TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኔዘርላንድ #አቶእሸቱ_ዓለሙ #ደርግ

በኔዘርላንድ የሚገኝ የይግባኝ ፍ/ቤት እ.አ.አ በ2017 ዓ.ም በጦር ወንጀለኝነት ጥፋተኛ የተባሉትን አቶ እሸቱ ዓለሙን የዕድሜ ልክ እስራት ባሳለፍነው ረቡዕ አጽንቷል።

የ67 ዓመቱ ተከሳሽ #በኢትዮጵያ በ1960 ዎቹ እና በ1970ዎቹ በነበረው ጨካኝ ኮሚኒስት ሥርዓት ወቅት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በደች የሚገኝ ፍ/ቤት የጥፋተኝነት ብይን ከ5 አመታት በፊት ሰጥቶ ነበር።

አቶ እሸቱ ዓለሙ የ2017 ፍርድ እንዲቀለበስላቸው ይግባኝ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም በሄግ የሚገኘው የይግባኝ ፍርድ ቤት ግን በ1960ዎቹ መጨረሻ እና በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ በኢትዮጵያ በኮ/ሌ መንግሥቱ ኃ/ማሪያም አመራር በተፈጸመው የቀይ ሽብር ዘመቻ ተሳታፊ ነበሩ ሲል ውሳኔውን አጽንቷል።

አቶ እሸቱ በመታመማቸው ምክንያት በይግባኝ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ላይ አልተገኙም ነበር።

የጉዳዩ ባለሞያዎች እንደሚሉት ከሆነ ወደ 150,000 የሚጠጉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ምሑራንና የፖለቲካ ሰዎች በወቅቱ የነበረው ስርዓት ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት ባደረገው ዘመቻ በጭካኔ ተገድልዋል።

አቶ ዓለሙ እአአ በ1978 በጎጃም ክፍለ ሀገር የደርግ ተወካይ የነበሩ ሲሆን በወቅቱ ደርግ በክፍለ ሀገሩ ከተቃዋሚዎቹ አንዱ ከነበረው ከኢህአፓ ጋር ሲፋለም ነበር።

ፍርድ ቤቱ እንዳለው " በተከሳሹ እውቅናና ተሳትፎ " የጦር ወንጀል በክፍለ ሃገሩ ይፈጸም ነበር።

በመቶዎች የሚቆጠሩና አብዛኞቹ ወጣት ተማሪዎች የሆኑት ሰለባዎች ካለ በቂ ምክንያት ተይዘው ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ የታሰሩ ነበር።

አንዳንዶች በከፋ ሁኔታ ሲደበደቡ አብዛኞቹ ደግሞ ካለ ፍርድ ሂደት ወደ እስር ቤት ይጋዙ ነበር። በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰለባዎች ደግሞ በሞት ተቀጥተዋል።

" የሞት ቅጣቱ በተከሳሹ አመራር ሰጪነት በጭካኔ ይፈጸም ነበር " ብሏል ፍ/ቤቱ።

አቶ ዓለሙ በ2017 የጥፋተኝነት ውሳኔ በተሰጠበት የፍርድ ሂደቱ መጀመሪያ ላይ በስሜት ተሞልተው ባደረጉት ንግግር በደርግ ላይ የቀረበውን ውንጀላ ተቀብለው ነገር ግን እርሳቸው በግላቸድ የፈፀሟቸው አለመሆናቸውን ለዳኞች ገልፀው ነበር።

አቶ ዓለሙ በደች ፍ/ቤት ጉዳያቸው ሊታይ የቻለው ከ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ጀምሮ ኔዘርላንድ ውስጥ መኖር በመጀመራቸውና በ1998 የሀገሪቱን ዜግነት በመቀበላቸው ነው።

#ASSOCIATED_PRESS | #VOA

@tikvahethiopia