TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.2K photos
1.45K videos
208 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲሷ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ ስለ ምእራብ ወለጋው ግጭት እና አሁን ስላለው ሁኔታ ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተናገሩት፦

"እውነት ነው #ግጭት አለ። ነገር ግን ግጭቱ በመከላከያ ሰራዊታችን እይታ ውስጥ ነው። ከእኛ #ቁጥጥር ውጭ አልሆነም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በምዕራብ ኦሮሚያ በቄለም ወለጋ አካባቢ #ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ አካላትን መንግስት በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር #አይሻ_መሀመድ አስታወቁ፡፡ ሁኔታው ህዝብንና ህገ መንግስትን #አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ መንግስት #እንደማይታገሰው ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በመከላከያ ሰራዊቱ የተደረገው ሪፎርም ሰራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ በአግባቡ እንዲወጣ የሚያደርግ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ተናገሩ። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ በዛሬው እለከት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የ6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የመከላከያ ሰራዊትን ቀንን አስመልክቶ ህዝባዊ ውይይት በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው። በዚህ ውይይት የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ🔝

7ኛው የመከላከያ ሰራዊትን ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዳማ ከተማ እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ ” ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችን ጠብቀን የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እናስቀጥላለን ” በሚል መሪ ቃል ነው በሀገር አቀፍ ደረጃ በመከበር ላይ ያለው። በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተከበረ ባለው የመከላከያ ሰራዊት ቀን ላይም የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ፣ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች፣ ሚኒስትሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

via fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ #ተሿሚ ሚኒስትሮች ቃለ መሃላ ፈጽመዋል!

--- አቶ #ለማ_መገርሳ - ሀገር መከላከያ ሚኒስትር
--- አቶ #ገዱ_አንዳርጋቸው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
--- ኢንጂነር #አይሻ_መሀመድ - የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

@tsegabwolde @tikvahethiopia