TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት ከሚያዚያ 16 ጀምሮ በመላው አዲስ አበባ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅነት በ " ቴሌብር " ብቻ ተግባራዊ ይደረጋል ሲል የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። በ " ቴሌብር " ነዳጅ ስለ መቅዳት አሸከርካሪዎች ሊያውቋቸው የሚገቡ ነጥቦች ምንድናቸው ? ☞ በቅድሚያ የ " ቴሌብር "ተጠቃሚ መሆን፤ ☞ በቂ ክፍያ የቴሌብር አካውንት ውስጥ መኖሩን ማረጋገጥ፤ ☞ የ " ቴሌብር " የሚስጥር…
#ነዳጅ #አዲስአበባ

ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል አማራጭ ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ ተጠቃሚዎች ከቴሌ ብር በተጨማሪ ሌሎችም የክፍያ ሥርዓቶችን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ይህን ተከትሎ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ክፍያ በ " ቴሌ ብር " ብቻ እንደሚፈፀም እያሳወቀ ይገኛል።

ባለፉት ተከታታይ ቀናትም ቢሮው የመኪና ባለቤቶች በቀሩት ጥቂት ቀናት የነዳጅ ክፍያ በ" ቴሌ ብር ብቻ " እንደሚከፈል በመገንዘብ ከእንግልት ለመዳን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ እያሳወቀ ነው።

ቢሮው መሰል መልዕክቶችን በተረጋገጠ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎቹ ነው ለህዝብ እያሰራጨ የሚገኘው።

ለመሆኑን የነዳጅ ክፍያ ከ " ቴሌ ብር " ውጭ መፈፀም አይቻልም ?

ኤግል ላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ለዚሁ አገልግሎት የሚውል " #ነዳጅ " የተባለ የሞባይል መተግበሪያ ማቅረባቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መተግበሪያው ተገልጋዮች የነዳጅ ክፍያቸውን ከንግድ ባንክ አካውንታቸው የተርጋ ቁጥራቸውን ብቻ በመጠቀም መክፈል ያስችላል ያለ ሲሆን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የነዳጅ ክፍያው " በቴሌ ብር ብቻ " ነው የሚፈፀመው እያለ ለህዝብ እያሰራጨ ያለው መልዕክት ትክክል እንዳልሆነ አስረድቷል።

" ነዳጅ " የተሰኘው የሞባይል መተግበሪያ ከክፍያ አማራጭነት በተጨማሪ አሽከርካሪዎች አቅራቢያቸው የሚገኙትን ማደያዎች ከአቅርቦታቸው ጋር ማግኘት የሚችሉበት አማራጭም እንዳለው ድርጅቱ ገልጾልናል።

የክፍያ አማራጩ በሀገሪቱ ከሚገኙ ማደያዎች 60 በመቶ ማዳረስ መቻሉንም ጠቁሟል።

መተግበሪያው የት ይገኛል ? https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሲቢኢ ብር መተግበሪያ አማካኝነት ነዳጅ ለመቅዳት የሚያስችል አዲስ የዲጅታል አሠራር መዘርጋቱን ገልጿል።

ክፍያውም በማንኛውም ስልክ በሲቢኢ ብር አጭር ቁጥር ወይም በሞባይል መተግበሪያው መፈጸም ይቻላል ተብሏል። አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ነው የተጠቆመው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #አዲስአበባ

በአዲስ አበባ ከነገ ሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በዲጂታል የክፍያ አማራጮች ብቻ ይደረጋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኤግልላየን ሲስተም ቴክኖሎጂ ጋር በመተባበር ያቀረበውን #ነዳጅ የተባለ መተግበርያ በመጠቀም ከ900 በላይ የሚሆኑ ማደያዎች ላይ የነዳጅ ግብይት መፈፀም የሚያስችል አሰራራር አስተዋውቋል።

የነዳጅ መተግበሪያን በመጠቀም እንዴት መገበያየት ይቻላል ?

- በመጀመሪያ የነዳጅ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር ያውርዱ፤

- ሙሉ መረጃዎን በማስገባት መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ ወዲያውኑ የነዳጅ መለያ ቁጥር በ አጭር የጽሁፍ   መልዕክት ይደርስዎታል።

- በመቀጠል መተግበርያው ላይ የተሽከርካሪዎን የሰሌዳ ቁጥር በማስገባት ተሽከርካሪዎን ይመዝግቡ።

- የነዳጅ መለያ ቁጥርዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ Utility ውስጥ በመግባት Utility payment በመምረጥ በመልእክት የደረሰንን የነዳጅ ID አስገብተን Link ማድረግ ወይንም በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ።

ከዚህ በኋላ ቀጥታ ከሂሳብ አካውንትዎ ግብይት መፈጸም ብቻ !

- ነዳጅ ለመቅዳት ማደያ በሚሄዱበት ወቅት የነዳጅ ቀጂ ባለሙያው የሰሌዳ ቁጥርዎን ፣  የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን በ(ነዳጅ ቀጂው) መተግበሪያ ላይ በማስገባት ግብይቱን ያስጀምራል።

- ወዲያውኑ በሚደርስዎት የአጭር የፅሁፍ መልዕክት የሚቀዱትን የነዳጅ መጠን እና የገንዘብ መጠን ትክክል መሆኑን በማረጋገጥ የሚስጥር ቁጥሩን(OTP) ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው በመንገር ግብይቱን ያጠናቅቁ።

ነዳጅን ለየት የሚያደርገው ፦

አንድ ጊዜ ብቻ ከሂሳብ አካውንትዎ ጋር በማስተሳሰር ቀጥታ ከአካውንትዎ የነዳጅ ግብይት የሚፈጽሙበት መሆኑ!

በአቅራቢያዎ ያሉ ነዳጅ ማደያዎችን እንዲሁም ነዳጅ መኖሩን እና አለመኖሩን አረጋግጠው መሄድ የሚያስችሎትን አማራጭ ይዞ መምጣቱ!

አንዴ በመተግበሪያው ላይ ከተመዘገቡ በኋላ የስማርት ስልክ አለማስፈለጉ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ?

ፕላይ ስቶር:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

አፕስቶር : https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

አሰራሩ በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ማከናወን ይቻላል።

#ነዳጅ #CBE #ኤግልላየን
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይትን በዲጂታል የክፍያ ዘዴ ለማስፈጸም ከትናንት በስቲያ ጀምሮ መተግበር የጀመረው አሠራር፣ የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎችን እያጨናነቀ እና ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆነ እንዳለ ተገልጿል።

ተገልጋዮች ከመጠን በላይ የነዳጅ ግዥ እየፈጸሙ በመሆኑ፣ በአንዳንድ ማደያዎች የነዳጅ እጥረት እየተፈጠረ መሆኑ ታውቋል፡፡

የዲጂታል ክፍያ መተግበሪያውን ለመጠቀም የተፈጠረው ብዥታም በብዙ ማደያዎች ረዣዥም ሠልፎች እንዲታዩ ከማድረጉም በላይ ቶሎ ነዳጅ ቀድቶ ለመሄድ አዳጋች እንዲሆን አድርጎታል፡፡ 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ አሁን ያለው መጨናነቅ የተፈጠረው አገልግሎቱን ለማስጀመር በቂ ጊዜ ባለመሰጠቱና አሽከርካሪዎች አገልግሎቱ ከመጀመሩ በፊት እንዲዘጋጁ ባለመደረጉ ነው ብሏል።

" ይሄንን ሥጋታችንን ቀደም ብለን  አሳውቀናል " ያለው ማህበሩ " አሁን ብዙዎች ወደ ሲስተሙ እየገቡ ቢሆንም ከሥጋት አንጻር የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " ሲል አሳውቋል።

ድርጊቱ የነዳጅ እጥረት ሊያስከትል ይችላል ተብሎ እንደሚሠጋ የገለፀው  የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆን እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል፥ ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ሲል ማህበሩ ጠቁሟል።

በሌላ በኩል ከዚሁ የነዳጅ ግብይት ጋር በተያያዘ ኢትዮ ቴሌኮም አሠራሩን ከመተግበር አንጻር ያለውን መጨናነቅ ለማስቀረት በሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ማደያዎች #ባለሙያዎችን በማሰማራት ለተገልጋዮች ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ደኤታው አቶ ኦዴኦ ሐሰን ፥ ይህን አገልግሎት ለመተግበር #መንገራገጮች ቢኖሩም፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው አዲስ አሠራር ከግንቦት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመላ አገሪቱ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋጋጠዋል፡፡

የአገልግሎቱ መጀመር ዘመናዊ ግብይትን ከማሳለጥ ባለፈ ከነዳጅ ሥርጭት ጋር በተያያዘ ሲፈጠሩ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችንና ብክነትን ከማስቀረት አኳያ፣ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል፡፡

ይህንን የገለፁት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል የነዳጅ ግብይት መተግበሪያዎቹን ይፋ ባደረገበት ስነ ስርዓት ላይ ተገኝተው ባሰሙት ንግግር ነው።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
ፎቶ ፦ ከማህበራዊ ሚዲያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ

የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር በሁለት ቀናት 43 ሺህ  የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ የግብይት  ልውውጥ  መካሄዱን አሳወቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ / ኢብኮ በሰጠው ቃል ነው።

ሚኒስቴሩ ምን አለ ?

- በ2  ቀናት ብቻ 43 ሺህ  የኤሌክትሮኒክ የነዳጅ የግብይት  ልውውጥ ተካሂዷል። በዚህም 80 ሚሊዮን ብር የሚሆን ሽያጭ ተካሂዷል።

- አፈፃፀሙ ከቀን ወደ ቀን  መሻሻሎች እየታዩበት ነው።

- ለዝግጅት የተሰጠውን ጊዜ በአግባቡ ባለመጠቀም ከነዳጅ ማደያ ቀጂዎች  በኩል የመተግበሪያው አጠቃቀም ውስነት፣  የሰው ሀይል ቁጥር ማነስ  እና አንዳንድ አሽከርካሪዎች መተግበሪያው ሳይኖራቸው ለአገልግሎት መቅረባቸው ፤ የአገልግሎት አሰጣጡ እንዲስተጓጎልና ሰልፍ እንዲፈጠር አድርጓል። አሁን ላይ አፈፃፀሙ ከቀን ወደ ቀን መሻሻሎች  እየታዩበት  ነው።

- አንዳንድ  አሽከርካሪዎች በቂ ነዳጅ እያላቸው የክፍያ ስርዓቱ በቴክኖሎጂ  መደገፉን ተከትሎ በመደናገጥ  የመሰለፍ ሁኔታ በግንዛቤ እጥረት የተፈጠረ በመሆኑ እርምት ሊወሰድበት ይገባል።

- ነዳጅ የሚገዙት እና የሚሸጡት አካላት  ልምድ እያገኙ ሲሄዱ በአንድ ሳምንት ውስጥ ችግሩ ይቀረፋል።

- ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ በክልሎች ጭምር የነዳጅ ግብይቱ  በኤሌክትሮኒክስ መካሄድ ይጀመራል። አሁን ያጋጠሙ ችግሮች እንዳይደገሙ  ከወዲሁ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በሰፊው እየተሰራ ነው።

#የንግድ_እና_ቀጠናዊ_ትስስር_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ነዳጅ

⛽️ " አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበተለሁ " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን

⛽️ " ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ሆነ ብለው የነዳጅ ዕጥረት ያጋጠመ ለማስመሰል መሞከራቸውን በክትትል ደርሼበታለሁ አለ።

" በሀገር ውስጥ በቂ የነዳጅ አቅርቦት አለ " የሚለው ባለስልጣን መ/ቤቱ ይህ እየታወቀ የነዳጅ ዕጥረት ይከሰታል የሚሉ አዋኪ መልዕክቶች ሆነ ተብለው የሚነዙ መሆኑን ሕብረተሰቡ ይገንዘብ ሲል አሳስቧል፡፡

በቀጣይ በነዳጅ ማደያዎች ላይ የአገልግሎት አሰጣጥ መዘግየት እና ዕጥረት መፍጠርን የመሳሰሉ ችግሮች በሚፈጥሩ አካላት ላይ ክትትል በማድረግ አስተማሪ እርምጃ እወስዳለሁ ሲልም አስጠንቅቋል።

በአንዳንድ የነዳጅ ማደያዎች ላይ የሚስተዋሉ ሠልፎች ፤ ኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግብይት ተግባራዊ መደረጉን ተከትሎ በአሽከርካሪዎች በኩል ግብይት ለመፈፀም የሚያስችል አካውንት ካለመክፈት ጋር የተያያዘ እንጅ የነዳጅ ዕጥረት አይደለም ሲል አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማኅበር ፥ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጠው ቃል ፤ ከአዲሱ የዲጂታል ስርዓት ጋር በተያያዘ የተሽከርካሪዎቻቸውን የነዳጅ ታንከር #በመሙላት፣ ግዥ የሚፈጸሙ አሽከርካሪዎች ለነዳጅ እጥረት መንስዔ እየሆኑ ነው ብሏል።

አሁንም ቢሆን ወደ ዲጂታል የግብይት ሥርዓቱ የማስገባቱ ሥራ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠር የሚችለውን የነዳጅ እጥረት ለመቅረፍ ተጨማሪ የነዳጅ አቅርቦት ያስፈልጋል ብሏል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥
" አሁን የሚታየው መጨናነቅ የተወሰኑ ቀናት ሊቀጥል የሚችል ቢሆንም እንኳን መጨናነቁን ለማስቀረት የግድ መንግሥት በቂ ነዳጅ ወደ ከተማው እንዲገባ ማድረግ ይገባዋል " ያለ ሲሆን " ይህንን ካላደረገ ዕድሉን አግኝተው ነዳጅ የሚቀዱ ተገልጋዮች፣ ከፍላጎታቸው በላይ እየቀዱ የሚቀጥሉ ስለሚሆን የነዳጅ አቅርቦቱ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የተደረገው የዲጅታል የነዳጅ ግብይት ከነገ ግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ #በመላ_ሀገሪቱ ተግባራዊ መደረግ ይጀምራል።

ነገ በመላው ሀገሪቱ በሚጀምረው የዲጂታል የነዳጅ ግብይት በሁሉም ክልሎች ያሉ ነዳጅ ማደያዎች ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ ነበር።

የዲጂታል ነዳጅ ግብይት ከነገ ጀምሮ በሁሉም ተሽከርካሪዎች እና በሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ ይሆናል።

እንዴት በዲጂታል መንገድ የነዳጅ ግብይት ማካሄድ ይቻላል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ አብሯቸው ከሚሰራቸው ኢትዮ ቴሌኮም / ቴሌብር ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ኤግል ላይን ቴክኖሎጂ / ነዳጅ / በኩል የነዳጅ ግብይቱን በተመለከተ ተከታዩን መልዕክት ያስተላልፋል።

#ቴሌብር

- በቴሌ ብር ነዳጅ ለመቅዳት ወደ ነዳጅ ማደያ ስትሄዱ በቅድሚያ ፤ የቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም *127# በመደወል የቴሌብር አካውንት በቀላሉ ክፈቱ፤

- ከቴሌብር ጋር በተሳሰሩ 20 ባንኮች ከሚገኝ የባንክ አካውንታችሁ፤ በየነዳጅ ማደያዎቹ በተመደቡ የቴሌብር ወኪሎች ወይም የአገልግሎት ማዕከሎች አማካኝነት ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ማስተላለፍ ይችላሉ፤

- የነዳጅ ማደያ ሠራተኞች ስልክ ቁጥርና የሚከፍሉትን የገንዘብ መጠን ሞልተው ሲጨርሱ በስልክዎ በሚደርስዎ የማረጋገጫ መልዕክት ላይ የገንዘብ መጠኑ ትክክል መሆኑን በማየት የሚስጥር ቁጥር ማስገቢያ ሳጥኑ ውስጥ የሚስጥር ቁጥር (ፒን) በማስገባት ያረጋግጡ፡፡

በመጨረሻም ክፍያው መፈጸሙን የሚያረጋግጥ አጭር መልዕክት የሚደርስዎ ሲሆን ከቴሌብር ሱፐርአፕም ደረሰኝ ማግኘት ይችላሉ፡፡

#ነዳጅ_መተግበሪያ

በነዳጅ ከነገ ጀመሮ በመላ ሐገሪቱ በሚገኙ 1100 በላይ የነዳጅ ማድያዎች ነዳጆን መቅዳት ይችላሉ።

- አንድ ጌዜ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ  አካውንቶን Link አርገው የሚጠቀሙበት፤

- በነዳጅ STANDBY( ፈጣን) ፈጣን አግልግሎት የሚያገኙበት ነው።

ከPLAY STORE እና APP STORE አውርደው ፣ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ አካውንትዎ ጋር ያስተሳስሩ ፦

For Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.eaglelionsystems.nedaj

For iOS:
https://apps.apple.com/us/app/nedaj/id1639807926

#CBE_BIRR

በሲቢኢ ብር ነዳጅ ሲቀዱ ሁለት አማራጮች አሉ።

የመጀመሪያው ፦

ራስዎ ወደ ሲቢኢ ብር መተግበሪያዎ ‘Quick Pay’ በመግባት ‘Fuel Payment’ የሚለውን የአገልግሎት አማራጭ መርጠው አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ክፍያ ፈጽመው ነዳጅ የሚቀዱበት ነው፡፡

ሁለተኛው ፦

ለነዳጅ ቀጂ ባለሙያው ሲቢኢ ብር የተመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ߹ የሰሌዳ ቁጥርዎን እና የሚቀዱትን ነዳጅ የገንዘብ መጠን አሳውቀው በሚደርስዎት አጭር መልእክት መሠረት የገንዘብ መጠኑን ትክክለኛነት አረጋግጠው ክፍያውን በመፈፀም ነዳጅ የሚቀዱበት አማራጭ ነው።

የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ለመጫን ወይም ለማዘመን ፦

ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

ለአፕል ስልኮች ፦
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

የነዳጅ ግብይት #በመላው_ሀገሪቱ  በ " ዲጅታል " መንገድ ብቻ እንዲሆን በተላለፈው ውሳኔ መሰረት ዛሬ ግንቦት 1/2015 ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

በክልሎች የነዳጅ ጉዳይ ከተነሳ አይቀር ...

በክልል ከተሞች ላይ #ነዳጅ በተለይም ቤንዚን እንደልብ ማግኘት የማይታሰብ ነው። ነዳጅ ሲገኝም ለሰዓታት ረጃጅም ሰልፍ መሳለፍ እና መንገላታት አይቀሬ ነው።

እንደ #ሀዋሳ ያሉ ትልቅ ከተሞች ውስጥ ነዳጅ በወረፋ ብቻ ሳይሆን በሳምንት ለተወሰነ ቀን ብቻ ነው መቅዳት የሚቻለው (ለከተማው ነዋሪ - በኩፖን) ። ይህም የሚከናወነው በታርጋ " #ሙሉ እና #ጎዶሎ ቁጥር " ነው የሚከናወነው። ማደያዎችም ከተመደበላቸው ተሽከርካሪ ውጭ ማስተናገድ አይችሉም።

" እንግዳ ነኝ ፤ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ አይደለሁም " ለሚሉት ደግሞ የነዳጅ ማደያዎች የሚኖሩበትን ከተማ የነዋሪ #መታወቂያ በማየት እንደሚቀዱ ለመረዳት ተችሏል።

ከምንም በላይ የሚገርመው እጅግ በርካታ ማደያዎች ባሉበትና አሁንም እየተሰሩባት ባለው ከኢትዮጵያ ግዙፍ ከተሞች አንዷ ሀዋሳ በየዕለቱ ነዳጅ የሚሸጡት እጅግ ውስን ቁጥር ያላቸው ማደያዎች ናቸው።

ይህ በእንዲህ እያለ ግን በከተማው ነዳጅ በጥቁር ገበያ ከፍ ባለ ብር እንደጉድ ነው የሚቸበቸበው። ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በሀዋሳ ዙሪያ ጭምር ነው ይህ የሚሆነው።

የከተማው የአስተዳደር አካላት ይህንን እያወቁ መፍትሄ እየሰጡ እንዳልሆነ ከተገልጋዮች ቅሬታ ይቀርባል።

እጅግ በጣም ብዙ ተሽከርካሪዎች በሌሉበት እና በርካታ ማደያዎች ባሉበት ከተማ ነዳጅ ለማግኘት በዚህ ደረጃ መቸገር ከምን የመጣ ነው ?

ከሰሞኑን በሀዋሳ ከተማ ስላለው የነዳጅ ግብይት ጉዳይ የሲዳማ ክልል ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ በድሶ አዲሳ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

አቶ በድሶ አዲሳ  ፦

" ችግሩ አለ ፤ ይህ የሆነው በቀን ከ3 ሚሊዮን ሊትር የማይበልጥ ቤንዚን ስለሚቀርብ በአገር ደረጃ የቤንዚን እጥረት በመኖሩ ነው።

ለዚህም ሲባል ተሸከርካሪዎችን በየቀኑ በተለያዩ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች መድበን ነው እንዲቀዱ የምናደርገው።

ችግሩ ያለው ቤንዚን ላይ ነው የነዳጅ ማደያዎችም ቤንዚን ለማግኘት አንድ ወር ይጠብቃሉ።

ነዳጅ በጥቁር ገበያ ሀዋሳ ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባም ይሸጣል ፤ ለዚህ ተብሎ ከሌላ ቦታ የሚገባ ነዳጅ አለ።

እንደዚህ ዓይነት ተግባር የሚፈጽሙ የተወሰኑ ማደያዎች መኖራቸው ታውቆም እርምጃ የተወሰደባቸው አሉ።

ግብይቱ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ሲሆን ችግሩ ይቀረፋል። "

ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይ በሀዋሳ ብቻ ሳይሆን በጎረቤት ሻሸመኔ፣ በሌሎችም ከተሞች ያለ ጉዳይ ነው።

እንደ ነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን መረጃ ከሆነ " በሀገር ውስጥ በቂ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት አለ " ነገር ግን በክልል ከተሞች ያለው ነዳጅ ለማግኘት የመቸገር ጉዳይና የጥቁር ገበያው ነገር መፍትሄ የሚያሻው ነው።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
የዋጋ ንረት . . . #ኢትዮጵያ

" አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና #ጠንካራ ሆኖ ቀጥሏል " - አቶ አህመድ ሽዴ

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ረቡዕ ለህ/ተ/ም/ቤት የሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸውን እና ታጠሪ ተቋማትን የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ፥ በመጋቢት ወር አገራዊው አጠቃላይ የፍጆታ ዕቃዎች የዋጋ ግሽበት 33.7 በመቶ መድረሱን ገልጸዋል።

የምግብ ነክ ዋጋ ንረት 34.5 በመቶ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ዋጋ ንረት 32.5 በመቶ ደርሷል ሲሉ አመልክተዋል።

አሁንም የዋጋ ንረቱ ደብል ዲጂትና ጠንካራ ሆኖ መቀጠሉን ያሳያል ብለዋል።

" ይህም በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚያሳድር ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

የዋጋ ንረቱን ለመቀነስ ምን አደረጋችሁ ?

አቶ አህመድ ሽዴ ፦

- የአፈር ማዳበሪያ ዋጋ በመጨመሩ ምክንያት ዘንድሮ የብር 17 ቢሊዮን ድጎማ ተደርጓል።

የማዳበሪያ ዋጋ በተለይ በዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ያለው ዋጋ እድገትን ተከትሎ የማዳበሪያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ነው ያደገው።

ይህም አንደኛ የውጭ ምንዛሬ ጫና በከፍተኛ ደረጃ አስከትሏል በሀገር ደረጃ። ሁለተኛ ሙሉ በሙሉ በብር ተመንዝሮ ወደ ገበሬው ይተላለፍ ቢባል የገበሬውን የመግዛት አቅም ታሳቢ በማድረግ ጫናው ከፍተኛ መሆኑ በመንግስት ታምኖበት 17 ቢሊዮን ብር ከበጀት ፀድቆ ድጎማ አድርገናል።

- ለአፈር ማዳበሪያ መግዣ ለክልሎች ፣ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር 56.7 ቢሊዮን ዋስትና ተሰጥቷል።

በየክልሉ ያሉ ገበሬዎች ማዳበሪያ እንዲቀርብላቸው ለማድረግ በክልሎቹ በቀረበ ጥያቄ 56.7 ቢሊዮን ብር ዋስትና ተሰጥቷል።

- #ነዳጅ ላይ አሁንም መንግስት በከፍተኛ ደረጃ እየደጎመ ነው ያለው። ከ180 ቢሊዮን ብር በላይ ተደጉሟል ባለፉት ዓመታት ፤ ዘንድሮም ያለው ከፍተኛ ነው ፤ ደረጃ በደረጃ ከአጠቃላይ ድጎማ ወጥተን ወደ targeted subsidy የመግባት ስራው ከአንድ ዓመት በላይ እየተሰራ ነው። መሉ በሙሉ ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት እየተሰራ ያለው ስራ የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ነው።

- መንግሥት በ97 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር 43 ሚሊዮን ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ለመግዛት ውል ገብቷል። ከዚህ ውስጥ በ33.8 ሚሊዮን ዶላር 15 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ከውጭ ተገዝቶ ወደ ሀገር ገብቷል።

- የሡፍ የምግብ ዘይት አቅርቦትን ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ ነው።

- ዘይት፣ ሩዝ፣ ስኳር፣ ከውጭ ሲገቡ ሆነ በሀገር ሲመረቱ ከቀረጥ እና ታክስ ነፃ ታደርገዋል። የዋጋ ንረቱ ከዚህም ከፍ እንዳይል እያገዘ ነው።

- ለሀገር ውስጥ አምራቾች ከለላ ለመስጠት መኮሮኒ እና ፓስታ #ከተጨማሪ_እሴት_ታክስ ነፃ ታደርጓል። ይሄም የዋጋ ንረቱ እንዳይባባስ ለማድረግ ታልሞ የተሰራበት ነው።

- መሰረታዊ ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉታ እንዲገቡ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት መንግሥት ብር 11.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ሳይሰበስብ ቀርቷል። ሸቀጦች በፍራንኮ ቫሉት መግባታቸው የዋጋ ንረቱ ከዚህ በላይ እንዳይባባስ ጥሩ ሚና አለው።

... በማለት የዋጋ ንረቱን ለመቆጣጠር ወስደናቸዋል ስላሏቸው እርምጃዎች አስረድተዋል።

@tikvah_eth_BOT @tikvahethiopia
#ነዳጅ

ለመጪው የ2016 ዓ/ም ወደ አገር ለማስገባት ለታቀደው 4.3 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነዳጅ 4.4 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በ2016 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋትን ነዳጅ ለማስገባት የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ፣ " ቪቶል " የተባለው የባህሬን ኩባንያ በድጋሚ በማሸነፉ የኮንትራት ውል ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በ2016 ዓ.ም. ለማስገባት ያቀደውን ሙሉ ለሙሉ ቤንዚን፣ እንዲሁም ከጠቅላላው የነጭ ናፍጣ ግዥ 40 በመቶውን " ቪቶል " ኩባንያ እንደሚያስገባ ታውቋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ለ1 ዓመት የሚያስፈልገውን 760 ሺሕ ሜትሪክ ቶን ቤንዚንና 1.2 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ ኩባንያው ያቀርባል፡፡

" ቪቶል " ጨረታውን ያሸነፈው ከሁለት ሌሎች ኩባንያዎች ጋር ተወዳድሮ እንደሆነ ተነግሯል።

" ቪቶል " እየተጠናቀቀ ላለፈው የበጀት ዓመት በተመሳሳይ የወጣውን ጨረታ አሸንፎ ሲያቀርብ ነበር።

ለ2016 በጀት ዓመት ያስፈልጋል ተብሎ የታቀደው ነዳጅ ከ2015 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በስምንት በመቶ ብልጫ አለው፡፡

በተናጠል ሲታይ ቤንዚን ስምንት በመቶና ነጭ ናፍጣ አምስት በመቶ ጭማሪ ይኖራቸዋል፡፡ 

Via Ethiopian Reporter

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

ሳዑዲ አረቢያ ከነዳጅ ምርቷ በቀን 1 ሚሊዮን በርሜል እቀንሳለሁ ማለቷን ተከትሎ የነዳጅ ዋጋ መጨመሩ ተነገረ።

ሌሎች የዓለማችን ነዳጃ አምራች አገራትም በተመሳሳይ የነዳጅን ዋጋን ለማረጋጋት በማሰብ የምርት አቅርቦታቸውን ለመቀነስ ተስማምተዋል ተብሏል።

ሳዑዲ አረቢያ በቀጣዩ ሀምሌ ወር በየቀኑ 1 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ከምርት አቅርቦቷ ላይ እንደምትቀነስ የገለጸች ሲሆን የነዳጅ ላኪዎች ሀገራት ማህበር ወይም ኦፔክ+ እንደ አውሮፓውያኑ በ2024 ዕለታዊ የነዳጅ አቅርቦት በ1.4 ሚሊዮን በርሜል እንደሚቀንስ ገልጿል።

ኦፔክ+ የዓለምን 40 በመቶ የነዳጅ ፍላጎት የሚያሟላ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የነዳጅ ምርት ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ሊያሳድር ይችላል።

የሳዑዲን ውሳኔ ተከትሎ በእስያ ገበያ የደፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ 2.4 በመቶ አሻቅቦ በበርሜል 77 ዶላር ሆኗል።

የሳዑዲ ኢነርጂ ሚንስትር ልዑል አብዱላዚዝ ቢን ሰልማን ፤ የነዳጅ ምርት አቅቦቱን የመቀነሱ ውሳኔ አስፈላጊ ከሆነ ከሃምሌም በኃላ #ሊራዘም ይችላል ብለዋል። ውሳኔው የዓለም የነዳጅ ዋጋን እንደሚያረጋጋ ገልጸዋል።

#ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#ነዳጅ📈

የነዳጅ ዋጋ እያሻቀበ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲሉ የነዳጅ ላኪዎች ህብረት መሪ አስጠነቀቁ።

የ23 ነዳጅ ላኪ ሀገራት ህብረት የሆነው ኦፔክ+ ዋና ፀሀፊ ሄይታም አል ጋይስ ፤ ለሃይል አቅርቦት ያለው ፍላጎት በመጨመሩ የነደጅ ዋጋ እንዳሻቀበ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ጸሃፊው " በቀን የነዳጅ ፍላጎት ወደ 2.4 ሚሊዮን በርሜል ሲያድግ እየተመለከትን ነው " ብለዋል።

ሁለቱ ዋነኛ የነዳጅ አምራችና ' ኦፔክ+ ' አባል የሆኑት ሳዑዲና ሩሲያ የወሰኑት ውሳኔ በዚህ ዓመት መጨረሻ ከፍተኛ የአቅርቦት እጥረት ያስከትላል ሲል ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቋል።

" ይህ ሁለት ሉአላዊ ሀገራት ሳዑዲ አረቢያ እና ሩስያ በፍቃደኝነት የወሰኑት ነው። ይህ ውሳኔ እርግጠኛ ልንሆንበት በማንችልበት ሁኔታ ምክንያት የተደረገ ጥንቃቄ ወይም ቅድመ ዝግጅት ብለን ልንገልጸው እንችላል " ሲሉ የኦፔክ+ ዋና ጸሃፊ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በምርት እጥረት ምክንያት የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 95 ዶላርን አልፎ የነበረ ሲሆን ዋጋው 100 ዶላርን ሊያልፍ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

ይህ የዋጋ ለውጥ በሚቀጥሉት 10 ወራት ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ሊያሻቅብ እንደሚችልና በወሳኝ የኢኮኖሚ መስኮች ያለው የዋጋ ግሽበት ለረዥም ጊዜ እንዲቀጥል ምክንያት ይሆናል የሚል ስጋትን ማጫሩን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳየ። በእስራኤል እና በፍልስጤም ሃማስ መካከል የተቀሰቀሰው ከፍተኛ ጦርነት የነዳጅ ዋጋ እንዲጨምር ማድረጉ ተዘግቧል። የአንድ በርሜል ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በ4 % በላይ መጨመሩ ተነግሯል። ባለፉት ሳምንታት ወደ 96 ዶላር ደርሶ የነበረው የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ባለፉት ቀናት ጥሩ የሚባል ቅናሽ እያሳየ መጥቶ ነበር። ነገር ግን ቅዳሜ በሃማስ እና እስራኤል መካከል…
#ነዳጅ

በመካከለኛው ምሥራቅ በእስራኤልና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ መፍጠር የጀመረው የዋጋ ጭማሪ ተጠናክሮ የሚቀጥል ከሆነ በኢትዮጵያ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ የመጣው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ የበለጠ ሰማይ ሊነካ ይችላል የሚል ሥጋት ፈጥሯል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት እስካሁን ድረስ የነዳጅ ዋጋን ወደ ተጠቃሚው ለማስተላለፍ በወሰነው መሠረት እስሁን ድረስ በአማካይ ከአሥር በመቶ በላይ የዋጋ ጭማሪ እያደረገ የመጣ በመሆኑ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሊፈጥር የሚችለው የዓለም የነዳጅ ዋጋ በቀጥታ ወደ ተጠቃሚው ማኅበረሰብ ከማስተላለፍ ሊቆጠብ እንደሚገባ የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክኤ መክረዋል።

የኢኮኖሚ ባለሞያው አቶ አወት ተክሌ ምን አሉ ?

" በመካከለኛው ምሥራቅ የሚከሰት ጦርነትና አለመረጋጋት በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።

በቀዳሚነትም የዓለም የነዳጅ አቅርቦትና ገበያ የሚታወክ በመሆኑ፣ ይህ ሁኔታ የሚከሰት ከሆነ አሉታዊ ተፅዕኖው ለኢትዮጵያም የሚተርፍ እና የሚያሰጋ ነው።

የዓለም የነዳጅ ምርትና ገበያ ሰላምን ይፈልጋል። እንዲህ ያሉ ትልልቅ ጦርነቶች በተለይ አገሮች በፖለቲካ አመለካከታቸው ወገንተኝነታቸውን በግልጽ በሚያሳዩበት ወቅት የነዳጅ ግብይት ላይ ተፅዕኖ ይኖረዋል።

በተለይ አሁን በተቀሰቀሰው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ምክንያት በአካባቢው የሚገኙ የመካከለኛው ምሥራቅ ነዳጅ ባለፀጎች ለአንደኛው ወገን የሚያደላ የፖለቲካ አቋም ለመያዝ ከተገደዱ ይህንን የፖለቲካ አቋማቸውን የሚገልጹት የነዳጅ ምርትና አቅርቦታቸውን በመገደብ እንደሚሆን ቀደም ሲል የነበራቸውን ተሞክሮ ያሳያል።

ከዛሬ 50 ዓመታት በፊት በነዚሁ ወገኖች መካከል በተቀሰቀሰ ጦርነት ነዳጅ አምራች አገሮች በሁለቱ ተፋላሚዎች መካከል ጎራ ለይተው በመሠለፋቸው በዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ዕክል ፈጥረው ነበር።

አሁንም እነዚሁ ተመሳሳይ አገሮች የሚፋለሙበት ጦርነት በመከሰቱ በነዳጅ ሀብት የታደሉት የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች በዋናነትም፣ ኢራንና ሳዑዲ ዓረቢያ ያሉ አገሮች አንደኛውን ተፋላሚ ወገን ደግፈው ምዕራባዊያኑ ደግሞ ሌላኛውን ወገን ደግፈው የሚቆሙ ከሆነ የዓለም የነዳጅ ምርትና አቅርቦትን ሊያስተጓጉልና ዋጋውም ጣሪያ ሊነካ ይችላል።

ይህ ሁኔታ ከተከሰተ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ትልቅ ፈተና ነው።

ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት ቀስ በቀስ የሚያደርገውን የዓለም የነዳጅ ዋጋን መሠረት ያደረገ ወርኃዊ የችርቻሮ ዋጋ ማስተካከያ ቆም ብሎ ሊፈትሸው ይገባል።

ያልጠበቀውን ጦርነት ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ እንዳለ ኅብረተሰቡ ላይ መጫን የሚያዋጣ አይደለም።

መንግሥት ከነዳጅ ድጎማ ለመውጣት በገበያ ዋጋ እየሠራ ቢሆንም እንዲህ ባሉ ያልተጠበቁ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ግን ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አጠቃላይ ኢኮኖሚው ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖው ግልጽ ከመሆኑ አንፃር በተለይም በአሁኑ ወቅት የሚታየው የዋጋ ንረት ጦርነቱ ሊያስከትል የሚችለውን የዋጋ ጭማሪ ኅብረተሰቡ ላይ እንዲጫን ማድረግ ተገቢ አይሆንም።

ይህ ካልሆነ ግን የዋጋ ንረቱን በማባባስ ማኅበረሰብን ብሎም ኢኮኖሚውን ይጎዳል።

በሌላ በኩል ግን የእስራኤልና የፍልስጤም ጦርነት ከተፋላሚ አገሮች ባሻገር አገሮችን ጎራ ለይተው ወገንተኝነታቸውን እየገለጹ መሆን ምናልባት ትላልቆቹ የነዳጅ አቅራቢዎች ነዳጅ ባያቀርቡ ዓለም ላይ ችግር እንዳይኖር በተቃራኒ ያሉ አገሮች ተጨማሪ ነዳጅ በማቅረብ ገበያውን ለማረጋጋት ሊሞክሩ የሚችሉበት ዕድል እንዳለ አለ። ይህ ሊሆን የሚችለበት ዕድል ጠባብ ቢሆንም አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር ሲታይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው አይቀመስም ብዙ አገሮችን ተጎጂ ያደርጋቸዋል፡፡

በተለይ ከፍተኛ የገቢ ንግድ ያለቸው አገሮች የዋጋ ጭማሪ ሊያስከትልባቸው ይችላል። ስለዚህ በተለይ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው ሊያስከትል የሚችለው ተፅዕኖ በማሰብ መንግሥትም ጊዜውን የዋጀ አሠራር ያስፈልገዋል።

በአጠቃላይ ግን የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ዓለም አቀፉን ኢኮኖሚ ይፈትናል፡፡

ጦርነቱ ዛሬ ያቆማል ቢባል እንኳን በብዙ መልኩ ተፅዕኖው ቀላል አይሆንም። በተለይ ዕቃን የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት ዘርፎች በሚፈጠርባቸው ሥጋት እንቅስቃሴያቸው ይገደባል፡፡ ከዚህም ሌላ መንቀሳቀስ ከቻሉም ከፍተኛ የኢንሹራንስ ሽፋን የሚጠይቁ መሆኑንና ተያያዥ ጉዳዮች የአቅርቦት ዋጋን ስለሚያስወድዱ የጦርነቱ ግልጽ የሆነ ተፅዕኖ አለው። "

(ከሪፖርተር የተወሰደ)

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት  #ነዳጅ

የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ስጪ በሆኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ በተደርገ ማሻሻያ ቀደም ሲል ሲሰጥ ከነበረው የድጎማ መጠን ዝቅ አንዲል መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የነዳጅ ድጎማ መጠን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፦
- በአገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣
- የከተማ አውቶብሶች
- ፐብሊክ ባስ
- ሚዲባስ፣ ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ላይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በየ6 ወሩ የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች የድጎማ መጠን ማስተካከያ የሚደረግ ሲሆን ከጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016ዓ.ም ለሚቀጥሉት 6 ወራት ፦

* ለቤንዚን ተጠቃሚ አገር አቋራጭ አውቶብሶች ፣የከተማ አውቶብሶች እና ፐብሊክ ባስ ብር 22.36 በሊትር ሲሰጥ የነበረውን ድጎማ ወደ 19.16 በሊትር ዝቅ እንዲል፣

* ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲሰጥ የነበረው ብር 23.21 በሊትር ድጎማ በሊትር 19.89 ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ የሆኑ ሚዲባስ፣ ሚኒባስ፣ ታክሲዎችና ባለሶስት እግር የሚሰጠው ድጎማ በየሶስት ወሩ የሚከለስ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ፦

* ከጥር 1 ቀን 2016ዓ.ም እስከ መጋቢት 30 ቀን 2016ዓ.ም ድረስ ለቤንዚን ተጠቃሚዎች ሲስጥ የነበረው ብር 12.78 በሊትር ድጎማ ወደ 6.39 በሊትር፣

* ለነጭ ናፍጣና ለኬሮሲን ሲስጥ የበነረው የብር 13.27 ድጎማ ወደ ብር 6.63 በሊትር ተቀናሽ እንዲሆን የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል፡፡

መረጃው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍ ቢ ሲ ነው።

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ #ነዳጅ

የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል።

የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ችግሩ ለመስተካከል ጊዜ ይወስድ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ደሳለኝ " ጉዳዩ ትልቅ ነዉ፤ እንደ ቀላል የሚታይ አይደለም ያሉን ሲሆን፤ በእርግጠኝነት መንግስትም ሌት ተቀን ርብርብ አድርጎ ነገሮችን ያስተካክላል ብለን ተስፋ እናደርጋለን " ብለዋል።

ከጅቡቲ ከሚመጣዉ በተጨማሪ ክምችት ውስጥ ነዳጅ አልነበረም ወይ ? የተባሉት አቶ ደሳለኝ፤ " ቤንዚን ከአዋሽ ፣ ከሱሉልታ ዲፖዎች ነው እየተጫነ ያለዉ ፤ አሁን ላይ ግን ከክምችት ለመጫን ያልፈለጉበት የራሳቸዉ ምክንያት ይኖራቸዋል ፤ መንግስትም ይህንን አይቶ መፍትሄ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን " ብለዋል።

" አንድ ያለን መንገድ የጅቡቲ ብቻ ነዉ " ብለው " መንገዱ የተበላሸ በመሆኑ ደግሞ የመቆራረጥ ችግር ያጋጥማል ከባድ ዝናብ ሲዘንብ ደግሞ ችግሩን ከፍ ያደርገዋል " ሲሉ ገልጸዋል።

" እንደዚህ ዓይነት ችግሮች የሚያግጥሙ በመሆኑ ለተወሰነ ጊዜ በትዕግስት ማለፍ አስፈላጊ ነው " ብለዋል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የነዳጅ ሰልፎች እየተስተዋሉ ይገኛል።

ይህ መረጃ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስአበባ #ነዳጅ የኢትዮጵያ ነዳጅ አዳዮች ማህበር ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ዕጥረት መከሰቱንና ምክንያቱ ደግሞ ጅቡቲ ላይ የዘነበ ከባድ ዝናብን ተከትሎ የመንገድ መቆራረጥ በመፈጠሩ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪም አስቀድሞም ከቦታዉ በበቂ ሁኔታ ነዳጅ እየተጫነ ባለመሆኑ መሆኑን አመልክቷል። የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ ፥ እነዚህ ምክንያቶች ከነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች የተነገራቸዉ…
#ነዳጅ

" እስከ ነገ ጠዋት ድረስ ችግሩ ይቀረፋል " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ፥ በአዲስ አበባ የነዳጅ እጥረት የተፈጠረው ጅቡቲ ላይ የዘነበውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ ድልድይ በመሰበሩ ነው ብሏል።

በተጨማሪም ነዳጅ የጫነ አንድ የነዳጅ ቦቴ ተገልብጦ መንገድ መዘጋጋት በማስከተሉ የነዳጅ እጥረት መከሰቱን ገልጿል።

ችግሩን ለመቅረፍ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በድሬደዋ በኩል እንዲገቡ መደረጉን የገለጸው ድርጅቱ ይሄንኑ ተከትሎ ትናንት ከሰአት ጀምሮ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መግባት መጀመራቸውን አሳውቋል።

#ዛሬ እና #ነገ ነዳጅ የጫኑ ተጨማሪ ቦቴዎች እንደሚገቡና ችግሩ እስከ ነገ ጠዋት ድረስ እንደሚቀረፍ ለብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ነዳጅ ማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለማግኘት እጅግ ረጅም ሰልፍ ለመጠበቅ እየተገደዱ ሲሆን በዚህ ምክንያት ስራቸውም እየተስተጓጎለ ነው።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ ፦ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል።

አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።

ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።

ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ

ዛሬ በአዲስ አበባ የምትንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ያለባቸውን ማደያዎች ከያዙት የነዳጅ መጠን ጨምሮ ከላይ በምስሉ መመልከት ትችላላችሁ።

#AddisAbabaTradeBureau

@tikvahethiopia
#ነዳጅ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ዛሬ አገልግሎት የሚሰጡ ማደያዎች እና በመሰራጨት ላይ የሚገኝ የነዳጅ አቅርቦት መረጃ ከላይ ተያይዟል።

#AddisAbabaTradeBureau

@tikvahethiopia
#ነዳጅ #ረቂቅአዋጅ

🔴" ዋናው ነገር ኮንትሮባንድ ንግድ መስራታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከባንኮች ብድር መውሰጃ እንደሆነ አረጋግጠናል " - የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

🔵 " ለኮንትሮባንድ ንግድና ብድር ማግኛ ብሎ የገባው ኩባንያ ስርዓት ይይዛል " - ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

በህገወጥ የነዳጅ ግብይት የታየዘ ግለሰብ ነዳጁ ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስራትና እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጣ የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ።

ረቂቁ ምን ይላል ?

- አዲስ የነዳጅ ምርት አከፋፋዮች ስራ ለመጀመር ቢያንስ 500 ሺህ ሊትር የነዳጅ ውጤቶች መያዝ የሚችል ማከማቻ / ዴፖ እና 4 ማደያዎችን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ያስገድዳል።

- በስራ ላይ ያሉ ማደያዎች ደግሞ አዋጁ ከሚጸድቅበት ጊዜ ጀምሮ ለአዲስ አከፋፋዮች የተጣሉትን ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

- አዲስ ጀማሪ ሆኑ ነባሮቹ በ3 ዓመታት ውስጥ ተጨማሪ 6 ማደያዎችን የመገንባት ግዴታ አለባቸው።

- የነዳጅ ውጤቶችን ከተፈቀደው ቦታ ውጭ ያከማቸ፣ ሊሸጥ ከሚገባው ሰው ቦታና የግብይት ስርዓት ውጭ ሲሸጥ የተገኘ ወይም አደጋ ያስከትላሉ በተባሉ መያዣዎች ሲሸጥ የተገኘ ማንኛውም ግለሰብ የተያዘው የነዳጅ ውጤት ተወርሶ ከ3 ዓመት በማይበልጥ እስርና ከብር 50 ሺህ እስከ ብር 100 ሺህ የሚደርስ ቅጣት ይፈጸምበታል።

- መንግሥት ከሚያወጣው የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ተመን ውጪ በተደጋጋሚ የመገበያየት ወንጀል እንዲሁም የነዳጅ ምርቶችን ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀል እስከ 3 ዓመት እስርና እስከ 300 ሺህ ብር ቅጣት ያስጥላል።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ እስመለአለም ምህረቱ ምን አሉ ?

አሁን አሁን ወደነዳጅ አቅራቢነት ስራ ለመሰማራት ከፍተኛ ፍላጎት እየታየ ነው ብለዋል።

በድርጅቱ በተደረገው ጥናት ይህ ፍላጎት የኮንትሮባንድ ንግድ እና ከባንክ ብድር ለመወሰድ ተብሎ የሚደረግ እንደሆነ ተደርሶበታል ሲሉ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው ፥ በዚህ 9 እና 10 ዓመት ውስጥ ከነበሩት 8 ወይም 9 ካምፓኒዎች አሁን 59 መድረሳቸውን ጠቁመዋል።

3ቱ የመንግሥት ገንዘብ አባክነው በፍርድ ቤት ክርክር ላይ ናቸው።

56ቱ ካምፓኒዎችን በማርኬትሼር በመደልደል ነዳጅ እየተሰጠ መሆኑን የገለጹ ሲሆን " ይህ ሁኔታ እራሱ እስካሁን ስምምነት የሌለበት ሁልጊዜ ጭቅጭቅ ያለበት ድርጊት ነው " ብለዋል።

ወደ ነዳጅ ግብይት አዲስ የሚገቡ ካምፓኒዎችን በተመለከተ ምንድነው አላማቸው ? ለምንድነው እንዲህ እያደገ የመጣው የሚለው መጠናቱን ገልጸዋል።

በጥናቱ ውጤትም " ዋናው ነገር ኮንትሮባንድ መስራታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ከባንኮች ብድር መውሰጃ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው " ብለዋል።

እነዚህ የነዳጅ ካምፓኒዎች ባንኮች ጋር ሄደው ብድር በሚጠይቁበት ጊዜ ባንኮቹ " ከናተ ጋር ያላቸው የሥራ አፈጻጸም ይጻፍልን " እየተባለ ደብዳቤ እንደሚጻፍ ገልጸዋል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ምን አሉ ?

° አዋጁ አላማ መንግሥት በየዓመቱ በሚሊዮን ዶላሮች የሚያወጣበትን ለነዳጅ ምርት በአግባቡ ለማስተዳደር ነው።

° በመንግሥት በኩል የነዳጅ አቅርቦትን የማበራከት አላማ የለም።

° አዋጁ በእያንዳዱ የግብይት ሰንሰለት ውስጥ ባሉት ተዋናዮች ላይ የህግ ሪስትሪክሽኖችን ይጥላል። የአቅራቢ፣ የማደያ ... ግዴታዎች አሉ።

° ግብይታችን ችግር አለበት። የአቅርቦት ችግር ሳይኖር ስርጭት ላይ ትልቅ ችግር አለ። የታሰበላቸው ቦታ ያለመድረስን በተመለከተ በክልሎች የሚቀርበው ቅሬታ ገሚሱ ትክክል ነው።

°
ነዳጅ አለ !! ሳምንት ሁለት ሳምንት ገበያ ማስራብ ፣ በነዳጅ ማደያዎች ውስጥ ነዳጅ ይዞ ' ቤንዚን የለም ፤ ናፍጣ የለም ' ብሎ መለጠፍ ይሄ ደግሞ ተጠያቂነት የማያስከትልበት ሴክተራል ባህሪው እንዲቀየር ይታሰባል፤ ይፈለጋል በመንግሥት በኩል ለዛም ነው ይሄ አዋጅ የሚወጣው።

° ከዚህ በኃላ ንግድን አንከለክልም እናሰፋዋለን ፤ ግብይቱ እንዲሳለጥ እንፈልጋለን ነገር ግን ለኮንትሮባንድ ንግድና ብድር ማግኛ ብሎ የገባው ኩባንያ ስርዓት ይይዛል።

° የነዳጅ ኮታ እና ስርጭት ላይ ፍትሃዊ ስርዓት ለመፍጠር ይሰራል።

° ከአቅርቦት እና ስርጭት ይልቅ ማስተዳደሩ ከባድ ነው።

°
ነዳጅ እያላቸው ዘግተው የሚቀመጡ ማደያዎች በስፋት አሉ። የቅጣት መጠኑ ላይ ጠንካራ ስራ ይሰራል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሪፖርተር እንዲሁም ከህ/ተ/ም/ቤት የቀጥታ ስርጭት ማግኘቱን ይገልጻል።

#ኢትዮጵያ #ነዳጅ #ረቂቅአዋጅ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ። ከመስከረም 28/2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የሁሉም የነዳጅ ውጤቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተሰምቷል። በዚህ መሰረት፦ ➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር ➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር ➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር ➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር ➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር…
#ነዳጅ

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በህዳር ወር በነበረበት የመሽጫ ዋጋ እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ " የነዳጅ ማደያዎች እና ኩባንያዎች ያልተገባ የነዳጅ ክምችት ከመያዝ እና የዋጋ ጭማሪ ከማድረግ ተቆጥበው ውሳኔውን ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግሉ " ሲል አሳስቧል።

የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ስንት ነው ?

➡️ ቤንዚን - ብር 91.14 በሊትር
➡️ ነጭ ናፍጣ - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ኬሮሲን - ብር 90.28 በሊትር
➡️ ቀላል ጥቁር ናፍጣ - ብር 100.20 በሊትር
➡️ ከባድ ጥቁር ናፍጣ - ብር 97.67 በሊትር 
➡️ የአውሮፕላን
ነዳጅ - ብር 77.76 በሊትር ሆኗል።

@tikvahethiopia