TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#WANTED #ተፈላጊ

በምስራቅ ጎጃም ዞን በ ' ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ' በቀራንዮ ንዑስ ከተማ ታህሳስ 18 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 አካባቢ የፍቅር ጥያቄ አቅርቦ አለመግባባት በመፈጠሩ ምክንያት ተጠርጣሪው አቶ ይኸነው ፈንታ ይሁኔ የተባለ ግለሰብ የፍቅር ጥያቄ ባቀረበላት ወጣት ፊት እና ሌሎች የሰውነት ክፍሏ ላይ አሲድ በመድፋት ከፍተኛ አካላዊ ጉዳት በማድረስ ከአካባቢው ተሰውሯል፡፡

የወረዳው ፖሊስም ወንጀሉ ከተፈፀመበት ሰዓት ጀምሮ ተጠረጣሪ ወንጀለኛውን ለመያዝ ክትትል እያደረገ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም በቁጥጥር ሥር አልዋለም።

ስለሆነም ተጠረጣሪ ግልሰቡ ያለበትን አካባቢ ለፖሊስ ትብብርና ጥቆማ በመስጠት በህግ ቁጥጥር ሥር እንዲውል ህዝቡ እገዛ እንዲያደርግ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ስልክ ቁጥር ፡ 058 661 02 01

" ወንጀል ሠርቶ ከተጠያቂነት ማምለጥ አይቻልም "

( በምስራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ፖሊሲ ጽህፈት ቤት )

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#ተወዳደሩ #GenerationUnlimitedEthiopia

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የጀነሬሽን አንሊሚትድ መፍትሔ አምጪ የሥራ ሃሳቦችን ማወዳደር ጀምሯል።

ሚኒስቴሩ የወጣቶችን የሥራ ፈጠራ ሃሳቦች ለማበረታታት ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር የሚያከናውነው የ 2014 ዓ.ም የጀነሬሽን አንሊሚትድ ለውጥ አምጪ የወጣቶች ውድድር ይፋ ሆኗል።

የዚህ ውድድር ተልዕኮ በዓለም አቀፍ ደረጃ 1.8 ቢሊዮን ወጣቶችን ከተለያዩ ዕድሎች ጋር ማገናኘት መሆኑ ተገልጿል።

አቶ ጥዑመዝጊ በርሔ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የአጋርነት እና ፈንድ ዳይሬክተር ፥ " ወጣቶችን የማገናኘት እና አቅማቸውን የማሳደግ እንቅስቃሴ በቀድሞ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ተጀምረው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከቀጠሉት አንዱ ሆኖ ይህ ዓለማቀፍ መሆኑ ይለየዋል " ብለዋል።

አክለውም ፤ " 35 በሚጠጉ አገራት መካከል የሚካሄድ፣ በአገራችን 5 ከተሞች ተከናውኖ በ 8 ሳምንታት የሚጠናቀቅ ፣ ሁለት ተወዳዳሪ ቡድኖችን ለዓለማቀፍ ውድድር የሚያዘጋጅ፣ ለአገራችን ወጣቶች ትልቅ መነቃቃት የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዕድሉን ይጠቀሙበት " ሲል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ተወካይ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ሃሳቦቻቸውን አዳብረው የማኅበረሰባቸውን ችግር በመፍታት ተፅዕኖ ማሳደር እንዲችሉ ድጋፍ በማድረጋችን ኩራት ይሰማናል ብለዋል።

ውድድሩ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች ዘላቂ የልማት ግቦችን ስኬት ለማፋጠን የሚቀርቡ የፈጠራ ሃሳቦች ላይ አትኩሮ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ሃሳባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ መነሻ ገንዘብ ይመድባል።

የውድድር የማመልከቻ መቀበያው ጥር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ሆኖ የካቲት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ይጠናቀቅና ውድድሩ ይቀጥላል።

ይህንን ውድድር የተለያዩ ዓለማቀፍ ተቋማት የደገፉት ሲሆን ሥራው በፈርስት ኮንሰልት አማካኝነት ይከናወናል።

በኦላይን ለመመዝገብ 👉 https://bit.ly/3rQOERQ

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#Share #ሼር

ለጠቅላላ ሀኪሞች የወጣ የኮንትራት ቅጥር ፦

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በዞን ጤና መምሪያ እና በልዩ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊውን ችሎታ የሚያሟሉ ሀኪሞችን በኮንትራት ቅጥር አወዳድሮ መመደብ እንደሚፈልግ አሳውቋል።

👉 የስራው መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 የሙያ መስመር /ተፈላጊ ችሎታ - በጠቅላላ ህክምና በዲግሪ የተመረቀ/ች
👉 የስራ ልምድ- #ዜሮ_ዓመት
👉 ብዛት - 379 (#ሶስት_መቶ_ሰባ_ዘጠኝ )
👉 ደመወዝ - 9,056
👉 የስራ ቦታ - በእጣ ነው የሚለየው

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በሚመደብበት በማንኛውም ዞን / ልዩ ወረዳ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ /የሆነች።

2ኛ. በዕጣ ከጤና ቢሮ ለዞን/ልዩ ወረዳ ሲመደቡ ዞን/ልዩ ወረዳ በሚሰጠው በማንኛውም ጤና ተቋማ /ምደባ / ቦታ ሄደው ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች።

3ኛ. በማንኛውም የመንግስት ተቋም ውስጥ ያልተቀጠረ /ያልተቀጠረች

የመመዝግቢያ ጊዜ ፦ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት። (ከተሰጠው ቀን ውጭ የሚመጣ አይስተናገድም)

የመመዝገቢያ ቦታ ፡ በደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ሲሆን ኦርጂናል የትምህርት እና የሙያ ፍቃድ ማስረጃ ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር መያዝ እንዳትዘነጉ።

የፈተናው ቀን : በቀጣይ ይገለፃል።

@tikvahethiopia
አስተያየት ስጡበት !

የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ምክር ቤቱ ዝርዝራቸውን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

በተለያዩ አግባቦች በተጠቆሙት 42 የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮች ላይ ከዛሬ ጀምሮ የህዝብ አስተያየት ይሰበሰባል።

ይህን 👉https://www.hopr.gov.et/am/web/guest/dialog-candidate ማስፈንጠሪያ በመጫን አስተያየት መስጠት እንደሚቻል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳውቋል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#AmharaRegion

የጠቅላላ ሀኪም የቋሚ ቅጥር ፦

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በክልሉ ስር ባሉ ጤና ተቋማት ጠቅላላ ሀኪሞችን መድቦ ማሰራት ይፈልጋል።

👉 የስራ መደቡ መጠሪያ - ጠቅላላ ሀኪም
👉 ደመወዝ - 9,056 ብር (ዘጠኝ ሺ ሃምሳ ስድስት ብር)
👉 ብዛት - 631 (#ስድስት_መቶ_ሰላሳ_አንድ)
👉 የስራ ቦታ - በክልሉ ባሉ የጤና ተቋማት ክፍት ቦታዎች
👉 ተፈላጊ የትምህርት ዝግጅት - በጠቅላላ ሀኪም የመጀመሪያ ዲግሪ እና 0 (#ዜሮ) ዓመት የስራ ልምድ
👉 የሞያ ፍቃድ ያለው / ያላት

የመመዝገቢያ ቦታ በአብክመ ጤና ቢሮ እና በሁሉም ዞን ጤና መምሪያዎች ማስረጃዎቻችሁን ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

የዞን ጤና መምሪያዎች ምዝገባው ከተጠናቀቀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በሶፍት ኮፒ እና በሃርድ ኮፒ እንዲልኩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ማሳሰቢያ ፦

1ኛ. በማንኛውም ጤና ተቋም ዕጣ በደረሰው ቦታ ላይ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነ/የሆነች
2ኛ. ከዚህ በፊት በመንግስት ጤና ተቋም በቋሚ ቅጥር ያልተቀጠረ/ያልተቀጠረች

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
የግል_ከፍተኛ_ትምህርት_ተቋማትና_እውቅና_ፈቃድ_የተሰጣቸው_የትምህርት_መስኮች.pdf
6 MB
#ETA

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እስከ የካቲት 2014 ዓ.ም ድረስ ያጠናቀራቸውን አጠቃላይ የ350 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን እና የትምህርት መስኮቻቸውን የእውቅና ፈቃድ የሚገልጽ የተሟላ መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

ከ350ው 330ዎቹ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ 20 ተቋማት በርቀት ትምህርት እውቅና የተሰጣቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና በክልል መንግስታት የሚተዳደሩ ተቋማት ይገኙበታል።

የእውቅና ፈቃድ ባልታደሰባቸው የትምህርት መስኮች #አዲስ_ተማሪ_መቀበል_እንዳይችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ይፋ የተደረገው መረጃ እስከ የካቲት ወር ድረስ ያለውን የእውቅና ፈቃድ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል።

በሂደት ላይ ያሉ የእውቅና ፈቃድ እና የእውቅና ፈቃድ እድሳት ጥያቄዎች ውሳኔ ሲያገኙ እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች የእውቅና ፈቃድ ሲሰረዝና በሌሎች ምክንያቶች የውሳኔ ለውጦች በሚኖሩበት ወቅት የመረጃ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አሳውቋል።

በመሆኑም ፦
- ተማሪዎች፣
- ወላጆች፣
- ቀጣሪና የሙያ ፈቃድ የሚሰጡ ድርጅቶች ፣
- የሚዲያና ማስታወቂያ ተቋማት ፣ እንዲሁም መላው ህብረተሰብ የተቋማቱን ወቅታዊ መረጃ በመከታተል ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ በጥብቅ አሳስቧል።

ተቋማት ይፋ ከተደረገው የእውቅና ፈቃድ መረጃ ውጪ ተማሪ ተቀብለው ቢያስተምሩ ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ባለስልጣኑ አሳውቋል፡፡

ይፋ በተደረገው መረጃ የማስተካከያ ጥቆማ የሚኖራቸው ተቋማት በህጋዊ ተወካዮቻቸው በኩል ለባለስልጣኑ ማሳወቅ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

[ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና እውቅና ፈቃድ የተሰጣቸው የትምህርት መስኮች ከላይ በ #PDF ተያይዟል ]

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#መልዕክት

ከሰዓታት በኃላ 2ኛው " የታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በኢትዮጵያ " መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

ለታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጣር 2 ለመታደም ሲመጡ ፦

👉 የራሳችሁን መስገጃ ይዛችሁ ኑ።

👉 አዘጋጆች የሚዘጋጁት ምግብ ቢኖርም ሁሉም የቻለውን ያህል ለሰዎች ጭምር የሚሆን ምግብ ይዞ ይምጣ።

👉 ሁሉም የተመገበበትን እቃ የሚያነሳበትን ፌስታል መያዝ እንዳይዘነጋ።

👉 በመሃል ሌባ ሊኖር ስለሚችል ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረግ።

👉 አቅመ ዳካማዎችን፣ታላላቆችንና ሴቶች የተሻለ ቦታ እንዲያገኙ አድርጉ።

👉 ለአስተናጋጆች፣ ለኻዲሞችና ለፀጥታ አካላት ፍፁም ታዛዥ ይሁኑ።

👉 በጦርነትና በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ለሚንቀሳቀሱ አስተባባሪዎች ድጋፍ ያድርጉ።

👉 እርስ በእርስ በመከባበር እና በመተዛዘን እጅግ የሰለጠነና ምስኪኖችን ታሳቢ ያደረገ ኢፍጣር እንዲሆን ሁላችንም ባለቤቶች እንደሆንን በማሰብ ተግባራዊ ያድርጉ።

📞 ማንኛውም አይነት አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙ በቦታው ለሚገኙ የፀጥታ አካላትና አስተባባሪዎች ወይም በፖሊስ የመረጃ ስልኮች 0111110111 እና ነፃ የስልክ መስመር 991 ላይ በመደወልና መረጃ በመስጠት ይተባበሩ።

(ከአዘጋጆች)

መልካም የኢፍጣር ስነስርዓት !

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ሦስት መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እናዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተላልፏል።

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ጥራታቸው፣ ደህንነታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጠ እና በጤና ላይ ከቀላል እስከ ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ፦

👉 Titan gel፣
👉 Mara Moja
👉 Relief የተባሉ መድኃኒቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አሳስቧል።

መድኃኒቶቹ በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ያልተመዘገቡና በህጋዊ መንገድም ወደ አገር ዉስጥ ያልገቡ ናቸው።

Titan gel የተባለው መድኃኒት በሐኪም ብቻ በመታዘዝ ጥቅም ላይ መዋል ያለበት ሲሆን ነገር ግን በድብቅና በህገወጥ መንገድ ገበያ ላይ አንደሚገኝ ታውቋቃ።

መድኃኒቶቹን ማንኛውም ግለሰብ ወይም አካል በህጋዊ ተቋማት ሆነ በህገወጥ መንገድ ሲያገኛቸው እንዳይጠቀማቸውና በባለስልጣን መስሪያቤቱ ነጻ የስልክ መስመር 8482 በአቅሪያባቸው ለሚገኙ የክልል ተቆጣጠሪዎች ወይም ለጸጥታ አካላት በመጠቆም አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በአዲስ አበባ ሀርመኒ ሆቴል ለዓለም ዓቀፉ የቁርዓን ውድድር ማጣሪያ ሲካሄድ ውሏል። የፊታችን እሁድ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር እንደሚካሄድ ይታወቃል። በዚህ ልዩ ውድድር ላይ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የመጡ ተወዳዳሪዎች መካከል ዛሬ የማጣሪያ ውድድሩ እየተካሄደ ሲሆን ውድድሩ በዓለም ዓቀፍ ዳኞች የተመራ ነበር። በእሁዱ ውድድር የሶማሌ ክልሉ ተወላጅ…
#እጅግ_በጣም_አስቸኳይ

በነገው ዕለት የዓለምዓቀፍ የቁርዓን ሂፍዝ ውድድር መዝጊያ ፕሮግራም በስታድየም ይደረጋል ተብሎ የተገለጸ መሆኑ ይታወቃል።

ይሁንና አንዳንድ ዶክመንቶች በጊዜ ባለማሟላታቸው እንዲሁም አዲስ አበባ ስታዲየም በእድሳት ምክንያት የተቆፋፈረና ምቹ ባለመሆኑ የመዝጊያው ፕሮግራም ከስታዲየም ውጪ እንዲደረግ ተወስኗል።

ስለዚህም ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቅን ከዚህ ጋር የተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮችን በቀጣይ ጊዜያት የምናሳውቅ ይሆናል።

ማሳሰቢያ ፦ ከሀገሪቱ ጫፍ እስከ ጫፍ ወደ አዲስ አበባ እየመጣችሁ ያላችሁ እንግዶች እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ይህንን በመገንዘብ ሳትለፉ ባላችሁበት እንድትከታታሉ እንጠይቃለን።

(አዘጋጅ ፦ ዘይድ እብን ሳቢት የቁርዓን ማህበር)

የነገውን ፕሮግራም ተካፋይ ለመሆን ስትጠብቁ የነበራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን የአዘጋጆቹን መልዕክት ያልሰሙ ካሉ #ሼር አድርጓቸው / ላኩላቸው።

@tikvahethiopia
#ሼር

የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት መስከረም 30 /2015 ከሚጀምረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ጋር በተያያዘ የዩኒቨርሲቲ እና ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች አድራሻ አሰራጭቷል ፤ ከላይ ይመልከቱ።

@tikvahethiopia
#Urgent🚨

በሊባኖስ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ ቀርቧል።

በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በተለይ በደቡብ እና ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርቧል።

ጽ/ቤቱ በደቡብ እና ምሥራቅ ሊባኖስ ያለው የፀጥታ ችግር እየተባባሰ እንደመጣ አመልክቷል።

ይህን ተከትሎ በአካባቢዎች ያሉ ዜጎችን ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ጠቁሟል።

በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ከታች በተቀመጠው መሠረት ፦

➡️ ስማቸውን ፓስፖርት ላይ እንደተፃፈው፣

➡️የፓስፖርት ቁጥር

➡️ ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

° በደቡብ ሊባኖስ (ታየር ፣ ሱር ፣ ቢንት ጅቤል ፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89

° በምሥራቅ ሊባኖስ (አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት አሳስቧል፡፡

#Share #ሼር

@tikvahethiopia