TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.49K videos
211 files
4.05K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጣልያን!

"በሌላው ሀገር እየሆነ ያለውን የምትመለከቱ ከሆነ በእናተ በሀገራቹ ማድረግ ያለባችሁ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው። መጀመሪያ ምን ማድረግ እንዳለብን ግራ ተጋብተን ነበር አሁን ላይ ግን ምን እየሆነ እንዳለ አውቀናል። እኛ ጋር የሆነው በእናተ ላይ ሊሆን ይችላልና ለመግታት ማድረግ ያለባችሁን ከወዲሁ ጀምሩ አትቁሙ! የአንዱ ተሞክሮ ለሌላው ትምህርት ነውና ጥንቃቄን መሰረት አድርጋችሁ ተንቀሳቀሱ" - ዶ/ር ኢማኑኤላ #EBC

የኮሮና ቫይረስን [ኮቪድ-19] መግታት ቀላል ነው፦

- የእጅዎን ንፅህና በአግባቡ ይጠብቁ
- ሰዎች በተሰበሰቡበት አይሂዱ
- ማህበራዊ ርቀትዎን ይጠብቁ
- በተጨናነቁ የትራንስፖርት አመራጮችን አይጠቀሙ
- የጤና ባለሞያዎችን ምክር ያዳምጡ
- የጤና ሚኒስቴር መምሪያዎችን ይተግብሩ
- ስለ ኮቪድ ትክክለኛ መረጃ ከWHO፣ ከጤና ሚኒስቴር እና ከህበረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብቻ ያግኙ!

ተጨማሪ ፦ 8335 / 952 ነፃ የስልክ መስመሮች ናቸው!

ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኝላችኃለን!
ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

#MoH #EPHI #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikurAnbessaSpecializedHospital

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል የሚፈልጉ ተመላላሽ ታካሚዎቹ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ባሉበት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች በተመላላሽ ታካሚዎቹ ሞባይል ስልኮች ላይ በመደወል ማማከርን ጨምሮ አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጧቸው መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጃንሜዳው አትክልት ተራ ነገ ስራ ይጀምራል!

አትክልት ተራ ሲሰጥ የነበረው የግብይት አገልግሎት ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው መሠረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ሥራው መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

በዚሁ መሠረት የአትክልት ተራ ከነገ መጋቢት 29/2012 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚዘጋ እና በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቁት ምክትል ከንቲባው ነጋዴዎች እና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የተወሰነውን ይህን ውሳኔ ማክበር እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።

#MayorofficeAA #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዕድገት በህብረት ህንፃ የ2 ወር ኪራይ ነፃ አደረገ!

የምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን የተማፅኖ ጥሪ ተከትሎ ሰባራ ባቡር አካባቢ የሚገኘው ዕድገት በህብረት ህንጻ ባለቤቶች 150 ለሚሆኑ ተከራዮቻቸው ለሁለት ወር በነፃ እንዲገለገሉበት ፈቅደውላቸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ምክትል ከንቲባው ለህንፃው ባለቤቶች ያላቸውን አክብሮት ገልፀዋል። ሌሎች አከራዮችም የእነሱን ፈለግ እንዲከተሉ ኢ/ር ታከለ ኡማ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተማሪዎች የሚያገኙትን ገቢ የወቅቱ ሁኔታ ታሳቢ ያደረገና ማህበረሰቡን በማይጎዳ የወርሃዊ ክፍያቸው በመግባባት ስሜት እንዲፈጸም በተለይም በቀጣዩቹ ሶስት ወራት የተማሪዎች ክፍያ ላይ ቢያንስ የ25 በመቶ ቅናሽ እንዲያደርጉ እንዲሁም በሌሎች አገልግሎቶች ላይ ቅነሳ ወይም ስረዛ እንዲደርጉ የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ማህበር ወስኗል - #EBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ላለፉት ሁለት ሳምንታት የኮሮና ቫይረስን በመከላከል እና መቆጣጠር ረገድ ሙያዊ እገዛ እና ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩት 12 ቻይናውያን የህክምና ዶክተሮች ስራቸውን አጠናቀቀዋል። በቀጣይ መሰል ድጋፍ ለማድረግ ወደ ጅቡቲ ያቀናሉ ተብሏል - #EBC

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#NewsAlert

በዛሬው ዕለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀጣይ የሚካሄደውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ የተቀመጡ ሦስት አንቀፆች ህገመንግስታዊ ትርጓሜ እንዲሰጣቸው በ25 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በህመንግስቱ አንቀፅ 83 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ምርጫውን መራዘም በተመለከተ ትርጉም የሚያስፈልጋቸውን አንቀፆች በአንድ ወር ወስጥ እንዲተረጉም ነው የወሰነው፡፡

የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የህገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ የውሳኔ ሀሳብ ማቅረቡን አስታውቀዋል።

የውሳኔ ሀሳቡ የህገ መንግስቱ አንቀፅ 54/1 አንቀፅ 58/3 እና አንቀፅ 93 ከህገ መንግስት አላማ እና ግቦች እንዲሁም መሰረታዊ መርሆች ጋር ለማስተሳሰር ትርጉም እንዲሰጥባቸው የሚል ህገ መንግስታዊ የመፍትሄ ሀሳብ ነው ያቀረበው።

#HPR #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በአዳማ ከተማ የኮቪድ19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በመገኘት ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱም የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስን ከመከላከል አንፃር ጠንካራ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የጤና ሚንስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እንዲሁም በተጓዳኝ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በጉብኝቱ ተካተዋል - #EBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
* TPLF

የ " ህወሓት ኃይሎች " ባለፉት ቅርብ ሳምንታት የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (USAID) የሆኑ የእርዳታ መጋዘኖችን መዝረፋቸው ተገለጸ።

የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳሬክተር ሾን ጆንስ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ፥ "የህወሓት አማጺያን በደረሱባቸው ስፍራዎች የሚገኙ የእርዳታ መጋዘኖችን ዘርፈዋል" ብለዋል።

የUSAID የኢትዮጵያ ተልዕኮ ዳይሬክተር ሾን ጆንስ ፥ "የታጠቁ ሰዎች ከዜጎች ምግብ ሰርቀዋል። ህወሓት በገባባቸውና ጦርነት በከፈተባቸው ሁሉም የአማራ አካባቢዎች መጋዘኖችን ዘርፏል፤ ተሽከርካሪዎች ዘርፏል። ውድመት ፈፅሟል" ሲሉ ተናግረዋል።

ሾን ጆንስ አክለው ፤ "በተለይ የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው የአማራ ክልል አካበቢዎች በርካታ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ስለመዝረፋቸው እና መጋዘኖቹ ባዶ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አለን" ብለዋል።

በተጨመሪ ፥ "ህወሓት ሁኔታዎችን ያለአግባብ እየተጠቀመ እንደሆነ አምናለሁ። ከተረጂዎች ላይ በኃይል እርዳታ እየነጠቀ አንደሆነ ይሰማናል፤ የምናውቀው ሃቅ ግን የህወሓት ኃይሎች በገቡባቸው አካባቢዎች ሁሉ የእርዳታ መጋዘኖቻችን ዘርፈዋል" ብለዋል።

ባለፈው ሳምንት በተባበሩት መንግሥት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ የአሜሪካ ተወካይ በተመሳሳይ "በአማራ ክልል ውስጥ የእርዳታ መጋዘን በህወሓት ኃይሎች መዘረፉን" ተናግረው እንደነበር ቢቢሲ አስነብቧል።

#EBC #BBC #AFP

@tikvahethiopia