#VladimirPutin
የራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው የ’እንኳን ደስ አለዎት’ መልዕክት አስተላለፉ። ፕሬዚዳንቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በቴሌግራም ባስተላለፉት መልዕክት የኖቤል ኮሚቴው ውሳኔ ትክክለኛ መሆኑን ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደሰላም ለመመለስ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሽልማቱ ተገቢ እንደሆነም አመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቀጣናው ሰላም ለማረጋገጥና የአፍሪካ አህጉር ዓለማቀፋዊ ትስስር እንዲጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት በመደገፍ የራሺያ መንግስት ከጎናቸው የሚቆም መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል። ፕሬዚዳንት ፑቲን በመልዕክታቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጤናና ስኬት ተመኝተዋል።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#VladimirPutin #NaredraModi
የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ ዛሬ BRICSን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ ያገኙትን እና በመጪው አዲስ አመት ወደ ተግባር የሚገቡትን አዳዲሶቹ የቡድኑ አባል ሀገራት፦
- ኢትዮጵያ፣
- አርጀንቲና፣
- ኢራን፣
- የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣
- ሳዑዲ አረቢያን
- ግብፅን " እንኳን ደስ አላችሁ " ሲሉ የደስታ መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል።
በሌላ በኩል ፤ ከBRICS መስራቾች አንዷ የሆነችው ሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ናሬድራ ሞዲ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የBRICS ቡድንን መቀላቀል" እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።
ሞዲ እንደ ንግድ፣ መከላከያ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ ኢትዮጵያ BRICSን እንድትቀላቀል ህንፍ ላደረገችው ድጋፍ አድናቆታቸውን ችረዋል።
በተመሳሳይ የቻይና መንግሥትም ለኢትዮጵያ " እንኳን ደስ እላችሁ " የሚል መልዕክት አስተላልፏል።
የBRICS ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ሲሆን የአዘጋጇ ሀገር ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ አሳውቀዋል።
(የፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን መልዕክት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia