TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrTsionFirew

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከሰሞኑን የኮሮና ቫይረስ ይዟቸው እንዳገገሙ በትዊተር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

ቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት ከሰሞኑን ዶክተር ፅዮን ፍሬውን በተለያዩ ጉዳዮች አነጋግሮ ነበር። ዶክተር ፅዮን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዩን መልዕክት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፈዋል ፦

በሽታው ስር ሳይሰድ በፊት መንግሥት እና የሚመለከታቸው ተቋሞች (ጤና ሚንስቴር እና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት) የሚያወጧቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች መከተል ይገባል።

ሰው አላግባብ መደንገጥ ሳይሆን የሚነገረውን ማድረግ አለበት፤ በማኅበራዊም ይሁን በማንኛውም ጉዳይ አትሰብሰቡ እየተባለ ሰው መሰብሰብ ካላቆመ በሽታው ይስፋፋል።

በተለይም በአሁን ወቅት “መዘናጋት ትክክል አይደለም። የምናውቀው ሰው እስኪሞት መጠበቅ የለብንም፤ ቁጥሩ 40 ሺህ ወይም 60 ሺህ እስኪደርስ መጠበቅ የለብንም። በጣም የምወደው ሰው ከዚህ በሽታ ሊሞት ይችላል ብለን እናስብ።

መዘናጋት በበሽታው የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ከፍ ከማድረጉም ባሻገር፤ ቫይረሱ ስጋት የሚሆንበትን ጊዜም እንደሚያራዝመው ያስረዳሉ።

በተጨማሪም ቤት መቀመጥና እጅ መታጠብን የመሰሉ ተግባሮች ቀላል ቢመስሉም የበርካቶችን ሕይወት ይታደጋሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

ይሄም ያልፋል!

'በኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ያስተላለፉት መልዕክት ፦

ኢትዮጵያ-ፋሲካን ዳግማዊ ትንሳኤን እና መጪ ሰርጎችን እንደ በፊት ተሰባስቦ በአንድነት መታደም ባለመቻላችን አንዳንዶቻችን በጣም እንዳዘንን እረዳለሁ።

ዛሬም ሆነ ነገ የመጣብን ክፉ ጠንቅ እስኪያልፍ ራሳችሁን ከአካላዊ መቀራረብ ስላራቃችሁም እናመሰግናለን።

አንዳንድ ወገኖች 'እረ ለፋሲካማ ተራርቀን አይሆንም!' ብላችሁ ለጠየቃችሁኝ መልሴ ቅልጥ ባለ ጦርነት ውስጥ ጥይት አየር ላይ ከወዲህ ወዲያ እየበረረ ቦምብ እዚህም እዚያ እየፈነዳ እንሰባሰብ አትሉም አይደል?

የጦርነት አውድማው ሆስፒታል ሆነ እንጂ ይሄንንም እንደዛ አስቡት ጦርነት ላይ ነን። እኛ የጤና ባለሙያዎቹ እየተፋለምን ነው። ስለዚህ በቤቶቻችሁ ሆናችሁ በዓሉን በሐሴት አክብሩ። ገበያውም ላይ እንጠንቀቅ አይዞን ይሄም ያልፋል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#DrTsionFirew

በአሜሪካ 'ኒውዮርክ ሆስፒታል' የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ ፣በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶክተር ጽዮን ፍሬው ከቀናት በፊት ከCNN ጋር ያደረጉት አጭር ቆይታ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

"በየቀኑ የሚዘገበው ቁጥር 0️⃣ወይም1️⃣ከሆነ ኮረና እየጠፋ ነው ማለት አይደለም። መጠንቀቅ ሞትን ይቀንሳል። ይሄንንም እውነታ በኒው ዮርክ እያየነው ነው። እንደ ችቦ ስንሰበሰብ እንነዳለን። ግን ነጠል እና ጠንቀቅ ስንል ብዙዎችን ከሞት እናድናለን!" - ዶ/ር ፅዮን ፍሬው

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAdeyTsegaye #DrTsionFirew

የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] በኢትዮጵያ እንዳይስፋፋ በማማከር ላይ የሚገኘው የዳያስፖራ የጤና ተመራማሪዎች አማካሪ ካውንስል የኮሮና ቫይረስን በከፍተኛ ሁኔታ በዋናው ቦታ-በኒውዮርክ ከተማ በመፋለም ላይ ለሚገኙ 2 ወጣት ሃኪሞች ምስጋና አቀረበ።

ካውንስሉ በ6ኛው ቨርቹዋል ሳምንታዊ ስብሰባው ላይ ለተገኙት ለድንገተኛ ክፍል ሃኪም ለዶ/ር ጽዮን ፍሬው (በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ህመም አገግማ ወደ ስራ የተመለሱ) እና ለጽኑ ህሙማን ክፍል ሃኪም ለዶ/ር አደይ (የሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን ልጅ) ለራሳቸው ሳይሳሱ እያደረጉ ላሉት አስተዋጽኦ ያለውን ከፍተኛ አድናቆት አቅርቧል።

ሁለቱም ወጣት ሀኪሞች በቅርቡ ታዋቂው The Wall Street Journal' ጋዜጣ ላይ ምሳሌ ስለመሆናቸው (Apr 7 & 14) ተዘግቧል።

(አምባሳደር ፍፁም አረጋ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

"ሁላችንም እንደ ግለሰብ የምንወስደው እርምጃ ትልቅ ሚና አለው። በአይኔም በተግባርም ኒው ዮርክ ውስጥ አይቼዋለሁ። ሆስፒታሎቻችንም ከወከባው ወጥተዋል። #መጠንቀቅን እንጂ መደንገጥን አንምረጥ። መሰባሰቡን እንተወው።" - ዶክተር ፅዮን ፍሬው (ከኒው ዮርክ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ስንል እንጠንቀቅ!

(በዶክተር ፅዮን ፍሬው - ከኒው ዮርክ ሆስፒታል)

በልጅነታችን ግዜ በኤች አይ ቪ ማስታወቃያውች “ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ” ይል ነበር። አሁንም በበሽታው የተጠቃው ሰው እየጨመረ ሲመጣ ከመደንገጥ #መጠንቀቅ

አንዳንዶቻችን ቢይዘኝም አይገለኝም የሚለውን አስተሳሰብ ትተን ለኛ ሳይሆን ለቤተሰቦቻችን ማሰብ አለብን። በተለይም ለእናት ለአባት እና ለአያቶቻችን የሞት መንስኤ ላለመሆን።

አሁን ደሞ በኒው ዮርክ አንዳንድ ህፃናት ልጆች ላይ የሚያመጣው የከፋ ህመም እያየን ነው። ለነሱም ስንል እንጠንቀቅ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsionFirew

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማብቃት ፥ የኮሮና ቫይረስ ማብቃት ማለት አይደለም። ይልቁንም ማስክ በማድረግ ፥ ርቀታችንን በመጠበቅ እና እጃችንን በመታጠብ ፥ የገጠመንን ተግዳሮት ለመሻገር ራሳችንን በበለጠ እንድንጠብቅ የሚያደርግ ነው።

ከበአላት እና ፌሽታ ጋር ተያይዞ ፥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ሊጨምር እንደሚችል ግልጽ ነው። ይሄ ግዴለሽነት ለጤና ባለሙያዎችን የሚያሳዝን ተግባር ነው!

ቫይረሱ መልከ-ብዙ ነው። ምን ጥሎ ምን አንስቶ እንደሚሄድ ገና አልታወቀምና ራሳችሁን ጠብቁ።

የጤና ባለሙያዎችን ልፋት ፥ የእናት የአባት ጸሎትንም ዋጋ አታሳጡ። እባካችሁ!

ዶክተር ፅዮን ፍሬው
መስከረም 19/2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia