TIKVAH-ETHIOPIA
" ኑሮውን አልቻለነውም " እጅግ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በየአካባቢያቸው የዳቦና የእንጀራ ዋጋ አሁን ላይ የደረሰበትን ጠቁመዋል። ከአዲስ አበባ ውጭ በክልል ከተሞች አንድ ትንሽ ተብሎ የሚታሰበው ዳቦ ከ5 ብር - 9 ብር ድረስ እንደየአካባቢው የሚሸጥ ሲሆን እንጀራ ከ15-20 ብር ድረስ ይሸጣል ፤ የፀጥታ ችግር ባለባቸው ቀጠናዎች ዋጋው እጅግ ተለዋዋጭ መሆኑን የገለፁት ቤተሰቦቻችን…
#ኢትዮጵያ
ዛሬ ጥዋት ከ #ዳቦ እና #እንጀራ ዋጋ በየጊዜው መጨመር ጋር በተያያዘ እንዲሁም በአጠቃላይ የኑሮው ሁኔታ ምን ያህል እየከበደ እንደሄደ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ሃሳብ ሲያጋሩ ነበር።
ከእነዚህም ቤተሰቦች መካከል በጤና ባለሞያነት የምታገለግል የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እኔ የምናገርበትን አጥቻለሁ ፤ የቲክቫህ ቤተሰቦች እየገፋው ያለሁትን ኑሮ ይስሙኝ ስትል መልዕክቷን እንዲህ ስትል ልካለች።
የጤና ባለሞያዋ የቲክቫህ አባል ፦
" እውነቱን ለመናገር ኑሮ ጫናዉ እኛ የመንግስት ሰራተኞች ላይ እጅጉን ብሷል።
ለምሳሌ ፦ እኔ በአንድ ትልቅ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እሰራሁ ደሞዜ 6193 ብር የግብር ተቀንሶበት 4776 ብር ይደሳል።
Duty ተብሎ ሌሊቱን ሙሉ ከፅኑ ታካሚ ጋር ስለፋ አድሬ ጠዋት የታካሚውን የአዳር ሁኔታ የሚረከበኝ የቀን ተረኛ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው አስረድቼና አስረክቤ ፤ ታዲያ የአደሩን ነገር አትጠይቁኝ መድሀኒት መስጠቱ ፣ በየ1 ሰዓቱ Vital ማንሳቱ ዳይፐር አንሶላ እንዲሁም ቁስል ማጠቡ እሄን ሁሉ አስረክቤ በከተማ አውቶብስ ድፍን ሁለት ሰዓት ወደሚፈጀው የተከራየሁት ቤት እጓዛለሁ።
የምስራበት አካባቢ ላይ እንዳልከራይ የደመወዜን እጥፍ ከየት አምጥቼ እከፍላለሁ ፤ ለዚህ ነው ከከተማ ወጥቼ የተከራየሁት እናማ ከመድከሜ የተነሳ አውቶብስ ላይ ማንቀላፉቱ የማይቀር ነው ፤ ቤት እደርስና የሚበላ ስለማይኖር ከምስራ ብተኛ ብዬ እተኛለሁ።
እደዛ ወገቤ ተሰብሮ ዝዬ ፤ ሌላ ተጨማሪ ስራ እንዳልሰራ ደካክሜ ብቻ ምን አለፋችሁ ፤ ለዚህ ሁሉ ድካም ያቺ ደሞዝ ናት ያለችኝ የDuty ክፍያ ተጨምራ እጄ ላይ የምትደርሰውን ብር ለቤት ክራይ ከፍዬ፣ የትራንስፖርት እና አስቤዛ አውጥቼ የት ትድረስና ? የኑሮው ጫና እኛ ላይ የባሰ ነው። "
.
.
ዛሬ አስተያየታቸውን ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የላኩ ዜጎች በኑሮ ውድነት ክፉኛ እየተፈተኑ መሆኑን በመግለፅ ፤ ገበያው በየጊዜው እየናረ ከዘላቂ መፍትሄ ይልቅ ሰሞነኛ ጉዳይ ሆኖ እያለፈ ነው ብለዋል።
ሚዲያዎችም ትኩረት የሚስብላቸው እና ገንዘብ የሚሰሩበት የፖለቲካ ፍጅትና ጦርነት ፣ ግጭት ስለሆነ ዜጎች እየተፈተኑበት ስላለው የኑሮ ውድነት ጉዳይ አድምተው ለመስራትና የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ እንዲሁም መፍትሄ እንዲሰጥ ለመጋፈጥ ፍላጎት የላቸውም በማለት ወቅሰዋል።
ከድሃ ጎሮሮ ላይ እየነጠቁ የሚበለፅጉ አካላትም ፣ የራሳቸውን የኑሮ ምቾት ብቻ እያሰቡ የሚሯሯጡ ነጋዴዎችም ለአፍታ ለታችኛውና ኑሮ እየፈተነው ላለው ማህበረሰብ እንዲያስቡ ጠየቀዋል።
መንግሥትም ጆሮ ሰጥቶ የሚሰማ ከሆነ ዜጎች በኑሮ ውድነት በተለይም ደግሞ በምግብ ነክ ነገሮች ላይ በየጊዜው በሚደረገው ጭማሪ ዜጎች እየተሰቃዩነውና መፍትሄ ይፈልግ ብለዋል።
Via @tikvahethiopiaBOT
@tikvahethiopia