውስጥ ፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት ማድረግ እንዱሁም ደግሞ በፀረ-ወባ ትንኝ ኬሚካል የተነከረ አጎበርን በአግባቡና በትክክል መጠቀም፤ዉኃ የቋጠረ ረግረጋማ ቦታን በማፋሰስ የወባ ትንኝ እንዳትራባ ማድረግ እና ወባ በብዛት ያለበት ቦታ ልንሄድ ከሆነ ሃኪም በማማከር ቀድመን ፀረ-ወባ መድሃኒት መውሰድ ናቸው፡፡

▪️ከላይ የተባሉትን ምልክቶች ብዙ ጊዜ በሽታውን በያዘችው ትንኝ ከተነከስን ከጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት በኋላ ልናይ እንችላለን፤አንዳንድ የወባ በሽታ አይነቶች ግን እስከ አመት ድረስ ምልክት ሳያሳዩ በሰዉነታችን ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።

▫️ምልክቶቹን ካየን ግን በአፋጣኝ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ይኖርብናል።

#WHO, #EthioDemographyAndHealth

@tikvahethiopia