TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር አብርሃም በላይ ምን አሉ ? የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በዛሬው እለት የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተረጋገጠ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተለልፈዋል። በመልዕክታቸው ፤ " የአሸንዳ በዓል ለትግራይና ትግራዎት  ልዩ ትርጉም ያለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ በአላችን ነው። " ብለዋል። " የዚህ አመት የአሸንዳ በዓል ህዝባችን ከደረሰበት ጉዳት ገና ባላገገመበት…
" በሚኒስትሩ የተላለፈው መልዕክት የአማራ ሕዝብ ከምድረ-ገፅ ፈፅሞ ሳይጠፋ የማይፈፀም የቀን ቅዥት ነው " - የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን

በትግራይ ጦርነት ከጀመረ በኃላ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን አስተዳደርን መዋቅርን በማፍረስ " የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን " በሚል የተቋቋመውና በአማራ ክልል ስር የሚገኘው አስተዳደር ከሰሞኑን የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ላወጡት መልዕክት ምላሽ የሚሰጥ መግለጫ አወጣ።

በዚሁ መግለጫው ፤ የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት አሳዛኝ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ነው ብሏል።

መክላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ የአሸንዳ በዓልን አስመልክቶ በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት መልዕክት የአማራ ክልል ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ የተላለፈ አደገኛ መልዕክት ነው ሲል ገልጿል።

" ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግስት ኃላፊነት ይዘው ሳለ ፍፁም ለአንድ ወገን ያደላ መልዕክት ማስተላለፋቸው ኃላፊነት የጎደለውና የአማራ ክልልን ወደለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ የተላለፈ መልዕክት ነው " ሲል ገልጾታል።

መልዕክቱ ፤ " የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር አማራ ክልልን ወደለየለት ብጥብጥና ግጭት እንዲያመራ ሆን ተብሎ የተረጨ መርዘኛ መልዕክት እንደሆነ እናምናለን " ያለው መግለጫው "  " ሚኒስትሩ ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ኃላፊነት ሳይኖራቸው እንዱን አካል ህገ-ወጥ ሌላውን ደግሞ ሕጋዊ ብሎ መፈረጅ ከፌዴራል ወርደው ለእንድ ክልል ለተወለዱበት ብሔር/ መወገን አመላካች ሆኖ አግኝተነዋል። " ብሏል።

" የአማራ ሕዝብን የእውነትና የፍትህ ጥያቄ የካደ ነው፡፡ " ሲልም አክሏል።

መግለጫው ፤ " በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተቋቋመው መንግስታዊ መዋቅር በሰዎች በበጎፍቃድ የተቸረው ሳይሆን ለዘመናት በተከፈለው ውድ መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ የዘነጉት ይመስላል " ብሏል።

ሚኒስትሩ ፌዴራሉ መንግስት ከሰጣቸው ኃላፊነት ውጪ ተገቢ ያልሆነ መልዕክት በማስተላለፋቸው የአማራን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል ሲልም ገልጿል።

" የተላለፈው መልዕክት የአማራ ሕዝብ ከምድረ-ገፅ ፈፅሞ ሳይጠፋ የማይፈፀም የቀን ቅዥት ነው፡፡ " ብሏል።

የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ከሰሞኑን ኣሸንዳን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ በሚያከራክሩ የትግራይ ቦታዎች ነዋሪው የሚያነሳው ጥያቄ ካለው በህገ-መንግስት ብቻ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።

" ህዝቡ በአጭር ጊዜ ወደ ቄየው ተመልሶ ህገ-መንግስታዊ መብቱ በሚያረጋግጥ መንገድ አስተዳደሩ ራሱ እንዲመሰርት ይደረጋል " ያሉት መከላከያ ሚኒስትሩ " በአከባቢዎቹ በነበረው ሁኔታ በመጠቀም ተፈጥሮ የቆየው አስተዳደር #እንዲፈርስና ከፌደራል የፀጥታ ሃይሎች ውጭ የታጠቀ ሃይል አንዳይኖር ፣ ይህ እንዲፈፀም የፌደራል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃላፊነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ትእዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ከዚህ ውጭ ከባለቤቱ በላይ ባለቤት ለመሆን የሚዳዳ ፤ ከባለ ጉዳይ በላይ ጉዳይ አለኝ የሚል ፤ ከህግና ስርአት ውጭ በጉልበት ለመንቀሳቀስ የሚሰራ አካል ካለ የፌደራል መንግስት በጀመረው መንገድ ህግና ህገ-መንግስታዊ ሰርአቱ እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ አሳስበዋል።

(ለመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ መልዕክት የተሰጠው ምላሽ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው።

የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው። 

የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት እየተዘናኑ ሳለ ከቤቱ ውጭ ወደ መጠጥ ቤቱ የተወረወረው ቦምብ የአራት ስዎች ህይወት ወድያው ሲቀጠፍ ፤ የቤቱ ሰራተኞች የሚገኙባቸው በርካቶች ቆስለዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ቆየት ብሎ ከሆስፒታል ምንጭ ባገኘው መረጃ ተጨማሪ አንድ ሰው ህይወቱ በማለፉ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 5 መሆኑን ተረድቷል።

መቐለን ጭምሮ የበርካታ የትግራይ ከተሞች የፀጥታ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ፤ ቲክቫህ የመቐለ ከንቲባ አቶ ይትባረክ አምሃ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።

መቐለ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ መጠጥ ቤቶች መግብያ በር ' ተተኳሽና ስለታም ነገሮች ይዞ መግባት የተከለከለ ነው ' የሚሉ ፅሁፎች ማንበብ ከጦርነቱ በኋላ የተለመደ እንደሆነ የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ። ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው። የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው።  የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት…
#Mekelle

የመቐለ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ትላንት ለሊት 8 ሰዓት ላይ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " በሚባለው መጥጥ ቤት ቦንብ የተወረወረው " በቀድሞ ተሰናባች ታጋይ " በነበረ ግለሰብ መሆኑን ታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው እስካሁን አልተያዘም።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ ፤ " ከአሸንዳ በዓል ጋር በተያያዘ በከተማዋ ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ሲደረግ ቆይቷል " ብለዋል።

" በበዓሉ መዝጊያ ቀን ትናንት ግን በከተማዋ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ አሳዛኙ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሞ ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጥቃቱን የፈፀመው ግለሰብ ማንነቱ ተለይቷል " ያሉት ኮማንደር ወልዳይ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የተወረወረው ኤፍዋን የተባለ የእጅ ቦንብ መሆኑን ፖሊስ አረግጧል። የጥቃቱ አላማም " የግለሰቦች ጠብ " መሆኑን አስረድቷል።

ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በበኩሉ 20 በቦንብ ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ መቀበሉን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ትላንት ለሊት በተወረወረው ቦንብ 5 ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶችም መቁሰላቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆስፒታል ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
🪙የቁጠባ ትንሽ የለውም በቴሌብር ሳንዱቅ ለነገ ጥሪት ያኑሩ

🛍ገበያ ሲወጡ እጅ ቢያጥርዎ ቴሌብር እንደኪሴ የጎደለውን ሞልቶ ያሰቡትን ያሳካል

🫰ለህልምዎ ስኬት አንስተኛ ብድር ሲፈልጉ ቴሌብር መላ ዋስ፣ ምስክር፣ እወቁልኝ ሳያበዛ ገበና ሸፍኖ ያበድርዎታል

💰ደሞዝዎ በቴሌብር ሲከፈልዎ ደግሞ በመዳረሻ የደሞዝዎን 30% ብድር በፈጣን ቀላል ምቹ እና አስተማማኙ ቴሌብር ያገኛሉ!

#የፋይናንስ_አገልግሎት_ለሁሉም
#አብረንዎት_ነን
ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ለአንድ ቀን ይቆያል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ነው ተብሏል። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊና የኮማንድፖስቱ አባል አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለምክር ቤቱ ንግግር አሰምተዋል። በዚህም ንግግራቸው ፤ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት " ድህረ ጦርነት የፈጠረው ልዩነት ነው " ብለዋል።…
#NewsAlert

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡

" በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ ብሆንም የምንችለውን ሁሉ ግን ሰጥቻለሁ ፤ጥያቄየንም ፓርቲዬ ተቀብሎኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤትም የክልሉን ፕሬዜዳንት የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ መቀበሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል። ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡ " በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ…
#NewsAlert

በአማራ ክልል አዲስ ፕሬዜዳንት ተሾመ።

ባለፉት ዓመታት በርካታ ፕሬዜዳንቶች የተፈራረቁበት አማራ ክልል ዛሬ አዲስ አስተዳዳሪ ተሹሞለታል።

አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀብሎ በምትካቸው አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ፕሬዜዳንት በማድረግ ሹሟል፡፡

አቶ አረጋ ከበደ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

የት የት ስፍራዎች አገልግለዋል ? የትምህርት ደረጃቸውስ ?

- መጀመሪያ ዲግሪያቸውን በልማት አስተዳደር ሰርተዋል።
- የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ረዳት የህዝብ ተሳትፎ አማካሪ ነበሩ።
- የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ነበሩ።
- የክልሉን ሚሊሺያ ጽህፈት ቤት በኃላፊነት ለአንድ ዓመት መርተዋል።
- የክልሉ ቴክኒክ ሙያ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።
- ወደ ክልል ኃላፊነት ከመምጣታቸው በፊት፤ የምስራቅ ጎጃም ዞንን በምክትል አስተዳዳሪ እና በዋና አስተዳዳሪነት መርተዋል።
- እስከ ዛሬ ድረስ የአማራ ክልል የስራ ፈጠራና ስልጠና ቢሮ ኃላፊ ነበሩ።

ፎቶ፦ AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በአማራ ክልል አዲስ ፕሬዜዳንት ተሾመ። ባለፉት ዓመታት በርካታ ፕሬዜዳንቶች የተፈራረቁበት አማራ ክልል ዛሬ አዲስ አስተዳዳሪ ተሹሞለታል። አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል። የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የመልቀቂያ…
#Amhara

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ብቻ በአማራ ክልል ከ5 በላይ ርዕሰ መስተዳደሮች ክልሉን መርተዋል።

እነማን ናቸው ?

- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
- ዶ/ር አምባቸው መኮንን (በህይወት የሉም)
- አቶ ላቀ አያሌው (በጊዜያዊነት ያስተዳደሩ)
- አቶ ተመስገን ጥሩነህ
- አቶ አገኘሁ ተሻገር
- ዶ/ር ይልቃል ከፋለ

በዛሬው ዕለት ነሃሴ 19 ቀን 2015 ዓ/ም ደግሞ አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው በክልሉ ምክር ቤት ተሹመዋል።

አማራ ክልል ፤ በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች አንፃር ጋር ሲተያይ እጅግ በርካታ ርዕሰ መስተዳደሮች የተፈራረቁበት ክልል ነው። ይህም ሁኔታ በክልሉ ውስጥ ያለውን ያልተረጋጋ የፖለቲካ ሁኔታ በግልፅ የሚያሳይ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በአማራ ክልል አዲስ ፕሬዜዳንት ተሾመ። ባለፉት ዓመታት በርካታ ፕሬዜዳንቶች የተፈራረቁበት አማራ ክልል ዛሬ አዲስ አስተዳዳሪ ተሹሞለታል። አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ሆነው መሾማቸው ተገልጿል። የአማራ ክልል ምክር ቤት በባህር ዳር እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፤ 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፤ 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የቀድሞው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የመልቀቂያ…
#Update

አቶ አብዱ ሁሴን የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ሆነው ተሹመዋል።

ዶክተር አህመዲን መሐመድ  ደግሞ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኅላፊ  ሆነው መሾማቸው ተን

ከዚህ በተጨማሪ የባህር ዳር ከንቲባው ዶክተር ድረስ ሳህሉ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ተሰምቷል።

በአዲሱ የክልሉ አስተዳዳሪ አቅራቢነት በምክር ቤት የተሰጡ ሹመቶች ሙሉ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia