TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57.1K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia #Adama ሰላም ሚኒስቴር " የአገር ግንባታ መሠረታዊያን በሚል ርዕስ ለሚዲያ አካላት ከቅን ልቦች በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር " ትላንት በአዳማ ከተማ የአንድ ቀን የምክክር መድረክ አካሂዶ ነበር። በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስትር አቶ ታዬ ደንደኣ፣ መሰል የውይይት መድረክ በኢትዮጵያ ለሚስተዋለው ግጭትና አለመግባባት መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችል…
#ETHIOPIA

" ለመሆኑ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ ? " - አቶ ወንድሙ ኢብሳ

" መከላከያ ወንድሞቹን መግደል የለበትም፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም " - አቶ ታዬ ደንደአ


ሰላም ሚኒስቴር ረቡዕ ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም አዳማ ከተማ አዘጋጅቶት በነበረው የውይይት መድረክ የተጋበዙት ጠበቃና የሕግ አማካሪ አቶ ወንድሙ ኢብሳ፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሌሎችም ጋዜጠኞች ፦
° ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ለማምጣት እየሄደበት ያለው ሁኔታ ፣
° ሁለት ጊዜ የከሸፈው የመንግሥትና የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / " ኦነግ ሸኔ " ድርድርን በተመለከተ የተሻለ አማራጭ ሊመጣ የሚችለው ምን ቢደረግ እንደሆነ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ተከታዮቹን ምላሾች እንካችሁ ብለዋል።

አቶ ወንድሙ ኢብሳ ስለሰላም ሚኒስቴር ምን አሉ?

* የሰላም ሚኒስቴር ላይ ጥያቄ አለኝ። ለመሆኑ እራሱ ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ ? ሰላም ሚኒስቴር በራሱ ጊዜ ሰላምን መስበክ አለበት በስውርም በአደባባይም ፡ አሁን ላይ ሰላም ሚኒስቴር ውስጥ የማያቸው ሰዎች በስውር አማፂያንን ሲደግፉ አያለሁ።

* ለምሳሌ የሁለተኛው የ " ሸኔ " እና የመንግሥት ድርድር ሲደረግ ከሰላም ሚኒስቴር ውስጥ የሆኑ ሰዎች (ስማቸው ከተፃፈ አላውቅም) ከሕውሓት ጋር የተደራደርክ፣ ሰላም የፈጠርክ " ሸኔ " ኦሮሞዎችን ለምንድን ነው እነርሱ የጠየቁትን ጥያቄ በሙሉ መልስ እሺ ያላልከው ? ያሉ አሉ።

* ጥያቄያቸው ደግሞ (የሸኔ) " የሽመልስ አብዲሳ ቦታ ለእኛ ይሰጠን፣ የኦሮሚያ መንግሥት አሁን ያለው ይፍረስና አዲስ ምርጫ ይካሄድ የሚል ነበር። ሰላም ሚኒስቴስ ውስጥ ሆኖ ይህን የሚጠይቅ ሰው ስላለ ሰላም ሚኒስቴር ጤናማ አይመስለኝም።

* አንድ ኢንጅነር ቢመረቅና ሥራ ቢያገኝ ለበርካታ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል። ፖለቲከኛ ግን 'ስንት ሰው ልግደል' ነው የሚለው። በእኔ ምክንያት አንድ። ሰው መሞት የለበትም የሚል ፓርቲ ያስፈልጋል። በፖርቲ ሥም የሚፈጠር ሞትን የኢትዮጵያ ሕዝብ #ማውገዝ አለበት።

የመንግሥትና የሸኔ (ኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት) ድርድር ዘላቂ መፍትሄው ምንድን ነው ? ለሚለው ጥያቄም፣ መንግሥትና የ " ሸኔ " ድርድር አሁንም መቀጠል አለበት ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ተሳታፊ ጋዜጠኞችና ሌሎች ምሁራን በበኩላቸው ፦

° ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሄደበት ባለው ተደጋጋሚ መንገድ ለሰላም ለውጥ ማምጣት ይችላል ወይ ?

° በግጭት ምክንያት
#የሚፈናቀሉ ሰዎችን አሁንም ማስቆም አልቻለም በዚህ ሁኔታ እንዴት ሰላምን መፍጠር ይቻላል ?

° መስሪያ ቤቱ ሰላምን ልማስረፅ ምን እየሰራ ነው ?

° የሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሑፎች ለችግሮችን ይመጥናሉ ወይ ?

° በተጨባጭ መሬት ላይ ያለው ችግር እንዴት ይታያል ?

° በአማራና በኦሮሚያ የሚስተዋሉ ግጭቶችን ለመፍታት ለምን መግባባት ላይ ማድረስ አልተቻለም ?.... የሚሉ ጥያቄዎች ተሰንዝረዋል።


የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንድአ ምን ምላሽ ሰጡ ?

- ብዙ ሥራ እየሰራን መጥተናል ገና ብዙ ይቀረናል። ነገር ግን የሚገባንን ሁሉ #ሥልጣን ተሰጥቶናል ብለን አናምንም እንደ ሰላም ሚኒስቴር። አዎንታዊ ሰላም ከማስረፅ አኳያ ትልቅ ስልጣን አለን እየሰራን ነው። የሰላም ችግር ሲፈጠር፣ #ሰው ሲፈናቀል ያንን የማስቆም ስልጣን ግን ለእኛ አልተሰጠንም። ይሄ #የአወቃቀር ችግር ነው።

- የአደጋ ሥጋት እንኳ #ለእኛ አይደለም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ነው። #ፓሊስ ለእኛ ተጠሪ አይደለም። መሆን የነበረበት እዚህ ነው። #የግጭት ሥጋት ሲኖር የምናዘው አንድም #ሚሊሻ የለንም። ስለዚህም ለሚፈጠሩ ግጭቶች የሰላም ሚኒስቴር #ሊወቀስ_አይገባም

- ትክክል ነው በተመሳሳይ አይነት ሥራ የተለየ ውጤት አይፈጠርም። በእኛ በኩል ግን ተመሳሳይ ሥራ እየሰራን ነው ብለን አናምንም። 

- ጥናታዊ ፅሑፎች እና በመሬት ላይ ያለውን ችግር በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ፣ የስልጣን፣ የኢኮኖሚ፣ የፍትህ ችግሮች አሉብን። ሥልጣን ካልተገደበ፣ ተጠያቂነት ካልተረጋገጠ፣ ኢኮኖሚው በፍትሃዊነት ካልተሰራጨ፣ ሌቦች ከተቆጣጠሩት…ሰላም ሊመጣ አይችልም።

- የተሰጠን ስልጣን ወቅታዊ ችግር መፍታት ሳይሆን ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ነው። 

- ተጠያቂነትን መስፈን አለበት። ከተጠያቂነት አኳያ ደግሞ ሥልጣን የተሰጣቸው አሉ። ለምሳሌ የፍትህ ሚኒስቴሩ ሥራው ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ መሆን ነበረበት #ድርድር ከመሄድ ይልቅ።

- ሰላም ሚኒስቴር ሰላም ነው ወይ? ለሚለው ጥያቄ አዎ ሰላም ነው። ሰላም የማንሆንበት ምክንያት የለንም። እኛ እያደረግን ያለነው የአገር አንድነት እንዲጠናከር፣ ሰላም እንዲሰፍን ተባብረን እየሰራን ነው።

- በኦሮሚያ ክልል ለ5 ዓመታት ጦርነት እየተካሄደ በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው ችግር አለ። የትግራይ ክልሉም በጣም ይጸጽተናል። ግን ይህንን የሚያደርገው ከጀርባ ያለው ማነው? እሱን ነው ማወቅ የሚያስፈልገው።

- መከላከያ ሰራዊት ወንድሞቹን መግደል የለበትም፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም። ከብሔርተኝነት አኳያ ኦሮሞም ፣ አማራም ፣ ትግራይም በጣም አስቸጋሪ ችግር ነው ያለው። ለአማራ ችግር ኮዙ ኦሮሞ ነው፣ ለትግራይ አማራ ነው ተብሎ ይወሰዳል። ግን ችግሩ በእውነት ምንድን ነው ? ከዚያ ጀርባ ያሉት እነማን ናቸው? ይህንን ሚዲያዎች ለሕዝብ ማስገንዘብ አለባቸው ብለዋል።

ጥንቅሩ በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
አቶ ታዬ ከሰሞኑን ምን ሲሉ ነበር ?

ዛሬ ታህሳስ 1/2016 ዓ/ም የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፊርማ ባረፈበት ደብዳቤ ከሰላም ሚኒስትር ዴኤታነት መነሳታቸው የተገለፀላቸው አቶ ታዬ ደንደአ ከሰሞኑን አነጋጋሪ ቃለ ምልልሶችን ሲሰጡ ነበር።

ለአብነት ፦

▪️የቲክቫህ - ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባልን ጨምሮ ፤ ለተለያዩ ብዙሃን መገናኛዎች በአዳማ በነበረ አንድ ፕሮግራም በሰጡት ቃለ ምልልስ ተከታዮቹን ብለው ነበር ፦

* እንደ ሰላም ሚኒስቴር የሚገባንን ሁሉ #ሥልጣን ተሰጥቶናል ብለን አናምንም። በሀገሪቱ የሰላም ችግር ሲፈጠር፣ #ሰው ሲፈናቀል ያንን የማስቆም ስልጣን ለእኛ አልተሰጠንም። ይሄ #የአወቃቀር ችግር ነው።

* የአደጋ ሥጋት እንኳን #ለእኛ አይደለም ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅሕፈት ቤት ነው። #ፓሊስ ለእኛ ተጠሪ አይደለም። መሆን የነበረበት እዚህ ነው። #የግጭት ሥጋት ሲኖር የምናዘው አንድም #ሚሊሻ የለንም። ስለዚህም ለሚፈጠሩ ግጭቶች የሰላም ሚኒስቴር #ሊወቀስ_አይገባም

* የስልጣን ፣ የኢኮኖሚ ፣ የፍትህ ችግሮች አሉብን። ሥልጣን ካልተገደበ፣ ተጠያቂነት ካልተረጋገጠ፣ ኢኮኖሚው በፍትሃዊነት ካልተሰራጨና ሌቦች ከተቆጣጠሩት …በፍፁም ሰላም ሊመጣ አይችልም።

* ተጠያቂነትን መስፈን አለበት። ከተጠያቂነት አኳያ ደግሞ ሥልጣን የተሰጣቸው አሉ። ለምሳሌ የፍትህ ሚኒስቴሩ ሥራው ተጠያቂነትን ከማስፈን አኳያ መሆን ነበረበት #ድርድር ከመሄድ ይልቅ።

* በኦሮሚያ ክልል #ለ5_ዓመታት ጦርነት እየተካሄደ በአማራ፣ በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋለው ችግር አለ። የትግራይ ክልሉም በጣም ይጸጽተናል። ግን ይህንን የሚያደርገው ከጀርባ ያለው ማነው ? እሱን ነው ማወቅ የሚያስፈልገው።

* መከላከያ ሰራዊት ወንድሞቹን መግደል የለበትም ፤ ወንድሞቹም መከላከያን መግደል የለባቸውም።

▪️ከቀናት በፊት ከ " ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ " ክፍል ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ደግሞ ተከታዮቹን ብለው ነበር ፦

- በአሁኑ ወቅት በመንግስት ወስጥ ሙስና እና ብልሹ አሰራር በከፍተኛ ሁኔታ የተንሰራፋ ነው።

- ድሮ መሬት ይዘረፋል ከሚባለው በላይ አሁን ሕጋዊ ሆኖ በቃላት መግለጽ በሚከብድ መልክ እየተንሰራፋ የአስተዳደር ቀውስ ተፈጥሯል።

- የኑሮ ውድነት ሰማይ ደርሶ የመንግሥት ሠራተኛ ቤት ኪራይ መክፈል አቅቶት ከዚህ ቀደም ዘመዶቹን ይረዳ የነበረው ሠራተኛ አሁን በቤተሰቦቹ ይደጎማል።

- በኦሮሚያ ያለው ሕዝባችን ባለፉት 5 ዓመታት ይሞት ነበር። ስንት እንደሞተም በቁጥር አይታወቅም። በጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በእስራኤል ስንት አንደሞተ፣ ከፍልስጤም ስንት አንደሞተ በቁጥር ይታወቃል። በኦሮምያ ያለው እልቂት ግን የሚታወቅ ነገር የለም።

- ስንት የደሃ ሰው ቤት ተቃጠለ፣ ስንት ሰላማዊ ዜጋ ሞተ፣ ምን ያህል ንብረት ተዘረፈ፣ ስንት ሰው አካሉ ጎደለ፣ የሚለውን የሚያውቀው ሰው የለም።

- በኦሮሚያ ከየትኛውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ነው ያለው ፤ ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ መልኩ ነው አሁን እየሆነ ያለው።

-  በመንግሥት እና በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት መካከል የነበረው የሰላም ድርድር እንዲደናቀፍ ያደረገው እኔ ያለሁበት መንግሥት ነው።

- #እኔ_ያለሁበት_መንግሥት ‘ ችግር ውስጥ ነን ፤ ተወያይተን መፍትሄ እናመጣለን ’ ብዬ ስጠይቅ ቤቱ ለውይይት ክፍት አይደለም በማምታታትና በማደናገር ማለፍ ነው የሚፈለገው፤ የእኔ መንግሥት እንዲህ ዓይነት ጸባይ ነው ያለው።

- የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትን (OLA) የሚመራው ጃል መሮ ፣ መንግሥት ከፈለገ ይግደለኝ ብሎ ፣ መንግሥት በሚቆጣጠረው የአየር ክልል አልፎ፣ ወደ ታንዛኒያ በአውሮፕላን መሄዱ ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ነው የሚያሳየው ብዬ አምናለሁ።

- በታንዛኒያ ፣ የዳሬሰላሙ የሰላም ድርድር ተጀምሮ በ2ኛው ቀን ፣ ከመንግሥት ወገን ፕሮፓጋንዳ መንዛት ነው የተጀመረው " ሸኔን አጥፍተናል፣ አከርካሪውን ሰብረናል " የሚል ፕሮፓጋንዳ ተጀመረ። ፕሮፓጋንዳ ብቻ ሳይሆን ጦር ከያለበት ተንቀሳቅሶ በ5 ዓመት ውስጥ ያላለቀው ጦርነት በድርድሩ ጊዜ ለመጨረስ፣ እንቅስቃሴ ተደርጓል። ይህ ከመንግሥት ወገን ለሰላም ፍላጎት አለመኖሩን ያሳያል።

▪️የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም. የ3 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ካቀረበ በኃላ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለምልልስ ይህንን ብለዋል ፦

° በአማራ ክልል ጉዳይ ፤ የተ / ም / ቤት ጭምር ሄዶ ህዝብ ባነገረትበ ጊዜ እንደዚህ አይነት አዝማሚያዎች መኖራቸው ቀድም ብሎ ተለይቶ ነበር፤ ግን ችግሮችን ከመፍታትና አፋጣኝ የሆነ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነትና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል። እኛ ፖሊስ / ፀጥታ ኃይል #የማዘዝ_ስልጣን አልተሰጠንም።

° መንግሥት ከሕወሓት ጋር የፈታውም እና ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት ጥሩ ነው። በአማራ ክልል ያለውም በዚያው መንገድ ሊታይ የሚችል ነው።

ዛሬ ከስልጣን እንደተነሱ የተነገረው አቶ ታዬ ደንደአ ፤
- የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባል፤
- አገሪቷን በሚያስተዳድረው የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው።

@tikvahethiopia