TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ሀረሪ ክልል⬇️

የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እና ህገ ወጥነትን ለማስቀረት የሚሰራ ኮሚቴ ማቋቋሙን የሐረሪ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ ገልፀዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ርዕስ መስተዳር አቶ ሙራድ አብዱልሀዲ አገራችን በለውጥ ውስጥ እንዳለች ትላንት በሰጡት መግለጫ አስረድተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለውጡን የማይፈልጉ ጥቅማቸው የተነካ አካላት በእምነትና በጎሳ #ግጭት ለመፍጠር እየጣሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

በክልላችንም አልፎ አልፎ ይኸው ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልፀዋል ፡፡ ርእሰ መስተዳድሩ በመቀጠልም #የህግ የበላይነትን ለማስከበር በክልሉ ምክር ቤት የሰላም ኮሚቴ መቋቋሙን ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ የተከማቸውን #ቆሻሻ አስመልክቶም የከተማዋ ነዋሪዎች እስካሁን ላሳዩት #ትእግስት ምስጋና አቅርበው ቆሻሻው በቀጣዮቹ ሁለት
ቀናት ውስጥ ይወገዳል ብለዋል፡፡

በፀጥታው በኩል #ከቄሮ እና #ፋኖ ጋር አብሮ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ባሉበት ቦታ #ሰኞ ምክክር እንደሚካሄድ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ፦ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert ባለፈው ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ በተፈጸመ የከፍተኛ አመራሮች ግድያ በጣት የሚቆጠሩ ቡድኖች በወንጀሉ በግልፅ ተሳትፈዋል አሉ የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዳንዶች ወንጀሉን አምነው እጃቸውን ሲሰጡ ሌሎች ደግሞ በፈጸሙት ወንጀል እየተሸበሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

“አዴፓ #ከፋኖ ጋር ወይም የፋኖ ትክክለኛ አስተሳሰብ ካለው ወጣት ጋር ግብ ግብ ሊገጥም አይችልም ” ያሉት አቶ ዮሐንስ ፣ “ትግሉ ወንጀለኛን ከማያዝ አንፃር መሆኑን ህብረተሰቡ ሊረዳ ይገባል” ብለዋል፡፡

“በተደራጀ መንገድ የመንግስትን እጅ ለመጠምዘዝና የህብረተሰቡን ሰላም በማወክ በወንጀል የሚሳተፉ ካሉ የገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የማንም ፓርቲ፣ ቡድንና ድርጅት አባል ቢሆኑም ከተጠያቂነት አያማልጡም” ብለዋል፡፡

#ፋኖ በስሙ #መነገጃ ሊሆን እንደማይገባ የጠቆሙት አቶ ዮሐንስ የፋኖን ስም ይዘው በወንጀል የሚሳተፍ ግለሰብም ሆነ ቡድንን የአማራ ወጣት ሆነ ህብረተሰቡ አምርሮ ሊታገላቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ተጨማሪውን ያብቡ👇
https://telegra.ph/YB-07-08
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara

ኢሰመኮ፦

- ከየካቲት 15 እስከ 28 ቀን 2016 ዓ/ም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ደጋ ዳሞት ወረዳ (ዝቋላ ወገም፣ ፈረስ ቤት01፣ ገሳግስና ጉድባ ሰቀላ ቀበሌዎች) እና ሰከላ (አጉት፣ ጉንድልና አምቢሲ ቀበሌዎች እና ግሼ ዓባይ ከተማ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎችና በታጣቂዎች መካከል የተካሄዱ የትጥቅ ግጭቶችን ተከትሎ በሲቪል ሰዎች ላይ ሞት፣ አካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ደርሷል።

- የካቲት 20/2016 በሰሜን ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ በሚገኘው የጋፊት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የአብነት ተማሪዎች የዕለቱን ትምህርትና ጉባኤ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት አካባቢ አጠናቀው ወደ ማደሪያ ጎጇቸው ከገቡ በኋላ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች አባላት ከሌሊቱ 6፡30 ሰዓት ገደማ ላይ ወደ ቦታው ደርሰው ተማሪዎችን “ #ውጡ ” እያሉ ተኩስ በመክፈት ቀድመው በወጡ #በ11_ተማሪዎች ላይ ግድያ እንደፈጸሙ፤ ሌሎች 8 ተማሪዎችንም ደግሞ በቁጥጥር ሥር አውለው ካሳደሩ በኋላ በማግስቱ ምንም ጥፋት የለባችሁም ብለው እንደለቀቋቸው ኢሰመኮ ለመረዳት ችሏል። በወቅቱ በአቅራቢያው የሚንቀሳቀስ የታጠቀ ኃይል እንዳልነበር ምስክሮች አስረድተዋል።

- መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ/ም በኦሮሞ ብሔረሰብ ልዩ ዞን የተነሱ ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር #በኤፍራታና_ግድም እና #ቀወት ወረዳዎች በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎች ላይ በፈጸሙት ጥቃት በሲቪል ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸሙን፣ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ ንብረት መውደሙን፣ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን እና የቀንድ ከብቶችና ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች መዘረፋቸውን ኢሰመኮ ተረድቷል።

- መጋቢት 6 ቀን 2016 በአማራ ክልል፣ በባሕር ዳር ከተማ ዘንዘልማ አካባቢ አቶ ብርሃኑ ሽባባው አካል ፣ አቶ በላይ አካል እና አቶ ተሾመ ይበልጣል የተባሉ ነዋሪዎች አንዱ በሚሠራበት ሱቅ እና ሁለቱ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ " ኑ ለጥያቄ ትፈለጋላችሁ " በሚል በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላ መጋቢት 7 ቀን 2016 በባሕር ዳር ቀበሌ 14 በተለምዶ ጉዶ ባሕር አካባቢ #የፊጥኝ_እንደታሰሩ በጥይት ተገድለው ተገኝተዋል።

- በባሕር ዳር ዳግማዊ ምኒልክ ክ/ከተማ ጋጃ መስክ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ መጋቢት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት ሶላት ስግደት አከናውነው ወደ ቤታቸው እየተመለሱ የነበሩ የእስልምና ተከታይ 5 ሰዎች (4ቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ) ተገድለዋል።

- ሚያዝያ 7/2016 ከጧቱ 3፡00 ሰዓት ላይ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ አጎና ቀበሌ ላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከእስቴ ወረዳ ወደ ላይ ጋይንት ወረዳ በመጓዝ ላይ እያሉ በአካባቢው ላይ በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች (#ፋኖ ) ድንገተኛ የደፈጣ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ታጣቂዎቹ አካባቢውን ጥለው እንደሸሹ #የመንግሥት_የጸጥታ_ኃይሎች ወደ ቦታው በመግባት 7 (1 ሴትና 6 ወንዶች) ሲቪል ሰዎች ላይ ከሕግ ውጪ ግድያ ፈጽመዋል። ከ15 በላይ የሚሆኑ የቆርቆሮ ክዳን ያላቸው መኖሪያ ቤቶች እና 3 የገለባ ቤቶችና ንብረት መቃጠላቸውን እንዲሁም ከ100 በላይ የሚሆኑ የቀበሌው ነዋሪዎች ወደ ሌላ አካባቢ የተፈናቀሉ መሆኑን የቀበሌው ነዋሪዎች እና ተጎጂዎች ገልጸዋል።

- ግንቦት 4/2016 ዓ/ም ከቀኑ ከ7፡00 ሰዓት አካባቢ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ግቢ ውስጥ 2 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ አንድ ሴት መምህርትን ጨምሮ ሌሎች 9 ሲቪል ሰዎች የቆሰሉ መሆኑን ኢሰመኮ ተረድቷል።

#Amhara #EHRC

@tikvahethiopia
#StateofEmergency #EHRC

" በእስር የቆዩ ሰዎች ሊለቀቁ ይገባል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (#ኢሰመኮ) ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አተገባበር ጋር በተያያዘ በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ጠየቀ።

በአማራ ክልል በመንግሥት እና በታጣቂ ኃይሎች (በተለምዶ “#ፋኖ”) መካከል ከሚካሄደው የትጥቅ ግጭት ጋር ተያይዞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ የነበረው እና ጥር 24 ቀን 2016 ዓ/ም ለተጨማሪ 4 ወራት የተራዘመው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ አዋጅ ተፈጻሚነት አብቅቷል።

ይህንን ተከትሎ በእስር የቆዩ ሰዎችን የመልቀቅ ሂደት እንዲቀጥል ኢሰመኮ አሳስቧል።

ኮሚሽኑ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም በሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያለውን ተጽዕኖ በተመለከተ ክትትልና ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ከአዋጁ ትግበራ ጋር የተስተዋሉ ክፍተቶችንና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን የሚያመላክቱ፣ እንዲሁም ምክረ ሐሳቦችን ያካተቱ ግንቦት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ያደረገውን ጋዜጣዊ መግለጫ ጨምሮ በተለያዩ ጊዜያት በርካታ የክትትልና የምርመራ ሪፖርቶች ይፋ ሲያደርግ የቆየ መሆኑ አስታውሷል።

በዚሁ አዋጅ አተገባበር ዐውድ ውቅጥ #በእስር የቆዩ ሰዎች እንዲለቀቁ ማድረግን ጨምሮ ወደ መደበኛው የሕግ አተገባበር ሂደት መመለስ፣ እንዲሁም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የተጣሉ የእንቅስቃሴ ገደቦች እንዲነሱ እና ሌሎችም ማኅበረሰባዊ #አገልግሎቶች እንዲመለሱ ኢሰመኮ ጥሪ አቅርቧል።

#EHRC #Ethiopia #StateofEmergency

@tikvahethiopia