TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሰላም ገብተዋል!

ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ #ለSTOP_HATE_SPEECH ሀገራዊ ንቅናቄ የተጓዙት #የኢትዮጵያ_ልጆች በሰላም ወደተቋማቸው ተመልሠዋል።

በቀጣይ-የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ እና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ #የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ወደ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እና ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተያይዘው ለሰላም እና ለፍቅር ጉዞ ያደርጋሉ!!

ተዘጋጁ-

•አምቦ ዩኒቨርሲቲ
•ጅማ ዩኒቨርሲቲ
•ሀረማያ ዩንቨርስቲ
•ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ

#STOP_HATE_SPEECH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

ኢትዮጵያን አስተዳድራለሁ የሚለው የሀገሪቱ መንግስት እንዲህ ያሉ መሰል ትንንሽ የሚመስሉ ያልተገቡ ድርጊቶችን ማስቆም ካልቻለ ሀገሪቱ ወደሌላ ትርምስ ውስጥ ሊትገባ የምትችልበትን በር ይከፍታልና ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ። ከሰሞኑን በየአካባቢው የሚስተዋለው ያልተባ ድርጊት ውጤቱ ጥሩ አይመጣም። ሁኔታዎች ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ከሆኑ ሀገሪቱ የማያባራ ቀውስ ውስጥ ዳግም መግባቷ ስለማይቀር ተገቢው ትኩረት እና ጥንቃቄ ያስፈልገዋል። ህዝብ የሚከተላችሁ ሰዎችም እንደዚህ ያለው ድርጊት ተገቢ አለመሆኑን ለትውልዱ ልታስተምሩ ይገባል። ሁሉም ነገር ሰላምና ሀገር ሲኖር ነው የሚያምረው!

#የቲክቫህ_ቤተሰቦች_መልዕክት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

ይሄ ከቢሾፍቱ ወደ ዱከም የሚወስደው መንገድ በመኪና ጎማዎች፣ በትንንሽ ድንጋዮች እንደተዘጋ የሚያሳይ ፎቶ ነው። በተጨማሪ ከቢሾፍቱ ወደ አ/አ ለስራ የወጡ ሰራተኞች መንገድ ተዘግቶባቸው ተመልሰዋል። በሌላ በኩል ከሰበታ ወደ አ/አ የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል። እንዲሁም በባሌ ሮቤ ከተማ መንገድ ተዘግቷል፤ የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴዎችም አሉ።

#የቲክቫህ_ቤተሰቦች

ጉዳዩን ለማጣራት ጥረት እያደረግን ነው!
@tsegabwolde @tikvhaethiopia