TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"እኛ ኢትዮጵያዊያን በፍቅር የተደመርን፤ #በፍቅር ያደግን ሰዎች ነን! አማራ~ኦሮሞ ትላልቅ ብሄሮች ለኢትዮጵያ #ውበት ነን!"

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ(አዋሮ ካምፓስ) ተማሪዎች ዛሬ ባደረጉት የአንድነት ሰልፍ ካሰሙት መፈክር የተወሰደ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አማራ🕊ቅማንት!

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ አያሌው ሰሞኑን ግጭት እየተስተዋለባቸው ባሉ የማዕከላዊ ጎንደር ቀበሌዎች በመገኘት ከአርሶ አደሮች ጋር ዛሬ ተወያይተዋል። ካሳለፍነው እሁድ ሌሊት ጀምሮ በጭልጋ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች በተመሳሳይ ሰዓት በተፈጠረ ጥቃት የሰው ህይወት አልፏል፡፡ በርካታ ቤቶች ላይ ደግሞ ቃጠሎእና ዝርፊያ ተፈጽሟል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ #ላቀ_አያሌው ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎ ንብረታቸውን ጭምር ተዘርፈው ተፈናቅለው በአንድ ቦታ ከተሰበሰቡ
ተፈናቃዮች ጋር ባደረጉት ቆይታ አርሶ አደሮቹ በርካታ ሃሳቦችን አቅርበዋል።

የአማራና ቅማንት ህዝብ ዘመናትን በአብሮነት #በሰላምና #በፍቅር አሳልፎ የተዋለደ አንድ ህዝብ ቢሆንም ሁለቱ ህዝብ እንዲለያይ ተደርጓል። ይሁን እንጅ በተፈጠረው ሴራ አሁንም ድረስ ግጭቶች እንዲፈጠሩ ብሎም ሞትና ስደት እንዲፈጠር መደረጉ አሳዛኝ ነው ያሉት አርሶ አደሮቹ በተለይ የቅማንት ሰዎች ነን የሚሉ ዘመናዊ መሳሪያና የወታደር ልብስ የታጠቁ አካላት በአማራው ላይ ግፍ እየፈፀሙ ናቸው ብለዋል።

ራሳችንን ለመከላከል ጥረት በምናደርግበት ወቅትም የማናውቃቸው ፀጥታ ነን የሚሉ አካላት አማራው ላይ ጫና እያሳደሩ ለሞት ስደት እና ዝርፊያ እንድንዳረግ አድርገዋል ብለዋል።

መንግስት ወንጀል እየፈፀሙ ያሉ ግለሰቦችን ድርጅቶችንና በማንነት ስም የሚነግዱ አካላትን በመለየት እርምጃ መውሰድና ህግን ማስከበር አለበት ብለዋል።

አሁን ተፈናቅለን ያለን አርሶ አደሮች መሰረታዊ ፍላጎቶቻችንን እየጨረስን በመሆኑ መንግስት ሊደርስልን ይገባልም ብለዋል።

ከአንድ ቀበሌ ተሰባስበው የመጡ ተፈናቃዮች ወደ 500 አርሶ አደሮች እንደሚደርሱ የገለፁ ሲሆን በተለይ ህፃናትና ሴቶች እንዲሁም አረጋውያን ለከፋ ግጭት እየተጋለጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቅማንት ህዝብ የማንነት ጥያቄ በክልሉ ምክር ቤት ራሱን እንዲችል ውሳኔ ከተሰጠ ወዲህ በነባሩ ጭልጋ(የአማራ ወኪል) እና በጭልጋ ቁጥር አንድ (የቅማንት ወኪል) በሚል ለሁለት አስተዳደር የተከፈለችው የጭልጋ ወረዳ አስተዳዳሪዎቿ በሰጡት አስተያየት እየተከሰተ ያለው ግጭት የሁለቱንም ህዝብ ፍላጎት የሚያንፀባረቅ አለመሆኑን ተናግረዋል። በማንነት ስም ሁከትና ትርምስ እየፈጠሩ ባሉ አካላት ላይ የማያድግም እርምጃ በመውሰድ መፍትሄ መስጠት የክልሉና የፌዴራል መንግስት ድርሻ ነው ብለዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ላቀ በበኩላቸው በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የሚሰሩና የሁለቱንም ህዝቦች የማይወክሉ አካላት መኖራቸውን ገልፀው ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም
የሁለቱ ህዝቦች ወንጀለኞችን የማጋለጥ ስራ በማከናወን ከመንግስት ጎን መቆም አለባችሁ ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ በትኩረት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ላቀ በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ህዝቦች ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።

በጭልጋ ወረዳ በተቀሰቀሰው የሰሞኑ ግጭት ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሞትን ጨምሮ ከ700 ቤቶች በላይ ተቃጥለዋል፤ ንብረት ተዘርፏል። ሰብል ክምር ተቃጥሏል። በአካባቢው ህገ ወጥ ድርጊቶች ተበራክተዋል።

የፌዴራል ወታደርና የክልሉ የፀጥታ ሃይል በአካባቢው ባይመጣ ኖሮ ችግሩ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል የአካባቢ ነዋሪዎችና አመራሮች ለአብመድ ተናግረዋል።

የጭልጋ ወረዳ ዋና መቀመጫ አይከል በአሁኑ ሰዓት ከማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውጭ ሆናለች። ትምህርት ቤቶች ስራቸውን አቁመዋል። የትራንስፓርት እንቅስቃሴም የለም፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት...

(ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ)
#STOP_HATE_SPEECH

በሀገር አቀፍ ደረጃ TIKVAH-ETH "የፀረ ጥላቻ ንግግር" ዘመቻ በማካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ያሉ የጥላቻ ንግግሮች ሀገራችንን #ወደማትወጣው መከራ ውስጥ የሚከታት በመሆኑ ጊዜው ሳይረፍድ ይህን እኩይ ተግባር በጋራ መዋጋት ያስፈልጋል።

በቅድሚያ በሺዎች የሚቆጠሩ የሀገራችን ወጣቶች በሚገኙባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ትኩረት በማድረግ የጥላቻ ንግግር ሊያመጣ የሚችለውን ችግር የማስገንዘብ ስራ እየሰራን እንገኛልን።

ሀሳቡን ካቀረብንላቸው የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ሀሳቡን በመደገፍ እንዲሁም ዘመቻውን ለማገዝ ፍቃደኝነቱን ያሳየን #የመጀመሪያውን ተቋም ነው። በዚህ አጋጣሚ በዶክተር #ታከለ ለሚመራው የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እንዲሁም #ለተማሪዎች_ህብረቱ ያለንን ላቅ ያለ ምስጋናና ክብር እንገልፃለን!!
.
.
.
ውድ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኑ ...3 ተከታታይ ምሽቶችን ከTIKVAH-ETH ጋር አሳልፉ! ስለጥላቻ ንግግሮች እና ከጊዜ ወደጊዜ እየከፋ ስለመጣው አግባብነት የሌለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንነጋገር! የሀገራችሁ ጉዳይ ካሳሰባችሁ ሀሳባችሁን ስጡ...የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ጠቁሙ!

ቅዳሜ፣ እሁድ እና ሰኞ በተከታታይ!

🔹ቦታ - ዋናው ግቢ(በተማሪዎች መግቢያና መውጫ በር አካባቢ)

⌚️ሰዓት - ከምሽቱ 12:30 ጀምሮ

እንግዶች ይኖራሉ!!

#በፍቅር ኢትዮጵያን እንገንባ!!
ከጥላቻ ንግግሮች #እንቆጠብ!!

(የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት)

በቀጣይ፦

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
ጅማ ዩኒቨርሲቲ
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
አምቦ ዩኒቨርሲቲ
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
መቀለ ዩኒቨርሲቲ
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ

#ለቀጣዩ_ትውልድ ከጥላቻ የራቀችን ሀገር እናወርሳለን! ሀሳቡን ለመደገፍ የምትፈልጉ፦
0919 74 36 30 @tsegabwolde

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#StopHateSpeech

የአይናቸውን ብር #አምባር በንባብ የሰበሩ
አንደበታቸውን በመልካም ንግግር የገረዙ
አእምሮአቸውን በመልካም አስተሳሰብ ያጠቡ
ልባቸውን #በፍቅር የሞሉ መልካም ትውልዶችን እናፍራ።

#StopHateSpeech
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH_ETH 🇪🇹 #StopHateSpeech

•ሚያዚያ 23
•ሚያዚያ 25 እና 26

√ረቡዕ - ወሎ ዩኒቨርሲቲ
√አርብ እና ቅዳሜ - መቀለ ዩኒቨርሲቲ

ወደ #ወሎ_ዩኒቨርሲቲ እና #መቀለ_ዩኒቨርሲቲ የሚጓዙት፦

√የአርባምንጭ ዩንቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

√የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት

ከ100 የሚበልጡ #የሰላም እና #የፍቅር አምባሳደሮች በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ይሰባሰባሉ!!

ኑ ኢትዮጵያን #በፍቅር እንገንባ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዳማ👆

የኦሮሚያ እና የሱማሌ ክልል ህዝቦች #በሰላምና #በፍቅር አብረው ለመኖርና ለመስራት ግንኙነታቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጎ የሚመክር የህዝብ ለህዝብ መድረክ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርስቲ❤️ሚያዚያ 26 እና 27👆

የመጨረሻው መዳረሻችን በሰሜናዊቷ ኮከብ መቐለ ከተማ የሚገኘው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ነበር። መቐለ ዩኒቨርሲቲ ብዙ ሺ ኪሎሜትሮችን አቆራርጠው ለፍቅር እና ለሰላም ለመጡት የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ደማቅ አቀባበል አድርጓል።

በመቐለ በነበረን የሁለት ቀን ቆይታ፦

√የደም ልገሳ

√በርካታ ታዳሚዎች የተገኙበት ልዩ መድረክ/የህክምና ባለሞያዎች ስለጥላቻ ንግግር ፅሁፎችን አቅርበዋል፤ ልዩ ልዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎች ቀርበዋል/ - ዝግጅቱ የተዘጋጀው በተማሪዎች ህብረትና በቅን ድል አማካኝነት ነበር።

√እሁድ የፅዳት ዘመቻ

√ሁለተኛው እና የማጠቃለያ መድረክ

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በግቢው ቆይታችን #በፍቅር ተንከባክቦ የቤተሰባችንን አባላት ምንም እንዳይጎልባቸው አድርጓል።

በመቐለው መድረክ፦

•የራያ ዩኒቨርሲቲ
•አክሱም ዩኒቨርሲቲ
•አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጥሪ ተደርጎላቸው ተገናኝተናል። በቀጣይም በየግቢያቸው ተመሳሳይ መድረኮችን በማዘጋጀት የግንዛቤ መስጫ ስራዎች ይሰራሉ።

ፍቅር፤ አድነት፤ ተስፋ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም...

ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ።

አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ።

እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዴባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር" ይላቸዋል "አይደለም! ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው በምላሹ ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል።አሁን የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" ሀገር 'በመቻቻል እና #በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና-

Via Book For All

ሰላም ህልውናችን ነው!
ሰላም እደሩ!

🗞ሃምሌ 09/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ #በጳጉሜ_ወር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመላው ዓለም በምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፀሎት እና ምህላ ወስኗል። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ ጌዴኦ አማሮና ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ ቋሚ ሲኖዶሱ 5ቱን የጳጉሜ ቀናት በፀሎትና ምህላ እንዲታሰብ መወሰኑን ገልፀዋል።…
"...ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው መሰረት ህዝበ ክርስቲያኑ #በአንድነት እና #በፍቅር ሊፀልይ ይገባል" - ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር)

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት የውጭ ጉዳይ መምሪያ የበላይ ኃላፊና የድሬዳዋና ጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ፥ ቋሚ ሲኖዶስ በወሰነው ውሳኔ መሰረት ከጳጉሜ 1 እስከ 5 ድረስ ባሉት ቀናት በአንድነት እና በፍቅር መፀለይ እንደሚገባ ገልፀዋል።

"ምዕመናኑ በአምስቱ ዕለታት #ስለሀገር ሰላም፣ #ፍቅር እና #አንድነት፣ በፀሎት እና በምዕላ በትጋት ጊዜውን እንዲያሳልፍ ጥብቅ መመሪያ የተላለፈ መሆኑን በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ለየአብያተክርስቲያናቱ እና ገዳማቱ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ላሉ ሁሉ እነዚህን ዕለታት በፀሎት እና በምዕላ እንዲያሳልፍ ተወስኗል" ሲሉ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶክተር) ለEOTC ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጾመ ፍልሰታ እና የቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክት ! በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፤ " የጾመ ፍልሰታ " መልዕክት አስተለልፈዋል። ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦ " . . . እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ…
#EOTC

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው #በፍቅር እንዲኖሩ እና #ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳሰቡ።

ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህንን ያሳስቡት ዛሬ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የጾመ ማርያም ሱባኤ ማጠናቀቂያ በዓል ላይ ነው።

ቤተክርስቲያንኗ ፤ " በኢኦተቤ በዐዋጅ ከተደነገጉት አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነውና የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገተ ሥጋ አስመልክተው ሐዋርያት የጾሙት ጾመ ማርያም በየዓመቱ በወርሓ ነሐሴ ከመባቻው አንስቶ ባሉት 16 ቀናት ካህናት እና ምእመናን ሌሊት በሰዓታት ጸሎት፤ ቀን በሥርዓተ ቅዳሴ በመሳተፍ በሕብረት ያሳልፉታል " ብላለች።

" በዚህ በጾመ ማርያም ወይም በተለምዶ የፍልሰታ ጾም ተብሎ በሚታወቀው ወቅት በርካታ ምእመናን እንዲሁም ሕጻናት በቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ሥርዓተ ቅዳሴውን ይከታተላሉ፤ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን ይቀበላሉ " ስትል ገልጻለች።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትም በዚህ ሕጻን ዐዋቂው፤ ወንድ ሴቱ የክረምት ብርድ እና ዝናብ ሳይበግረው በሕብረት በሚጸልበት የሱባኤ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመገኘት ሥርዓተ ቅዳሴውን በመምራት እና ምእመናንን በመባረክ ማሳለፋቸውን ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር  በገዳሙ ተገኝተው በዓሉን ያከበሩ ሲሆን በቅዳሴው መካከል ባስተላለፉት ትምህርትና ቃለ ቡራኬ " የሰላም ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔርን ለኢትዮጵያ ሰላምን ይሰጥ ዘንድ ክርስቲያኖች ከመጠላላት ርቀው በፍቅር እንዲኖሩ እና ሰላማውያን እንዲሆኑ አሳስባለሁ " ብለዋል።

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሱባኤው ወቅት የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ ማስተላለፋቸው የሚታወስ ነው፡፡ 

መረጃ እና ፎቶ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ/ጽ/ቤት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia