TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የወላይታ ሶዶ ውሎ‼️

በደቡብ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ ዙሪያ ህገወጥ የተባሉ ቤቶች #መፍረሳቸውን ተከትሎ በከተማይቱ ዛሬ ግርግር እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ። በከተማይቱ #የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርም የዓይን እማኞቹ ገልጸዋል።

አቶ ዳንኤል ዓለሙ የተባሉ የከተማይቱ ነዋሪ ለጀርመን ራድዮ እንደተናገሩት በከተማይቱ #ግርግር የተቀሰቀሰው ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ ነበር። የግርግሩ መነሻም በተለምዶ “የጨረቃ ቤቶች” ተብለው የሚጠሩ በከተማይቱ ዙሪያ ከተገነቡ መኖሪያ ቤቶች መፍረስ ጋር የተያያዘ እንደሆነም ገልጸዋል። “በጣም ግርግር ነበር። የተወሰነ ጥይት ተኩሰዋል። ሰው ሩጫ ላይ ነበር” ሲሉ የነበረውን ሁኔታ ገልጸዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የከተማይቱ ነዋሪም ከቀኑ ስድስት በኋላ ጥይት ይሰማ እንደነበር አረጋግጠዋል። የቤቶችን መፍረስ በመቃወም መንገድ ዘግተው የነበሩ ሰዎችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ መተኮሱንም የዓይን እማኙ ገልጸዋል። ግርግሩን የፈሩ ሱቆች እና ምግብ ቤቶች ተዘግተው መዋላቸውን የሚናገሩት እኚሁ ነዋሪ ወደ 10 ሰዓት ገደማ ግን ከተማይቱ “ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ተመልሳለች” ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ ህገወጥ ናቸው የተባሉ ቤቶች እየፈረሱ የሚገኙት ቀድሞ የገጠር ቀበሌዎች የነበሩ ነገር ግን ከአንድ ዓመት ወዲህ በከተማይቱ ክልል ስር በተካተቱ ሶስት አካባቢዎች እንደሆነ ነዋሪዎች ለDW አስረድተዋል። ላሬና፣ ኦፎሳሬ እና ቆንቶ በተባሉት በእነዚህ ቦታዎች የእየፈረሱ ያሉት ቤቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት የኮሚዩኒኬሽን የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ መንግስቱ ቶራ ዛሬ በከተማይቱ የተፈጠረው ግርግር “የህገ ወጥ ግንባታን ለመከላከል እየተደረገ ካለው እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ አይደለም” ሲሉ አስተባብለዋል። “ሰባት ሰዓት አካባቢ ጎማ በመቃጠሉ ሰዉ አመጽ ሊቀሰቀስ ነው በሚል ሰግቶ፣ ፈርቶ ነበር። ግን ምንም ነገር የለም። ተረጋግቷል” ሲሉ ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

የከተማይቱ የባህል፣ ቱሪዝም እና የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዛሬ በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ ካለፈው ከትላንት ጀምሮ የሶዶ ከተማ አስተዳደር እና በዙሪያ ያለው ወረዳ ህገወጥ ግንባታ የመከላከል እና የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቋል። በህገወጥ ግንባታ ተሳታፊ የሆኑ ግለሰቦች “ስራውን ለማስተጓጎልና የከተማውን ጸጥታ ለማወክ” መሞከራቸውንም ጠቁሟል። “መንገድ በመዝጋት፣ ደን የማቃጠል ሙከራ በማድረግ እና ሌሎች ችግሮችን ለመፍጠር ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል” ያላቸው ግለሰቦችም “#በቁጥጥር ስር ውለዋል” ብሏል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ...

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ ተማሪ ሞት የተጠረጠሩ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ ዓርብ ግንቦት 16/2011 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ምንጩ ያልታወቀ ጥቃት በተማሪዎች ላይ ደርሷል ብሏል።

ጥቃቱ ከተለመደው የተማሪ #ፀብና #ግርግር ለየት ያለ ባህሪ ያለው ሲሆን፥ ጩኸትና ግርግር የማይታይበት ተማሪዎችን #በአሰቃቂ ሁኔታ ጥቃት የሚያደርስ ነበርም ነው ያለው።

ጥቃት አድራሾችም ፊታቸውን በመሸፈናቸው በቀላሉ ለመለየት አስቸጋሪ ነበር ያለው ዩኒቨርሲቲው፥ ሆኖም ግን አርብ ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ ከግቢ ወጥተው ወደ ጫካ ሲገቡ በማህበረሰቡ ጥቆማ የተወሰኑትን የፀጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ሥር አውሏቸው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪዎች ስለ ችግሩ እና ስለ ቀጣይ የተማሪዎች ሰላም ተወያይተዋል። ድርጊቱን ያወገዙት ተወያዮቹ ችግር ፈጣሪዎቹን በማጋለጥ ለፀጥታ አካላት እንደሚሰጡም ቃል ገብተዋል። እስካሁን በድርጊቱ የተጠረጠሩ ተማሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ነው በውይይቱ ላይ የተገለፀው።

የአማራ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤትም የክልሉ መንግሥት እና ሕዝብ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በአንድ #ተመራቂ ተማሪ ላይ በደረሰዉ የሕይወት መጥፋት ከልብ ማዘኑን በመግለፅ ድርጊቱን አጥብቀው #እንደሚያወግዙት ገልጿል።

የክልሉ መንግሥት ከሕዝቡና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ጥቃት አድራሾችን ተከታትሎ ለሕግ እንደሚያቀርብ ማስታወቁንም ነው አብመድ የዘገበው።

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው የሀዘን መግለጫም በደብረማርቆስ ዩንቨርሲቲ ተማሪ በነበረው ወጣት ሰዓረ አብርሃ ህልፈተ ህይወት የተሰማዉ #ጥልቅ_ሃዘን ገልጿል።

ጉዳዩን በአፅንኦት እየተከታተለው እንደሚገኝ የገለፀው የክልሉ መንግስት፥ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንዲቀርቡ እና አስፈላጊዉ ፍርድ እንዲያገኙ ከሚመለከተዉ አካል ሆኖ እንደሚሰራ በመግለፅ ለሟች ቤተሰብ፣ ወዳጅና ዘመድ መፅናናትን ተመኝቷል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የወንደሰን አስክሬን ወደሀዋሳ እያመራ ነው...

ነቀምት ከተማ ተጫዋች የሆነው ወንድወሰን ዮሐንስ በትላንትናው ዕለት በነቀምቴ ከተማ በተነሳ ድንገተኛ #ግርግር በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፏል። ወንድወሰን ዮሐንስ ትውልድ እና እድገቱ #በሀዋሳ ኮረም ሰፈር አካባቢ ሲሆን በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የእድሜ እርከኖች ከተጫወተ በኋላ በስልጤ ወራቤ እና ኢትዮጵያ ውሀ ስራ (ኢኮስኮ) ሲጫወት ቆይቶ አሁን ወደሚገኝበት ነቀምት ከተማ አምርቶ እየተጫወተ የሚገኝ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ነበር። የተጫዋቹ አስከሬን ወደ ሀዋሳ እያመራ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በነገው ዕለትም በትውልድ ከተማው ሥርዓተ ቀብሩ ይፈፀማል ተብሎ ይጠበቃል።

Via SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia