TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አስቸኳይ

የሳዑዲ አረቢያ የፀጥታ አስከባሪ አካላት በሳዑዲ የተለያዩ ከተሞች የመኖርያ ፈቃድ ባላቸውም ይሁን በሌላቸው ነዋሪዎች ላይ የፍተሻና የአፈሳ እርምጃ እየወሰዱ እንደሆነና ዜጎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክት ተላልፎ ነበር።

የሳዑዲ ፀጥታ ኃይሎች በሰሩት ኦፕሬሽን ተይዘው በሹሜሲ የማቆያ ጣብያ የሚገኙ ዜጎች ከፍተኛ የውሃ የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።

በመሆኑም:-

1ኛ. ከ10 ቀን እስከ 3 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ህፃናት የሚሆን ወተት

2ኛ. ከ1 ቁጥር እስከ 5 ቁጥር የሆኑ የህፃናት ዳይፐር/ሃፋዛ/

3ኛ. ለታዳጊ ህፃናት እና ለአዋቂዎች የሚሆኑ ደረቅ ምግቦች

4ኛ. ለሴቶች እና ለሕፃናት የሚሆኑ የመፀዳጃ ቁሳቁሶች በተለይ ዋይፕ እና ሞዴስ

5ኛ. የሚጠጣ ውሃ እጥረት ያጋጠመ በመሆኑ ዜጎቻችን ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠዋል።

ዕርዳታ ማድረግ የምትፈልጉ ግለሰቦች/ አደረጃጀቶች በጄዳ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ኮሚዩኒቲ) የስራ ኃላፊነቱን ወስዶ እንቅስቃሴ የጀመረ በመሆኑ ዕርዳታችሁን በኮሚኒቲ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ማድረስ እንደሚቻል በጄዳ የሚገኘው ቆንስላ ፅ/ቤት ዛሬ ማምሻውን ገልጿል።

ይህ መልዕክት የደረሳችሁ ጅዳ አካባቢ የምትገኙ የቲክቫህ አባላት በመሉ የምትችሉትን ሁሉ ታደርጉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

@tikvahethiopia
#ችሎት

3 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ክስ መሰረተ።

ዐቃቤ ህግ የ #አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጁን ተገን በማድረግ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል የሙስና ወንጀል የፈፀሙ 3 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ላይ ክስ መስርቷል።

ክስ የተመሰረተባቸው ፦
1ኛ ተከሳሽ ኮንስታብል ተሰማ መለሰ በዲስፕሊን ጥፋት ከስራ የተሰናበተ
2ኛ ተከሳሽ ዋ/ሳጅን ፈንቴ ፈይሳ የፖሊስ መኪና ሾፌር
3ኛ ተከሳሽ ረ/ሳጅን ተስፋዬ በላይ የፖሊስ መኪና ተወርዋሪ ናቸው።

ተከሳሾች ምንድነው የፈፀሙት ?

ተከሳሾቹ በጥቅም በመመሳጠር ህዳር 03 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ ከ12፡30 - 1፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ በኮልፌ ቀራንዩ ክ/ከተማ ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ የሰሌዳ ቁጥር 0228 በሆነችና 2ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክራት የፖሊስ መኪና የግል ተበዳይ አቶ ዘሪሁን ሀይሉ ወደሚኖርበት መኖሪያ ቤት ይሄዳሉ።

1ኛ ተከሳሽ የፖሊስ አባል በመምሰል 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ደግሞ የፖሊስ አባልነታቸውን ሽፋን በማድረግ ምርመራ የማከናወን እና የግል ተበዳይን የመያዝ የስራ ድርሻ ሳይኖራቸው እና ምንም አይነት ትዕዛዝ ሳይሰጣቸው 2ኛ ተከሳሽ የግል ተበዳይን “በወቅታዊ ጉዳይ ትፈለጋለህ” በማለት 1ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች ወደ ግል ተበዳይ መኪና በመግባት 1ኛ ተከሳሽ ተበዳይን ያለምንም ጥያቄ 6 ወር ትታሰራለህ እኛ እንድንተባበርህ ከፈለክ 200 ሺ ብር ስጠን ብለው ይጠይቁታል።

በመጨረሻም 120 ሺ ብር እንዲሰጣቸው ተስማምተው 60 ሺ ብሩን 1ኛ ተከሳሽ ወደሚጠቀምበት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሞባይል ባንኪንግ ገቢ እንዲያርግ በማድረግ እና 10 ሺህ ብር በጥሬው በአንደኛ ተከሳሽ አማካኝነት ተቀብለው ከተከፋፈሉ በኋላ ቀሪውን ገንዘብ ሊቀበሉ ሲሉ በማህበረሰቡ እና በህግ አስከባሪ አካላት ተይዘዋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል። 

ዐቃቤ ህግ ከዚህ በፊት ታህሳስ 4/2014 ዓ.ም ተመሳሳይ ወንጀል በፈፀሙ አራት የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ክስ መስርቶ ተከሳሾች ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ መልስ በመስጠት የችሎቱን ብይን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Ministry-of-Justice-12-29
#ATTENTION 📣

ድንበር የለሽ ዶክተሮች (MSF) በአፋር ክልል እየጨመረ የመጣው የምግብ እጥረት ቀውስ ስጋት እንዳጫረበት ገልጿል።

ድርጅቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መሠረታዊ የሚባሉ የጤና ማዕከላትን እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማያገኙበት ሁኔታ ነው የሚኖሩት ብሏል።

በተጨማሪም በርካታ ሕፃናት በከፋ የምግብ እጥረት ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲል አመልክቷል።

የዘንድሮው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር አራት እጥፍ ብልጫ ባለው መልኩ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ሕፃናትን መመልከቱን ገልጿል።

ከነዚህ ውስጥ 35 ሕፃናት የሞቱ ሲሆን አብዛኞቹም ወደ ሆስፒታል በገቡ በ48 ሰዓታት ውስጥ ነው ሕይወታቸው ያለፈው።

በአፋር ውስጥ ካሉ የጤና ማዕከላት አብዛኞቹ አገልግሎት ላይ እንዳልሆኑ ያስታወቀው MSF በሥራ ላይ ያሉት 20 በመቶ ብቻ  ናቸው ብሏል።

በክልሉ እየተከሰተ ያለው ቀውስ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሞ የረድኤት ማኅበረሰቡ #አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ እንደሆነ አሳስቧል።

እንደን MSF ሪፖርት በጦርነት ክፉኛ የተጎዳችው የትግራይ ክልልን ወደሚያዋስነው የአፋር ክልል የተፈጠረውን ግጭት በመፍራት በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ክልሉ ጎርፈዋል።

በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን የተወሰኑት ከአንድ ወር በላይ በእግር ተጉዘው አፋር ደርሰዋል።

ተፈናቃዮቹን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎች በአፋር ለከፍተኛ ስቃይ የተጋለጡ ሲሆን MSF አፋጣኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግም ማሳሳቡን ቢቢሲ ድርጅቱን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#አስቸኳይ

ሰኔ 4 ቀን 2014 ዓ/ም በአማራ ክልል፣ ሰሜን ሜጫ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

በሰሜን ሜጫ ወረዳ ቆለላ ቀበሌ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ፦
- ጋፈራ፣
- አውጣ
- ባችማ
- ተክለድብ በተባሉ ቀበሌዎች 1409 በሚደርሱ የአባወራ ቤቶች ላይ ከባድና ቀላል የንብረት ጉዳት ደርሷል።

በእስሳት እና አትክልት፣ ፍራፍሬ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ ለተጎዱ 5 ቀበሌዎች #አስቸኳይ_ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

አጠቃላይ የደረሰው ጉዳት ዝርዝር በዚህ ተያይዟል ፦ https://telegra.ph/North-Mecha-06-13

#ሰሜን_ሜጫ_ወረዳ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን የሚገኙ 4 ወረዳዎች እና 1 ከተማ አስተዳደር የ "ክላስተር" አደረጃጀትን በየም/ቤቶቻቸው ባካሄዱት አስቸኳይ ጉባኤ አፅድቀዋል። የመስቃን እና ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እና የቡታጅራ ከተማ ማዕከሉን ቡታጅራ ያደረገ አዲስ ዞን ለመመስረት በተጨማሪነት የወሰኑ ሲሆን የማረቆ እና ቀቤና ወረዳዎች ደግሞ ወደ ልዩ ወረዳነት ለማደግ ውሳኔ አሳልፈዋል። የማረቆ፣ ቀቤና፣…
የደቡብ ክልል ዕጣፋንታ ምን ይሆን ?

መንግስት ክልሉ በክላስተር ተከፍሎ በአጎራባች ያሉ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች አንድ ላይ በመሆን ሁለት አዲስ ክልል እንዲመሰርቱ አቅጣጫ አስቀምጧል።

ይህን አቅጣጫ ከተትሎም የዞን እና ልዩ ወረዳ ም/ቤቶች በየም/ቤቶቻቸው በመሰባሰብ በቀረቡላቸው የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ውሳኔ አሳልፈዋል፤ ውሳኔያቸውንም ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት አስገብተዋል።

አዎ! በመንግስት አቅጣጫ መሰረት በአንድ ላይ ሆነን በአዲስ 2 ክልል እንደራጃለን ብለው በምክር ቤት ያፀደቁ አጠቃላይ 10 ዞኖች እና 6 ልዩ ወረዳዎች ናቸው።

ከእነዚህ መካከል ግን በብቸኝነት የጉራጌ ዞን " ክላስተር አልደግፍም ፤ የህዝቡም ፍላጎት አይደለም ፤ እኛ የምንፈልገው በክልል መደራጀት ነው ፤ ይህም በህጋዊ መንገድ ምላሽ ሊሰጥበት ይገባል " ሲል የክላስተር አደረጃጀትን በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ ውድቅ አድርጎታል።

ከዚህ በኃላ ግን በዛው በዞኑ ውስጥ ያሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት በዞናቸው ም/ ቤት በአብላጫ ድምፅ የተላለፈውን ውሳኔ እንደማይቀበሉ በመግለፅ " ክላስተር እንደግፋለን " የሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

ውሳኔ ያሳለፉ (ትላንት) የማረቆ፣ ቀቤና፣ የመስቃን፣ ምስራቅ መስቃን ወረዳዎች እንዲሁም የቡታጅራ ከተማ ም/ ቤቶች ሲሆኑ #ዛሬ ደግሞ የቡኢ ከተማ፣ የደቡብ ሶዶ ወረዳ እና የሶዶ ወረዳ ምክር ቤቶች "ክላስተር እንደግፋለን " በሚል ውሳኔ አሳልፈዋል።

" ፌዴሬሽን ም/ቤት ስብሰባ ይቀመጣል "

የፌዴሬሽን ም/ቤት በ " ደቡብ ክልል " አደረጃጀት ጉዳይ ላይ ነሃሴ 12 #አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ እና ከክልሉ ጋር ተያይዞ የሚወስናቸው ውሳኔዎች እንደሚኖሩ የም/ቤቱን ህዝብ ግንኙነት ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#አስቸኳይ

በአሁን ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጨማሪ አሃዶችን የመፍጠር ቴክኖሎጂዎች (Blockchain technologies) ላይ የተመሰረቱ የክሪፕቶ ምርቶችና አገልግሎቶች ሁኔታ በመስፋፋት እና ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ የክሪፕቶግራፊ ውጤት/ምርትንና አገልግሎትን በተመለከተ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 808/06 አንቀጽ 6 (9) በተሰጠው ስልጣን መሰረት " የክሪፕቶ ምርትና ዝውውርን የመቆጣጠር እና አስፈላጊውን መስፈርት ማውጣትና የአጠቃቀም ስርዓት መዘርጋት " ሃላፊነት ተሰጥቶታል።

በዚህም ዘርፉን በአግባቡ ለመግራት ይቻል ዘንድ ፦የክሪፕቶ ምርት፤ አገልግሎት፣ ዝውውርና ማይኒንግን በተመለከተ ስራዎችን የሚያከናውኑ እና መምዝገብ ለሚፈልጉ ወይም ለመመዝገብ ጠይቀው ሂደት ላይ ያሉ በአስተዳድሩ ድረ-ገጽ በተቀመጠው ቅጽ መስረት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲመዘገቡ አስተዳደሩ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

ይህንን ተግባራዊ በማያደርጉ እና በዚህ ስራ ያለምዝገባ ተሰማርተው በሚገኙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቋል።

ለተጨማሪ መረጃ የአስተዳደሩን ድረ-ገጽ www.insa.gov.et/Crypto ወይም https://crypto.insa.gov.et መጎብኘት ይቻላል ተብሏል።

@tikvahethiopia
#DrAbrhamBelay

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ ፤ በትግራይ ያጋጠመውን ቀውስ አይነተኛ የመፍቻ መንገድ፣ " ህዝቡ በተደራጀ አዲስ የሀሳብ ጥላ የመፍትሔው ባለቤት እና አካል ለመሆን ሲወስን #ብቻ የሚረጋገጥ ነው " አሉ።

የመከላከያው ሚኒስትር ይህንን ያሉት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተረጋገጠ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት ፅሁፍ ነው።

" ጊዜው ያለፈበት የፖለቲካ ኃይልም ሆነ አስተሳስብ፣ ከትግራይ ህዝብ ኑባሬ ደህንነት፣ ሰላምና መረጋጋት ከቶ ሊበልጥ አይገባም " ያሉት ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ፤ " በመላው ትግራይ እና የተለያዩ አከባቢዎች የምትገኙ የትግራይ ተወላጆች የመፍትሔ ሀሳቦች እንዲንሸራሸሩ ፣ የተደራጀ #አስቸኳይ ህዝባዊ ስክነትና ምክክር እንዲሰፍን እንድንዘጋጅ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#አስቸኳይ

አስቸኳይ የነፍስ አድን እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ።

የቡርጂ ልዩ ወረዳ ተከስቶ ባለው ድርቅ ምክንያት በመኖ እጥረት 4496 ዳልጋ/የቀንድ ከብቶች እና በርካታ የጋማ ከብቶች እንዲሁም ፍየልና በጎች እየሞቱ መሆኑ ተገልጿል።

አሁን ላይ በህይወት ያሉት እንስሳትም ከተኙበት መነሳት የማይችሉ የደከሙ እንደሆኑ ተገልጿል።

በወረዳው ዓመቱን ሙሉ ይፈሱ የነበሩ ወንዞች በመድረቃቸው እንስሳቱ ውሃ ፍለጋ ረጅም ኪሎ ሜትር ተጉዘው ከጠጡ በኋላ ደክመው መመለስ ሳይችሉ በዚያው በየመንገዱ እየሞቱ እንዳሉም ተነግሯራ።

በበሬ አርሶ የሚኖረው ህብረተሠብ በሬዎቹን በሞት በማጣቱ ለከፋ ረሀብ መጋለጡ ተጠቁሟል።

ክልቾ በተባለችው ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ይርጋለም ጮታ ከ30 የዳልጋ ከብቶች ውስጥ 23ቱ ሞተው 7ቱ በህይወት ያሉ ቢሆንም እነሱም ደክመው ለመሞት መቃረባቸውን አመልክተዋል።

እኚሁ አርሶ አደር ከነቤተሠባቸው በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ሌሎችም አርሶ አደሮች ያሏቸውን ከብቶች በድርቁ እያጡ በመሆኑ ለአስከፊ ድህነትና ረሃብ እየተጋለጡ መሆኑን አስረድተዋል።

በወረዳው በህይወት ያሉትን እንስሳት ሽፈራውና ሌሎችም ቅጠሎች እየተቆረጠ የነፍስ ማቆያ ቢሆንም ከዚህ በኋላ ግን አስቸኳይ የመኖ እና የመድኃኒት ድጋፍ ካልተደረገ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ወረዳው ገልጿል።

ሁሉም አካላት በድርቁ ለተጎዳው የቡርጂ ህዝብ የቻለውን ያህል እርዳታ በማድረግ የህይወት አድን ስራ እንዲሰራ ይፋዊ ጥሪ ከወረዳው ቀርቧል።

መረጃው ከቡርጂ ልዩ ወረዳ የተገኘ ነው።

@tikvahethiopia
#EOTC

ቅዱስ ሲኖዶስ የፊታችን ረቡዕ #አስቸኳይ ጉባኤ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ዛሬ አሳውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ጥሪ ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" #አስቸኳይ የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና መሥሪያ ቤት እንዲሁም በ11ዱ የክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች ሲሰጥ የነበረው “ አስቸኳይ ” የፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው መቋረጡን የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ለምን ተቋረጠ ?

አገልግሎቱ የተቋረጠው #ከአቅም_በላይ የባለ ጉዳይ ፍሰት ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ መጠነ ሰፊ #የሠነድ_ማጭበርበሮች በመስተዋላቸው ነው።

ከዚህም በተጨማሪ ተገልጋዮች ሊገለገሉ ሌሊት ላይ በሚመጡበት ወቅት በተለያዩ ህገ-ወጥ ግለሰቦች የሚደርስባቸው እንግልትና ጉዳት በአገልግሎት አሰጣጥና በተገልጋዩ ላይ ተግዳሮት በመፍጠሩ ነው።

ስለሆነም የማስተናገድ አቅም እና ሌሎች ክፍተቶች እስከሚስተካከሉ ድረስ ይሰጥ የነበረው የ “ አስቸኳይ ” ፓስፖርት አገልግሎት ለጊዜው ተቋርጧል።

አስቸኳይ ጉዞ ያላቸው በምን ይስተናገዳሉ ?

ቀድሞ ይሰራበት በነበረው አሰራር መሰረት #አስቸኳይ_ጉዞ ያላቸው አገልግሎት ጠያቂዎች ማስረጃዎቻቸውን አቅርበው #በዋና_መስሪያ ቤት ብቻ ከመጋቢት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ይስተናገዳሉ።

ማሳሰቢያ ፦ ተገልጋዮች ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከህገወጥ ደላሎች እንዲጠነቀቁ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የመደበኛ ፓስፖርትን በተመለከተስ ?

የመደበኛ ፓስፖርት ተገልጋዮች ቀድሞ በነበረው ሂደት መስተናገድ #ይቀጥላሉ

ምንጭ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

@tikvahethiopia
#ትግራይ #እስልምና
 
ለዓመታት የተቋረጠው ግንኙነት እንዲቀጥል ስምምነት ላይ መደረሱ ተነገረ።

በአስከፊውና ደም አፋሳሽ ጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮችና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግንኙነት የቀረበውን ይፋዊ ይቅርታ ተከትሎ ግንኙነቱ ወደ ቀድመው እንዲመለስ መወሰኑ ታውቋል።

የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት 2014 ዓ/ም ላይ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተለይቶ ራሱን ችሎ እንደተቋቋመ በይፋ አስታውቆ ነበር።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ጦርነቱ መቆሙን ተከትሎ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የትግራይ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ግንኙነት ወደነበረበት እንዲመለስ ጥረት ሲደረግ ቢቆይም አልተሳካም ነበር።

ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም የትግራይ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በመቐለ ከተማ ባካሄደው #አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አቀረበ ባለው የይቅርታ ደብዳቤ ላይ ከተወያየ በኃላ በሙሉ ድምፅ በመቀበል ከሶስት አመታት በላይ የተቋረጠው ግንኙነት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጿል።

በደም አፋሳሹ እና አስከፊው የትግራይ ጦርነት ምክንያት በተፈጠረ መቃቃርና አለመጣጣም የትግራይ የኦርቶዶክስ የሃይማኖት አባቶች ከኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስትያን ተለይተው " መንበረ ሰላማ " በሚል የራሳቸው ቤተክህነት ማቋቋማቸው ይታወቃል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ሲሆን በነገው ዕለት ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ ይሆናል።
                                       
@tikvahethiopia            
#አስቸኳይ

“ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን #ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ ” - የታጋች እናት

በሊቢያ ደላሎች የታገተው የሀዋሳው ተወላጅ ኢትዮጵያዊ ወጣት ጌድዮ ሳሙኤል፣ በአጋቾቹ ልዩ ልዩ ድብደባዎች እየተፈጸሙበት እንደሚገኝ ፣ አጋቾቹ ወጣቱን ለመልቀቅ 1.7 ሚሊዮን ብር እንደጠየቁ፣ ገንዘቡ በፍጥነት ካልገባ “ እንገድለዋለን ” በማለት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደሰጡ የታጋች ቤተሰቦች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ።

የታጋቹ እናት ወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ በሰጡት ቃል፣ “ አጋቾቹ ወደ ታች ዘቅዝቀው እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ‘1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን’ አሉኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ እባካችሁ ልጄን ታደጉኝ ” ሲሉ እያለቀሱ ጠይቀዋል።

“ በሄደ በ17 ቀኑ ከሊቢያ ስልክ በጓደኛው አማካኝነት ተደወለልኝ። ስልኩን ሳነሳ ‘ሊቢያ ላይ ተይዟልና 950 ሺሕ ብር ተጠይቋል’ ብሎ ጓደኛው ነገረኝ ” ያሉት የታጋቹ እናት፣ “ ከዚያ ወዲያውኑ ደግሞ ሊቢያዎቹ እየገረፉት ምስል ላኩልኝ። አካውንትም ላኩልኝ ‘ገንዘብ ላኪ’ ብለው ” ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፣ “ እንደገና ለ3ኛ ጊዜ መደኃኒት ሰጥተውት እንደ እብድ እያደረገው ቪዲዮ ላኩልኝ። እንደገና ለ4ኛ ጊዜ ደግሞ ወደ ታች #ዘቅዝቀው #እየገረፉት ቪዲዮ ላኩልኝ። ከዚያ ‘ተሽጧል 1.7 ሚሊዮን ብር አምጭ’ ብለው ደወሉ። ቪዲዮ እያሳዩም ‘1.7 ሚሊዮን ብር ታመጫለሽ አታመጭም?’ አሉኝ ” ብለዋል።

በዚህም “ እኔ የለኝም ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉልበቴ ስለሆነ ለምኘ፣ እርዳታ አሰባስቤም እከፍላለሁ አልኳቸው። ለ5ኛ ጊዜ እንደገና #ፀጉሩን ላጭተው የሆነ #ውሻ አስመስለው ምስል ላኩልኝ። ከዚያ በኋላ በቃ ‘የጨመረሻ ቀን ብለው’ ደወሉ። ልጄም በጣም #እያለቀሰ ‘አስለቅቂኝ’ አለኝ። እነርሱም ‘ነገ #አርብ 1.7 ሚሊዮን ብር ካላስገባሽ ልጅሽን በፊት ለፊትሽ ገድለን ቪዲዮ እንልክልሻለን ” አሉኝ ሲሉ አንብተዋል።

አጋቾቹ ‘ብር ላኪ’ ሲሏቸው ባለማወቅ የመፍትሄ መንገድ መስሏቸው የላኩትን አካውንት በሕግ እንዳሳገዱ፣ በዚህም አጋቾቹ የወጣቱን ስቃይ እንዳበዙት፣ ከታገተ ከአንድ ወር በላይ እንደሆነው፣ ገንዘቡ እስኪሟላ ተጨማሪ ቀን መጠየቃቸውን የገለጹት እናት፤ “ ፌደራልም ሊቢያና ሱዳን ድንበር ላይ የሊቢያ መግቢያ ላይ ነው የታገተው ብለው ነገሩኝ ” ብለዋል።

ወ/ሮ ገነት፣ ምርመራውን ይዞታል የተባሉ የፌደራል ፓሊስ አባል የአጋቹን አካል ቢደርሱበትም በሕግ በኩልም መፍትሄ እንዳላገኙ አስረድተዋል።

ያላቸው አሁናዊ የምርመራ ሂደትን በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው መርማሪው የፌደራል ፓሊስ ጉዳዩን በጽሞና ከሰሙ በኋላ “ መልስ መሰጠት የሚችለው እንደ ተቋም ስለሆነ በተቋሙ በኩል ኦፊሻል ደብዳቤ ይዘው በአካል መጥተው አመራሮችን ማነጋገር ይችላሉ ” ከማለት ውጪ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

ሆኖም ስለጉዳዩ በደብዳቤ ጠይቀን ምላሹን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

እናት አጋቾቹ ከጠየቁት ውስጥ እስካሁን የተሰበሰበው ወደ 350 ሺሕ ብር ብቻ እንደሆነ አስረድተው “ ሀዘን ላይ ነኝ። በቅርቡ ልጄ ሞቶብኛል። አሁን ደግሞ ይሄ ደረሰልኝ ብዬ፣ አሁን እንደዚህ ሆነብኝ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ረድቶኝ ልጄን እንዲያስለቅቅልኝ በትህትና እጠይቃለሁ ” ሲሉ ተማጽነዋል።

ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ የወ/ሮ ገነት ጥላሁን ይግለጡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000523577402 ሲሆን ሌሎችም የሂሳብ ቁጥሮች ከላይ ተያይዟል።

በስልክ ልታገኟቸው የምትፈልጉ 0916848184፣ 0911720985 ደውሉላቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR (1).pdf
#ይነበብ🚨

" በወንጀል የተገኘን ንብረት #ህጋዊ_ማስመሰልና #ሽብርተኝነትን_በገንዘብ_የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር " የወጣ ረቂቅ አዋጅ ለሕ/ተ/ም/ቤት ቀርቧል።

በዚሁ ረቂቅ ላይ በክፍል 5 ' ስለ ምርመራ '  ሰፍሯል።

ረቂቁ ስለ #ምርመራ ምን ይላል ?

- በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ወይም የወንጀል ፍሬን ተከታትሎ ለመለየት #የዳኝነት_አካላት ለተወሰነ ጊዜ፦

በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ #ክትትል_ለማድረግ

የኮምፒዉተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችንና ሰርቨሮችን ለመለየት፣

መገናኛዎችን #በክትትል ሥር ለማዋል ወይም #ለመጥለፍ

ድርጊቶችን፣ ባህሪዎችንና ንግግሮችን በድምፅ እና በምስል #ለመቅረፅ እና #ፎቶግራፍ_ለማንሳት

የደብዳቤ ልዉዉጦችን #ለመጥለፍ እና #ለመያዝ

በሽፋን ሥር ስለሚደረግ ምርመራና በቁጥጥር ስር የሚደረግ ማስተላለፍ ለመጠቀም፣

የሚያስችል ትዕዛዝ #ለወንጀል_መርማሪ_አካላት መስጠት ይችላሉ።

- የመርማሪ አካል የተደነገጉትን የማስረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚችለዉ ፍርድ ቤት አስተማማኝ ምክንያት መኖሩን በማረጋገጥ #ሲፈቅድ_ብቻ ነዉ።

- መርማሪው አካል #አስቸኳይ_ሁኔታ_ካጋጠመው በአካባቢው ያለውንና የሚመለከተውን የዓቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን በመጠቀም ማስረጃዎችን ሊሰበስብ ይችላል፡፡

- መርማሪ አካል #ያለፍርድ_ቤት_ትዕዛዝ የምርመራ ዘዴዎችን ተጠቅሞ ማስረጃ ለመሰብሰብ በጀመረ በ፵፰ ሰዓት ውስጥ ምክንያቶቹንና በዓቃቤ ሕግ የተሰጠውን ጊዜያዊ ፈቃድ ጨምሮ ለፍርድ ቤት በፅሁፍ ማቅረብ ይኖርበታል። ፍርድ ቤቱ የጥያቄውን አግባብነት መርምሮ ለመቀበል ወይም ደግሞ ውድቅ ለማድረግ ይችላል፡፡

- ፍርድ ቤት የምርመራ ዘዴ ማስረጃ እንዲሰበስብ ለመርማሪ አካል ፈቃድ ሲሰጥ፡-
ሀ. ማስረጃ ስለሚሰበሰብበት ዘዴ እና ስለሚከናወንበት አግባብ፤
ለ. የሚከናወንበት ጊዜ በተመለከተ ተገቢውን ትዕዛዝ መስጠት አለበት፡፡

- የማስረጃ ማሰባሰቢያው ዘዴ ጠለፋ ወይም ክትትል እንደሆነ #ጠለፋዉ ወይም #ክትትሉ የሚደረግበትን የስልክ ፣ የፋክስ ፣ የሬዲዮ ፣ የኢንተርኔት ፣ የኤሌክትሮኒክስ ፣ የፓስታና የመሳሰሉትን የግንኙነት መስመሮች አድራሻ ወይም መለያ መጥቀስ አለበት፡፡

- ማንኛውም የመገናኛ አገልግሎት አቅራቢ በመርማሪ አካል ጠለፋውን ለማካሄድ ሲጠየቅ ጠለፋው በፍ/ቤት ወይም በአቃቤ ሕግ የበላይ ሃላፊ የተፈቀደ መሆኑን በማረጋገጥ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ አለበት፡፡

- በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር በሕግ አስከባሪ አካላት በጠለፋ የተገኘ ለጉዳዩ አግባብነት ያለው ማስረጃ #በጠለፋ_በተገኘበት_መልክ_በቀጥታ ካልቀረበ በቀር ዋጋ አይኖረውም፡፡

ሙሉ ረቂቅ አዋጁን በዚህ ያንብቡ 👇 https://t.iss.one/tikvahethiopia/88222

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia