TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ደኢህዴን #SEPDM መደበኛ ጉባኤዉን ሲያካሂድ የቆየቅ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ በሲዳማ ክልልነት ጉዳዩ ላይ የደረሰበትን ውጤት ይፋ ያደርጋል ተብሎ እየተጠበቀ ነዉ። ይሁን እንጂ ከመግለጫው አስቀድሞ የንቅናቄው ማዕከላዊ ኮሚቴ ሲዳማ ክልል ሆኖ እንዲመሰረት የሚያስችለውን ውሳኔ አሳልፏል የሚሉ መረጃዎች በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ ። ያም ሆኖ ግን እሰከአሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ከክልሉ ገዢ ፓርቲም ሆነ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ይፋዊ ማረጋገጫ የለም። ጉዳዩን ለማጣራት የጀርመን ራድዮ ወደ በደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ ጹህፈት ቤት ሃላፊዎች ስልክ ደውሎ ያገኘው ምላሽ ተከታዩ ነው፦ «ንቅናቄው የራሱን መግለጫ እስኪያወጣ #ጠብቁ»

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ልዩ ስብሰባ ተጠናቀቀ
==================================
የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት 10 ቀናት ከሰኔ 28 እስከ ሐምሌ 07/2011 ዓ/ም በአገራዊና ክልላዊ ወቅታዊ የፖለቲካና የጸጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም አዳዲስ ክልል ሆኖ የመደራጀት ጥያቄዎች ላይ ሲያካሄድ የነበረውን ስብስባው በስኬት አጠናቋል፡፡

ማእከላዊ ኮሚቴው አገራችን አሁን ያለችበትን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ የተጀመረው አገራዊ ለውጥ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሮ አቋም ወስዷል፡፡ ክልላዊ አደራጃጀቱን በተመለከተ ዝርዝር ሳይንሳዊ ጥናት ተደርጎ የቀረበ ሲሆን ጊዜ ወስዶ በሳል ውይይት ተካሂዶበታል፤ የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል ፡፡ በማያያዝ የክልሉን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ማድረግ፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር ላይ ጥልቅ ውይይት ተካሂዶ ጠንካራ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

ስለሆነም የደኢህዴን ማእከላዊ ኮሚቴ ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን አጠናክሮ የማስቀጠል፣ የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችንና ውጤታቸው ተጠናክረው እንዲሁም የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በጽናትና በመርህ ላይ ቆሞ በመታገል ለላቀ ስኬት እንዲበቃ ማእከላዊ ኮሚቴው በሙሉ መግባባብት ላይ በመድረስ ለቀጣይ ተልእኮም በቁርጠኝነት መዘጋጀቱን አረጋግጧል፡፡

ዝርዝር መግለጫው እንደደረሰ ይቀርባል፡፡

Via #ደኢህዴን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ስብሰባውን ረግጦ የወጣ አንድም የማዕከላዊ ኮሜቴ አባል የለም።" #ደኢህዴን #SEPDM

"...በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ስብሰባውን ረግጠው የወጡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አሉ ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆን የማዕከላዊ ኮሚቴው ጽ/ቤት ኃላፊ ጓድ ሞገስ ባልቻ ገልፀዋል።" #ደኢህዴን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የሀዋሳ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የሲዳማ እና የሀድያ ዞን ከፍተኛ ባለስልጣናትን ከኃላፊነት #ማገዱን አስታወቀ።

#ደኢህዴን ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር እና የሲዳማ ዞን አመራሮች የታገዱት ሰሞኑን በሀዋሳ ከተማና እና በሲዳማ ዞን የገጠር አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት የራሳቸው ሚና ነበራቸው በሚል ነው። የሃድያ ዞን አመራሮች በዞኑ የህዝቡን ሰላም እና ደህንነት አደጋ ላይ ከሚጥሉ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ የማገድ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።

ድርጅቱ ከስልጣን አግጃቸዋለሁ ያላቸውን የሲዳማና የሀድያ ዞን ባለስልጣናት ''የፊት አመራሮች '' ከማለት ውጪ ቁጥራቸውንም ሆነ ማንነታቸውን አልጠቀሰም። በደቡብ ክልል በከፋ እና በወላይታ ዞኖች የተስተዋሉት ተመሳሳይ ድርጊቶችም የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ናቸው ሲል ድርጅቱ በመግለጫው ጠቁሟል።

ምንጭ: የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEPDM

ደኢህዴ ዛሬ በጀመረውና ለ5 ቀናት ይዘልቃል በተባለው ስብሰባ በሃገራዊ እና ክልልላዊ ወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች እና በክልል ለመደራጀት በቀረቡ ጥያቄዎች መነሻነት የተዘጋጀው የጥናት ውጤት ላይ ይመክራል ተብሏል።

ንቅናቄውን ዛሬ ያወጣውን ሙሉ መግለጫ ታነቡት ዘንድ👇
#ደኢህዴን ----- https://telegra.ph/SEPDM-07-25
#ደኢህዴን

በአዲስ አበባ የሚገኙ የደኢህዴን ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዳማ ያካሄዱት መድረክ ተጠናቋል፡፡ አመራሮቹ በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት አስመልክቶ ይፋ በተደረገው ጥናት ላይ ተወያይተዋል፡፡

በደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ የተጠናዉ ጥናት የዜጎችን ህገ መንግስታዊ መብት የሚጥስ አለመሆኑም ተብራርቷል፡፡

የደኢህዴንና የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ፤ ደኢህዴን የህዝቦችን ጥያቄ በግምት ሳይሆን በእውቀት ላይ ተመስርቶ በጥናት ለመመለስ በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በመነሳት በሀገር ደረጃ አዲስ ልምድ ይዞ የመጣና አማራጭ ሃሳቦችን እያበረከተ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ መድረኩ ብሄራዊና ሀገራዊ ማንነትን አጣጥሞ ለመሄድ መግባባት የተፈጠረበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለሶስት ቀናት በቆየው በዚህ መድረክ ከክልል አደረጃጀት ጥያቄ በተጨማሪ በወቅታዊ፣ አገራዊ፣ ክልላዊ እና በከተማው የፖለቲካዊና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia