TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወደ 100 የሚጠጉ የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት ተገድለዋል " ወደ ኢትዮጵያ ዘልቆ ጥቃት የሰነዘረው የአልሻባብ የሽብር ቡድን በርካታ ታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። ይሄ የሽብር ቡድን በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከመታቱ በፊት በንብረት እና ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ተነግሯል። አልሸባብ ፤ ከሶማሊያ ጋር ወደ ሚዋሰነው ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን በመግባት ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ በሶማሌ ልዩ ኃይል…
#ይፋዊ_መግለጫ !

" የአልሸባብ የሽብር ቡድን ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሷል " - የሶማሌ ክልል ፀጥታ ም/ቤት

ዛሬ ምሽት የሶማሌ ክልል ፀጥታ ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫው ከ4 ቀናት በፊት "አቶ" በሚባለው ቦታ ወደ ሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን አልሸባብ የሽብር ቡድን ታጣቂ መግባቱን አመልክቷል።

የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች " ሁልሁል " በሚባል ንዑስ ቀበሌ ከተከበቡ በኋላ ሙሉ ለሙሉ ለወሬ ነጋሪ ሳይተርፍ ተደምስሰዋል ሲል አሳውቋል።

የፀጥታ ም/ቤቱ አልሸባብ በኤልከሬ ወረዳ አልፎ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመግባት በኢትዮጵያ የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው " ሸኔ " ቡድን ጋር ለመገናኘት አልሞ እንደነበር ገልጿል።

አልሸባብ ወዳሰበው ቦታ ሳይደርስ የያዛቸውን 13 ተሽከርካሪዎች ተቃጥለዋል ያለው የክልሉ ፀጥታ ም/ቤት " ይዞት የገባው ትጥቅ እና ስንቅ ተማርኳል " ብሏል።

ለ3 ቀናት ያህል በተካሄደው ኦፕሬሽን ከ100 በላይ የአሸባሪው አልሸባብ ቡድን አባላት መገደላቸውን የክልሉ ፀጥታ ም/ቤት አሳውቋል።

ለኦፕሬሽኑ መሳካት የሶማሌ ክልል ህዝብ ለጀግናው የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል የተለያዩ ምግቦች፣ በርካታ የቁም እንስሳቶች፣ መጠጦች ፣አልሰባሳት እንዲሁም ደም በመለገስ ከልዩ ሀይሉ ጎን መቆማቸው የተገለፀ ሲሆን የክልሉ ህዝብ ላደረገው ድጋፍና እገዛ የፀጥታ ምክር ቤቱ ምስጋና ማቅረቡን ከክልሉ ኮሚኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር  ሀገር አቀፍ ፈተናዎችን መቼ ለመስጠት እቅድ ይዟል ? ቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰውና በትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ፣ ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለሁሉም የክልል ትምህርት ቢሮዎች የተሰራጨ አንድ ደብዳቤ የዚህ ዓመት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ሊሰጡ #የታቀደበትን ጊዜ ያመለክታል። የደብዳቤውን ትክክለኝነት ቲክቫህ…
#MoE #ይፋዊ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ #ይፋ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE #ይፋዊ የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ጊዜ #ይፋ አድርጓል። ሚኒስቴሩ ፤ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ #በመንግስት_ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል ብሏል። ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ…
#MoE #ይፋዊ

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ #በይፋ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ይሰጣል ብሏል።

የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ፈተናውን እንደሚወስዱም ገልጿል።

በ2014 ዓ.ም የህግ መውጫ ፈተና ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ ያላስመዘገቡ ተማሪዎችም በዚሁ ጊዜ ፈተናውን የመንግስት ዩኒቨርሲቲ የመፈተኛ ማዕከላት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተናን ለመሥጠት የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያደርግ መቆየቱ አስታውሷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ይፋዊ

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜን በይፋ አሳውቋል።  

በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በልዩ ሁኔታ በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ  ተማሪዎች ፈተና ተዘጋጅቶ እንዲላክና አጠቃላይ ሂደቱ  እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ተቀምጧል።

ፈተናውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተሰጠው ትምህርት መሠረት ከማዕከል በጋራ ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ  ተብሏል።

በዚህም መሰረት በሴሚስተሩ በተሰጠው ትምህርት የተቋማት የውስጥ ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና ውጤት 50 ከመቶ  ይይዛል ተብሏል።

ተማሪዎችም በ2016 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ ሆነው ለመገኘት የሁለቱ ድምር አማካይ 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ፈተናውን በማስተዳደርና ውጤት በመግለጽ በ2016 የፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን  ለይተው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ የ2016 የትምህርት ካሌንደር የተስተካከለ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ  ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሪሜዲያል ትምህርት ሚኒስቴር ከአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና ጋር በተያያዘ ምን ውሳኔ አስተላለፈ ? ትምህርት ሚኒስቴር የአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፈተና አሰጣጥን በተመለከ ትላንት ሰኞ ምሽት ከፕሬዚደንቶችና የተቋማት ሃላፊዎች ጋር ከተወያየ በኃላ ከፈተናው ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማስተላለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚመለከተው አካል ለማወቅ ችሏል። በዚሁ የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ የሬሜዲያል ፈተና አሰጣጥ…
#ይፋዊ

የትላንት የሬሜዲያ ፈተናዎች ተሰርዘዋል።

በሬሜዲያ ፈተና ሂደት ወቅት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔዎች አሳልፏል።

የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ረሜዲያል ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ትናንት ሰኔ 26/2015 ዓ.ም በዩኒቨርስቲዎች መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ በፈተና ሂደት በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1) ሰኔ 26/2015 የተሰጡት የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች ተሰርዘው ተማሪዎች በቀሩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ እንዲመዘኑ።

2) ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት የታቀደው ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ።

3) በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት ይሰጣል።

(ትምህርት ሚኒስቴር)

NB. ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ዛሬ ይፋ ባደረገው መረጃ ትላንት ፈተናው መሰጠት ከተጀመረ በኃላ ተፈጥረዋል ያላቸውን ችግሮችን በዝርዝር አላሳወቀም።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia