TIKVAH-ETHIOPIA
ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#ተጨማሪ
የቀሲስ ዐባይ መለሰ ግድያ በስፋት ተሰማ እንጂ የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ባለችበት አካባቢ ብዙ ፈተና ይገጥማት እንደነበር አገልጋዮችና ምዕመናን ለ " ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን " ተናግረዋል።
እዛው ቤተክርስቲያን አካባቢ ስልክ የተቀሙ ፣ ጩቤ በያዙ ሰዎች ማስፈራሪያ የደረሰባቸው ፣ ሻሽ ጠምጥመው ሲሄዱ #የተመቱ መኖራቸውን ጠቁመዋል።
ያለውን ችግር የሚመለከታቸው አካላት እንዲያዩ ጠይቀዋል።
አንድ ምዕመን ፤ " ቤተክርስቲያን አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈፀምባት መሆኗን ገልፀው ተልዕኮዋን ለማስፈፀም ሰላም ያስፈልጋታል " ብለዋል።
" የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ሆኑ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ይህች ቤተክርስቲያን ከሚገባው በላይ እየተጎዳች ስለሆነ ጉዳቷን ለሚመለከተው አካል ማቅረብ የግድ ነው ፤ መስዋዕትነት መክፈልም ያስፈልጋል ምክንያቱም ቅዱስ ስጋ ክቡር ደሙን ካልተመገብን እኛ ሀገረ እግዚአብሔርን አናገኝም " ሲሉ ገልጸዋል።
መንግስት የመጀመሪያ ስራው ህግ ማስከበር መሆኑን የገለፁት እኚሁ ምእመን እንዲህ ያለ ጥቃት (በቀሲስ ዐባይ መለሰ ላይ የደረሰ) እንዳይደርስ ዜጎች ወጥተው እንዲገቡ ተገቢ የሆነ ጥበቃ ሊያደርግ ይገባዋል " ብለዋል።
" ትልቁ ችግር መንግስት ስራውን ባለመስራቱ ምክንያት ነው ይሄ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ ያለው " የሚሉት ምዕመኑ " መንግሥት ከማንኛውም ነገር በፊት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ሰላም ለማስከበር ነው ፤ ዜጎች የፈለጉበት ቦታ ሰርተው ፤ ጥረው ግረው እንዲኖሩ ዕልውናቸውንና ደህንነታቸው / ዕልውናችንን መጠበቅ ነው " ሲሉ አስገንዝበዋል።
" ይህ ባለመሆኑ ነው ሰው በወጣበት የሚቀረው እዚሁ ሰፈሩ ውስጥ ጥቃት የሚደርሰው ፤ መንግሥት እንዲያህ አይነት ድርጊት እንዳይፈፀም ስራው ባለመስራቱ ነው ችግር እየተፈጠረ ያለው ፤ መንግስት ስራውን ሊሰራ ይገባል " ብለዋል።
@tikvahethiopia