TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደሴ🔝

በኦሮሞ ልዩ ዞን በተከሰተው #ግጭት የተገደለን የአማራ ልዩ ሀይል አባል የቀብር ስነስርዐት ተከትሎ በደሴ ከተማ መለስተኛ የተቃውሞ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን፣ #መንገዶችም ተዘግተው ውለዋል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያን እንዳናጣት‼️

"ሰሞኑን በከሚሴና አካባቢው የተቀሰቀሰው #ግጭት አላስፈላጊ የህይወት ዋጋ እያስከፈለ በመሆኑ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች የልዩ ዞኑ መስተዳደርና የፌዴራል መንግስት ተቀናጅተው አካባቢውን የማረጋጋት ስራ በአስቸኳይ እንዲስሩ ጥሪ ማቅረብ እወዳለሁ። እንደሚደርሰን መረጃ ከሆነ በአካባቢው ያለው ግጭትና ውጥረት አሁንም እንደቀጠለ ነው። እደዚህ አይነት ግጭቶች መንግስት አስፈላጊውን አፅንኦት ሰጥቶ እንዲቆሙ ካላደረጋቸው ወደ አጎራባች አካባቢዎች ብሎም ክልሎች በቀላሉ የመዛመት ባህሪ አላቸው። በመሆኑም የፌዴራል መንግስቱ ጊዜ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ሊሆን አይገባውም። በዚህ አጋጣሚ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለይ ተደማጭነት ያላችሁ ግለሰቦች inflammatory የሆኑና ግጭት የሚያባብሱ ቃላትን ከመወርወር እንድትቆጠቡ አደራ እላለሁ።" አክቲቪስት ጃዋር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው ሌላ ክልል #እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ #ተስፋቸውን ይቁረጡ፡፡›› የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ #ዮሐንስ_ቧያለው
.
.
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ ቧያለው በክልሉ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተከሰተው #ግጭት ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በግጭቱ ሕይወታቸውን ባጡ ወገኖች እና በደረሰው የንብረት ውድመት አዴፓ ማዘኑን የገለፁት አቶ ዮሐንስ ለተጎጅ ቤተሰቦችና ወገኖች #መፅናትን ተመኝተዋል፡፡

ጉዳቱ ከመድረሱ በፊት የክልሉ መንግሥት ሥጋቱን ያውቀው እንደነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም ‹‹እንደስጋት በክልሉ የፖለቲካ ኃይሎች ግጭትን ለዓላማቸው መጠቀሚያ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ግምቶች ነበሩን፤ ግን ከገመትነው #የፈጠነ ሆኖብናል›› ብለዋል። ይህን ያክል የንብረት እና የሰው ሕይወት ጠፍቷል ለማለት የቴክኒክ ቡድኑ የጥናት ምላሽ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ ሕግና ሰላምን በማስጠበቅ ረገድ በአዴፓ እና በክልሉ መንግሥት እምነት አጥቷል የሚሉ ሐሳቦች ይደመጣሉ በእናንተ በኩል ምን ግምገማ አለ? ተብሎ ከጋዜጠኞች ለተነሱ ጥያቄዎችም አቶ ዮሐንስ ‹‹እንዲያውም አሁን ሕዝቡ በአዴፓ ላይ ከፍተኛ #እምነት የጣለበት ወቅት ነው፤ አዴፓ በሕዝቡ አመኔታ ማግኘቱን ተከትሎ #ለመነጣጠል የሚፈልጉ ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ በመሆኑ ሕዝቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል›› ብለዋል፡፡ ‹‹በተለያዩ አካባቢዎች የተፈጠሩ ግጭቶች የአዴፓ እና የአማራ ሕዝብ አንድነት የሚያስፈራቸው ኃይሎች የፈጠሩት ሴራ ነው›› በማለትም ተናግረዋል፡፡

ሕዝቡ መራር በሆነው በዚህ ጊዜ #አብሮነቱን እንዲያጠናክር የጠየቁት አቶ ዮሐንስ ‹‹አማራ ክልል ውስጥ ወንጀል ሠርተው በሌላ ክልል እንደበቃለን ብለው የሚያስቡ ካሉ ተስፋቸውን ይቁረጡ፤ ከአጐራበች ክልሎች እስከ ፌዴራል መንግሥት ድረስ ወንጀለኞችን ለመያዝ በጥምረት እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡ በክልሉ መሠል ችግር እንዳይከሰት ብቁ ዝግጅት እንደተደረም ተናግረዋል፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
37 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

ባለፈው #ቅዳሜ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ሊካሄድ በነበረው ጨዋታ ላይ #ግጭት እንዲፈጠር በማነሳሳት የተጠረጠሩ 37 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጉዳዮች መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ ዳንጊሶ ጉዳዩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል።

ሃላፊው በመግለጫቸው የራሳቸውን ፖለቲካዊ አጀንዳ የሚያራምዱ አካላት በሸረቡት ሴራ በዕለቱ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

በተፈጠረው ግጭትም በአንዲት ሴት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደምትገኝና 17 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል።

ከዚህ ባለፈም የ10 መኪናዎች መስታወት ሙሉ በሙሉ የተሰባበረ ሲሆን ፥ አንድ ግሮሰሪ ላይም ዘረፋ ተፈጽሟል ነው ያሉት።

ግጭቱ የከፋ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የፀጥታ አካላት በመቀናጀት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉንም አንስተዋል።

ስለሆነም መገናኛ ብዙሃን የተከሰተውን ችግር ከማጋነንና #የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት #እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽንም ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በደቡብ ፖሊስና በወላይታ ድቻ እግር ኳስ ክለቦች መካከል የሚደረገውን ጨዋታ ጨምሮ ሀዋሳ ከተማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ ታውቋል።

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ

በድሬዳዋ በተለምዶ “መስቀለኛ” በተባለው አካባቢ ሰርግ ላይ የተፈጠረ ድንገተኛ #ግጭት አድማሱን አስፍቶ ለሦስት ቀናት በአካባቢው ውጥረት እንዲነግስ አድርጓል፡፡ በግጭቱ መንስዔነት የተለያዩ ምክንያቶች እየተነገሩ ሲሆን እስከትላንት ጠዋት ድረስ በአካባቢው የተኩስ ድምፅ እየተሰማ ነው ተብሏል፡፡ በግጭቱ እስካሁን ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው ተነግሯል፤ ከገንደተስፋ ወደመስቀለኛ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶ የቆየ ሲሆን ትላንት የአካባቢው ተማሪዎችም የ10ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና አለመፈተናቸው ታውቋል፡፡

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ...

በቀን 27/09/2011 ዓ/ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በተፈጠረ #ግጭት የመካኒካል ኢንጂነሪንግ 2ኛ ዓመት የሆነ ተማሪ ዮሃንስ ማስረሻ በሞት ተለይቷል በዚህም ዩኒቨርሲቲው የተሰማውን ሃዘን ገልፆ ድርጊቱን የፈፀሙ ግለሰቦችን ለህግ ለማቅረብ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል። ለተማሪው ወላጆች፣ ቤተሰቦች እና ጓደኞች መፅናናትን ተመኝቷል።

TIKVAH-ETH በወጣቱ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይመኛል!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በድሬዳዋ ከትናንት በስተያ ምሽት አንስቶ እስከ ትላንት በቀጠለ #ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሆስፒታል ምንጮች እና የዓይን ምስክሮች ለዶቼቬለ/ለጀርመን ድምፅ ራድዮ/ ተናገሩ። በዚሁ በተለምዶ ደቻቱ እና 5ተኛ ተብለው በሚጠሩ ሰፈሮች ወጣቶች መካከል ተፈጠረ በተባለው ግጭት #በጥይት ተመተው ቀላል እና መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው 3 ሰዎች እንዲሁም የአንዲት ወጣት #አስከሬንም ሆስፒታላቸው መምጣታቸውን የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አብዱራህማን አቡበከር ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የዓይን ምስክሮች ደግሞ በግጭቱ ወቅት የሌላ አንድ ወጣት ህይወት በተባባሪ ጥይት ማለፉን ተናግረዋል። በሰፈሮቹ ዛሬ አንጻራዊ #ሰላም መስፈኑ ተዘግቧል።

🗞ቀን 13/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በተማሪዎች መካከል በተነሳ #ግጭት የህይወት፣የአካልና የንብረት ጉዳት መድረሱን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው በጀነራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ ትላንት በተነሳው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች አምስት ተማሪዎች መቁሰላቸው ተመልክቷል።

በግቢው የተማሪዎች ዲን ዋቅጋሪ ጉልማ እንደገለጸው በህመም ላይ የነበረ አንድ ተማሪ ከትላንት በስቲያ ህይወቱ ካለፈ በኋላ በአንዳንድ ተማሪዎች ሌሊቱን ግጭት እንዲቀሰቀስ ተደርጓል።

በዚህ ግጭትም ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች አምስት ተማሪዎች ላይ ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በተማሪዎች መኝታ አካባቢ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከክልል ከፌዴራልና ከዞኑ የተውጣጣ ግብር-ሃይል ተቋቁሞ ተማሪዎችን ለማቀራረብና ለማግባባት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ሊቀመንበር ዩሴፍ ደቻሳ በበኩሉ ችግሩ በተፈጥሯዊ መንገድ የሞተን ተማሪ ተገፍትሮ ነው የሞተው በሚል አንዳንድ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ በነዙት ወሬ ምክንያት መፈጠሩን ተናግሯል።

በአሁኑ ወቅት በጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ የሚገኙ ተማሪዎች ተበታትነው ያሉ ቢሆንም የማግባባት፣ በችግሩ ዙሪያ ግንዛቤ የመፍጠርና ጉዳት ያደረሱ ተማሪዎችንም በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
🗞ቀን ሰኔ 26/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በትላንትናው ዕለት ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሀዋሳ ከተማ በተፈጠረ #ግጭት በትንሹ 3 ሰዎች #መሞታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
.
.
(#Reuters) - At least three people have died in Ethiopia's southern city of Hawassa, hospital authorities said on Friday, amid a showdown between state security forces and some local activists who want to declare a new region for their Sidama ethnic group.

የሮይተርስን ዘገባ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/HAWSSA-07-19
#ያሳዝናል

ከትናንት ጀምሮ በሲዳማ ዞን በተፈጠረው #ግጭት በተለይ በሞርቾ እና በሃገረ ሰላም ከተሞች #ከሞቱት መካከል አብዛኛዎቹ #ታዳጊ ወጣቶች መሆናቸውን የጀርመን ራድዮ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DrAbrhamBelay

የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በትግርኛ ቋንቋ ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በሰጡት ቃለ ምልልስ ምን አሉ ?

- ሁሉም ክልሎች እና የፌደራል መንግስት ተቋማት ለትግራይ መልሶ ማቋቋም እንዲረዱ ፣ ትምህርት ጨምሮ ሁሉም የመንግስት አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ያስቻለው የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ነው ፡፡ ስለሆንም የፕሪቶሪያው የሰላም ውል አሁንም በቦታው ነው ያለው።

- ከጦርነቱ በፊት የነበረው #ግጭት_ቆስቋሽ ሁኔታ እና አካሄድ ወደ ጦርነት እንዳይሸጋገር ለማድረግ በፌደራሉ መንግስት ብዙ ጥረት ተደርጓል። ክልሉን ይመሩ የነበሩ ሰዎች ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። ጦርነቱ በትግራይ #አመራሮች እና #ኤሊቶች ገፋፊነት ከተጀመረ በኋላም ጦርነቱ ቆሞ ወደ ውይይት እንዲገባ ጥረት ተደርጓል። ጦርነቱ ውድመቱ እንዳይባባስ በድብቅም ይሁን በግላጭ በርካታ ውይይቶች ቢካሄዱም ሊሳካ አልቻለም።

- ጦርነቱ ተከትሎ በተለይም ከትግራይ ውጪ በመላ አገሪቱ ውስጥ የነበሩ ባለሃብቶች ፣ የመንግስት ሰራተኞችና በሌላ ስራ የተሰማሩ ከስራ ውጪ የሆኑበት ፣ የታሰሩበት ፣ ንብረታቸው በርካሽ በመሸጥ እንዲሰደዱ የሚገደዱበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። ይህን እንዲቆም የፌደራል መንግስት ባደረገው ሰፊ ጥረት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ብዙ አላሳፈላጊ ነገሮች ማቆም ተችሏል።

- " በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ከኔ በላይ ደስተኛ ያለ አይመስለኝም። ምክንያቱ ስምምነቱ ብዙ ነገሮችን ከማባባስ ታድጓል፡፡ በፌደራል መንግሥት በኩል ስምምነቱን የፈረሙ የመንግስት ልኡካን ጀግኖች ናቸው፡፡ ምክንያቱ እንደ አገር ሊቀጥል የነበረው የስውና የንብረት ኪሳራ እንዲቆም ያደረጉ ናቸውና፡፡ "

- የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሁሉም የትግራይ ችግሮች ይፈታል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ስምምነቱ እንደ አገርና ትግራይ ብዙ ጥፋቶችን አስቁሞልናል፡፡ ስምምነቱ በመፈረሙ ምክንያት ተኩሶ ቆሞ ህዝቡ የሰላም አየር እንዲተነፍስ ሆኗል፡፡ ትልቁ የስምምነቱ ትሩፋት ይህ ነው።

- ከተወሰኑት በቀር በርካታው የትግራይ አከባቢዎች በፌደራል መንግስት ቁጥጥር ስር ውለው ነበር። በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት የአከካቢው አስተዳደር ተረክቧል። አሁን የተቀሩት አከራካሪ የሚባሉ ቦታዎች ናቸው። እነዚህም ተጨማሪ ግጭትና ደም መፋሰስ እንዳያስከትሉ በማሰብ በፌደራል መከላከያ ሰራዊት ስር እንዲቆዩ ተደርጓል።

- በትግራይ ክልል የተቋቋመው ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ውጤት ነው። ሁሉም ክልሎችና የፌደራል መንግስት ተቋማት ለክልሉ እንዲረዱ ፣ ትምህርት ጨምሮ ሁሉም የመንግስት አገልግሎት እንዲጀምሩ ያስቻለው የፕሪቶሪያው የሰላም ውል ነው ፣  ስለሆንም የፕሪቶሪያው የሰላም ውል አሁንም በቦታው አለ።

- ስምምነቱ ከውል በላይ በሁለቱ ተወያዮች በኩል መተማመን እንዲፈጠረ ያበረከተው አስተዋፅኦ ስምምነቱ ከስምምነት በላይ መሆኑ አንድ አመላካች ተደርጎ ይወሰዳል።

- የእርሻ እና የኢንዳስትሪ ስራ እንዲነቃቃ የሚያግዝ የማሽነሪና የውጭ ምንዛሪ መሰጠቱ፣ የክልሉ የትምህርትና የጤና ተቋማት መልሶ የመገንባት ሂደት እንዲፋጠን ያስቻለው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውጤት ነው።

- የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፌደራል መንግስት የሚመራውን የብልፅግና ፓርቲ ጨምሮ ሌሎች የፓለቲካ ፓርቲዎች የተካተቱበት አሳታፊ ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም ቢደነግግም ፣ የፌደራል መንግስትና የብልፅግና ፓርቲ በሆደ ሰፊነትና ለሰላም ካለቸው ፍላጎት በሚመነጭ ክልሉ ሃላፊነት ወስዶ በፍጥነት ጊዚያዊ አስተዳደር እንዲመሰረት እድል መሰጠቱ ሊመሰገንና እውቅና ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው።

- ከትግራይ ምዕራባዊና ደቡባዊ ዞኖች የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቄያቸው የመመለስ ጉዳይ መዘግየቱ አለ የሚባል ቢሆንም የተዘነጋ እንዳልሆነ ግን ሊሰመርበት ይገባል። የፌደራል መንግስት ፍላጎት ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ ማድረግ ነው። ይህ አቋሙም ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ውል ማግስት ጥረት ከማድረግ ባሻገር 2015 ዓ.ም ክረምት እንዲመለስ ፍላጎት ነበር። ይሁን እንጂ በአፈፃፀም መዘግየት ምክንያት እስከ አሁን አልተሳካም።

- ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው የመመለስ ጉዳይ ዳግም ወደ ጦርነት በማይመልሰን መልኩ መፈፀም አለበት የሚለው አቅጣጫ ተቀምጦ የፌደራል መከላከያ ሰራዊት ጥያቄዎች በሚነሳባቸው አከባቢዎች ያሉ ታጣቂዎች ትጥቃቸው እንዲፈቱ የማድረግ ስራ እየሰራ ነው። ቢሆንም ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ወደ አከባቢው አልተመለሰም የፌደራል መንግስት አቋም ህዝቡ ወደ ቄየው ተመልሶ የራሱ አመራሮች መርጦ በአመቺ ጊዜ በአከባቢው ህዝብ ውሳኔ እንዲካሄድ ማድረግ ነው።

- የፌደራል መንግስት አቋም ግልፅ ነው ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ይመለሱ ፣ ራሳቸው በመረጡዋቸው መሪዎች ይተዳደሩ ፣ የህዝበ ውሳኔው ጉዳይ ጊዜ ሲደርስ የሚከናወን ይሆናል። አሁንም አቅጣጫው እንዲፈፀም በመጠባበቅ ላይ ነን ፣ ዳግም ግጭት ሳይፈጠር ከዚህ በላይ የተሻለ አማራጭ አለኝ የሚል ካለ ደግሞ የፌደራል መንግስት ለማዳመጥ ዝግጁ ነው። 

- የሻብዕያ ሰራዊት ከኢትዮጵያ መሬት ስለመውጣት ጉዳይ ምን አሉ ? 👉 "  ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት በፊት በበርካታ የትግራይ አከባቢዎች የሻዕብያ ሃይል ገብቶ ነበር ፣ ከስምምነቱ በኋላ እንዲወጣ ተደርጓል ፣ አሁንም የተቀሩ ቦታዎች ካሉ ቦታዎቹ እና ቀበሌዎች ከፌደራልና ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተውጣጣ ቡድን በዝርዝር አጥንቶ እንዲያቀርብና መፍትሄ እንዲሰጠው እየሰራን ነው ሁሉም ልክና መስመር ይይዛል። "

- በትግራይ የተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ በተለመደው አካሄድ ይፈታል የሚል እምነት የለንም ፣  እርግጥ ነው ወደ አከባቢው መድረስ ያለበት የሰብአዊ ድጋፍ እየደረሰ ነው ፣ እየተላከ ያለው ድጋፍ ወደ ተጠቃሚው መድረሱ ማረጋገጥ እንዳለ ሆኖ ፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎችና የፈደራል የመንግስት ተቋማት እገዛ በማድረግ ችግሩ በመፍታት እንዲረባረቡ አቅጣጫ ተቀምጧል።

- በትግራይ የተከሰተው ድርቅ እና ረሃብ በዘላቂነት የሚፈታ ከፌደራልና ከክልሉ የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ በቅርቡ ይፋ ይደረጋል። ይህንን ግብረ ሃይል የሚያቀርበው ጥያቄ ለመመለስ ሁሉም የትግራይ ተወላጆችና መላ ኢትዮጵያውያን ዝግጁ እንዲሆኑ ከወዲሁ ጥሪ እናቀርባለን።

ቃለ ምልልሱን ተከታትሎና ወደ አማርኛ ትርጉም መልሶ ያቀረበው የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው፡፡

#TikvahMekelleFamily

@tikvahethiopia