#UKRAINE #NATO
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ዛሬ በመዲናቸው ኬዬቭ ሆነው በቴሌቪዥን ለህዝባቸው ባሰሙት ንግግር ላይ የተናገሩት ፦
" ...ምዕራባውያን መሪዎች ሩሲያ አገራችንን ልትወር መሆኗን ያውቁ ነበር፤ ፑቲን ከተሞቻችንን በቦምብ እንዲደበድቡ ፈቅደዋል።
በዩክሬን ላይ ጥቃት እንደሚፈጸም እና ጉዳትም የማይቀር መሆኑን እያወቀ NATO ሆን ብሎ የዩክሬን ሰማይ ለበረራ ዝግ እንዳይሆን አድርጓል።
የNATO መሪዎች ዛሬም ከበረራ ነጻ የሆነ ቀጠና ውሳኔን ባለማሳለፋቸው ምክንያት ተጨማሪ የዩክሬን ከተሞች እና መንደሮች በቦምብ እንዲደበደቡ ፈቅደዋል።
NATO ዩክሬንን ለመከላከል እርምጃ ባለመውሰዱ በጦርነቱ ምክንያት ለሚሞቱ የአገራችን ዜጎች ሕይወት ተጠያቂ ነው። "
ለምንድነው NATO የዩክሬንን አየር ማይዘጋው ?
NATO በምድርም ሆነ በአየር ወደ ዩክሬን የመግባት ፍላጎት የለውም።
ለNATO ውሳኔ ምዕራባውያን ባለሥልጣናት እንደምክንያት የሚያስቀምጡት በዩክሬን ከበረራ ነጻ የሆነ ቀጠና ከተከለለ የNATO አውሮፕላኖች ጥሰት በሚፈጽሙ የሩሲያ ተዋጊ አውሮፕላኖች ላይ ጥቃት መሰንዘር ይችላሉ።
ይህ ደግሞ 3ኛው የዓለም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።
@tikvahethiopia

#Ukraine
ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ጋር ወዳጅ የሆኑ ሀገራት (አሜሪካ እና አጋሮቿ) ፕሬዜዳንቱ በሩሲያ ሃይሎች ቢያዙ ወይም ቢገደሉ በእሳቸው ቦታ ላይ ስለሚኖረው ‘የመተካካት ሂደት' እየተወያዩ መሆናቸውን ኒውዮርክ ታይምስ ዛሬ አስነብቧል።
አሜሪካ እና አጋሮቿ ሩስያ የሚታዘዝላትን መንግስት በኬዬቭ እንዳታስቀምጥ ስጋት አላቸው ተብሏል። ለሚቀመጠው መንግስትም እውቅና እንደማይሰጡ እና ይህም እንዳይሆን እንደሚከላከሉ ነው አቋማቸው።
ከዚህ ቀደም የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን በፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌስንኪ የምትመራውን ዩክሬን " የምዕራቡ ዓለም አሻንጉሊት " ሲሉ የጠሯት ሲሆን የዩክሬን ጦር ከአስተዳደራቸው ስልጣን እንዲነጥቅና እንዲቆጣጠር ጥሪ አቅርበው እንደነበር ይታወሳል።
አሁንም በዩክሬን እና በሩስያ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን የዩክሬኑ ፕሬዜዳንት ህዝባቸው እንዲፋለም ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
በተጨማሪ " ዓለም ለሩስያ ሮኬቶች እና አውሮፕላኖች የአየር ቀጠናችንን የመዝጋት ኃይል አለውና ይዝጋልን ፤ የዩክሬንን ሰማይ አስተማማኝ ለማድረግም የጦር አውሮፕላኖች ያስፈልጉናል " የሚል ጥሪ እያቀረቡ ነው።
ትላንት ቭላድሚር ፒቲን በዩክሬን ሰማይ ላይ የበረራ ክልከላ ለማድረግ የሚሞክር የትኛውም ኃይል በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እንዳደረገ እንደሚታይ እና እንዲህ ያለው እርምጃ ለአውሮፓ እና ለዓለም አስከፊ መዘዝ የሚያስከትል እንደሆነ ማስጠንቀቃቸው አይዘነጋም።

የዩክሬን መንግሥት ስንዴ፣ አጃ እና መሰል የእህል ምርቶች ከሀገር ውጭ ለገበያ እንዳይቀርቡ ማገዱ ዛሬ ይፋ ሆኗል።
የግብር እና ምርቶችን የሚመለከተው አዲሱ ሕግ ዩክሬን ውስጥ የተደነገገው በዚህ ሳምንት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።
በአሁን ሰዓት ከሩስያ ጋር በጦርነት ላይ የምትገኘው ዩክሬን የምድራችን ከፍተኛ የስንዴ አምራች ሀገር ናት።
በተጨማሪ ዓለማችን ግማሹን የሱፍ አበባ እና ከዚህ ሰብል የሚገኙት ዘይትና ሌሎች ምርቶችን የምታገኘው በአሁን ሰዓት ጦርነት ላይ ካሉት 2ቱ ሀገራት ነው።
ዩክሬን በበቆሎ ምርቷም በዓለማችን የምትታወቅ ሀገር ናት።

TIKVAH-ETHIOPIA
#Russia #Poland #Germany አዲስ አበባ ያለው የሩስያ ኤምባሲ ያሰራጨው መልዕክት መነጋገሪያ ሆኗል፤ በኤምባሲዎች መካከልም ውዝግብ ፈጥሯል። የሩስያ ኤምባሲ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጿል። ይህ መልዕክት እየደረሰው ያለው ከገፁ ተከታዮች መሆኑን አመልክቷል። ኤምባሲው " ሀገሮቻችን…
#Ukraine
በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩክሬን ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ፥ ሩስያ በዩክሬን ላይ በፈፀመችው ወረራ ለዩክሬን ያላቸውን ድጋፍን እና አብሮነት የገለፁትን ተከታዮቹን አንደሚያደንቅ ገልጿል።
" ወዳጆቻችን እናመሰግናለን " ያለው የዩክሬን ኤምባሲ ወረራውን የፈፀመችው ሩስያ በሁሉም ዩክሬናውያን ከተሸነፈች በኃላ ኤምባሲው ቁርጠኛ ለሆኑ የፌስቡክ ወዳጆቹ በሎተሪ ወደ ዩክሬን ከክፍያ ነፃ የመግቢያ ቪዛ ሊሰጥ እያሰበ መሆኑን አሳውቋል።
ኤምባሲው እስከዛሬ ንቁ የሆኑ የፌስቡክ አክቲቪስቶች ብሎ የ38 ሰዎችን (ኢትዮጵያውያን) ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ የሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ለሩስያ ድጋፋቸውን የሚገልፁ በየዕለቱ ብዙ ደብዳቤዎች ፣ በመቶዎች የሚቆጠር አስተያየት እንደሚደርሰው ገልጾ ፤ " ሀገሮቻችን በችግር ጊዜ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት እንደዚህ አይነት ጠንካራ ፣ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፣ ወዳጃዊ ግንኙነት ስላላቸው ኩራት ይሰማናል " ማለቱ አይዘነጋም።
ኢትዮጵያውያን ተከታዮቹ እያሳዩት ላለው ድጋፍና ከሩስያ ጎን እንደሚቆሙ መምረጣቸውን በእጅጉ እንደሚያደንቅ መግለፁ ይታወሳል።
ይህን የሩስያ ኤምባሲ መልዕክት ተከትሎ በአዲስ አበባ የፖላንድ እና የጀርመን ኤምባሲዎች የሩስያን ኤምባሲ የሚቃወም ጠንካራ መልዕክቶችን ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

#Ukraine #Russia
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከሩሲያ ጋር ውጤት የሚያስገኝ የሰላም ንግግር በአስቸኳይ ማድረግ እንደሚፈልጉ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ለሕዝባቸው ባስተላለፉት የቪድዮ መልዕክት በግዛታቸው ውስጥ ግዙፍ ወታደራዊ ዘመቻ እያካሄደች ካለችው ሩሲያ ጋር " ካለምንም መዘግየት ትርጉም ያለው " የሰላምና የደኅንት ንግግር እንዲጀመር ጠይቀዋል።
ይህ ሩሲያ በአገራቸው ላይ በከፈተችው ወረራ በፈጸመችው "ስህተት" የሚደርስባትን ጉዳት ለመቀነስ ያላት ብቸኛው እድል ነው ሲሉ ዜሌንስኪ ተናግረዋል።
" ለመገናኘት፣ ለመነጋገርና የዩክሬንን የግዛት አንድነት እንዲሁም ፍትህን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ዜሌነስኪ ለሩሲያ ጥሪ አቅርበዋል።
" ይህ ካልሆነ ግን ሩሲያ ከሚገጥማት ውድቀት ለመውጣት በርካታ ትውልዶችን መጠበቅ ሊያስፈልጋት ይችላል " ማለታቸውን #ቢቢሲ ዘግቧል።
በሌላ በኩል ፤ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ባለፈው ሀሙስ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት አገራቸው ጦርነቱን ለማቆም ከዚህ በፊት ይፋ አድርጋው የነበረውን ቅድመ ሁኔታዎች በድጋሚ ገልፀዋል።
ዋነኞቹ ቅድመ ሁኔታዎች ፦
- ዩክሬን NATOን እንደማትቀላቀል ማረጋገጥ።
- ዩክሬን ትጥቅ እንድትፈታ፣
- በዩክሬን የሩሲያ ቋንቋ እንዲከበር እና የናዚ አመለካከት አራማጅ ናቸው የተባሉ ኃይሎችን ዩክሬን እንድትቆጣጠር፣
- ክራይሚያ የሩሲያ ግዛት መሆኗን፣ በቅርቡ ነጻነታቸውን ላወጁት ምሥራቃዊ የዩክሬን ግዛቶች ደግሞ እውቅና እንድትሰጥ ዋነኞቹ የሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው።

Photo
#Ukraine #Russia
ሩሲያ የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍት ገለፀች።
ሀገሪቱ ይህን የገለፀችው በዩክሬን እያካሄድኩ ነው ያለችውን “ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ” የመጀመሪያውን ምዕራፍ ማጠናቀቋን ባሳወቀችበት ወቅት ነው።
ሀገሪቱ ተጠናቋል ባለችው የመጀመሪያ ምዕራፍ ያስቀመጠችው ግቦች እንደተሳኩ የገለጸች ሲሆን ብዙ የዩክሬን ግዛቶችን መቆጣጠሯን አሳውቃለች።
ሩስያ ጦሯ የዩክሬንን ዋና ከተማ ኪቭን ጨምሮ ካርኪቭ፣ ቼርኒሂቭመ ሱሚ እና ሚኮላይቭ የተባሉ አካባቢዎችን መክበቡን ገልፃለች። በተጨማሪ ኬርሶን እና ዛፖሮዚ የተባሉ የዩክሬን ግዛቶች አሁን ላይ በእጇ ላይ መውደቁን አሳውቃለች።
በዩክሬን የተገንጣዮች ግዛት የሆነችውን ሉሃንስክን ደግሞ 93 በመቶ መቆጣጠሯን አሳውቃለች።
የዩክሬንን የአየር ክልል ለመዝጋት ከሚሞክር ኃይል ጋር ጦርነት እንደምትከፍትም ዝታለች።
4 ሳምንታት ባስቆጠረው የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት ምክንያት ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ሰዎች ሲያልቁ ከ3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ተሰደዋል።
መረጃው የአልዓይን ኒውስ ነው።

የሩስያን ድንበር ጥሰው ገቡ የተባሉ ሁለት የዩክሬን ጦር ሂሊኮፕተሮች የነዳጅ ማከማቻ ላይ ጥቃት መፈፀማቸው ተሰማ።
ሁለት የዩክሬን ሄሊኮፕተሮች የሩሲያን ድንበር ጥሰው በሀገሪቱ ምዕራባዊ ከተማ ቤልጎሮድ የነዳጅ ማከማቻ ቦታ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የአከባቢው አስተዳዳር ዛሬ አስታውቋል።
የአካባቢው አስተዳዳሪ የሆኑት ቫያቼስላቭ ግላድኮቭ በቴሌግራም ቻናላቸው ላይ ሁለት የዩክሬን ጦር ሄሊኮፕተሮች በፈፀሙት የአየር ጥቃት በሚያስተዳድሩት አካባቢ ባለ የነዳጅ ማከማቻ ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን ጽፈዋል።
በቃጠሎው ምክንያት በነዳጅ ማከማቻው ውስጥ የነበሩ ሁለት ሰራተኞች መቁሰላቸው ተገልጿል።
የዩክሬን እና ሩስያ ጦርነት ከተጀመረበት ጊዜ አብስቶ ሩስያ ፤ ዩክሬን ድንበሯን አልፋ ጥቃት ፈፀመችብኝ ብላ ሪፖርት ስታደርግ ይህ የመጀመሪያ ነው።
የ2ቱ ሀገራት ጦርነት እስካሁን ድረስ ይህን ነው የሚባል መፍትሄ ሳይገኝለት ከወር በላይ ተቆጥሯል።
አሁንም ጦርነቱ እንዲቆም ለማድረግ ንግግሮች ቢኖሩም ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ግጭት እንዲቀጥል የሚያደርጉ ወታደራዊ ሁኔታዎች እንደሚስተዋሉ እየተነገረ ነው።
በሀገራቱ ጦርነት ምክንያት ከሚጠፋው የሰው ህይወት ፣ ከሚሰደደው ሰው ባለፈ በዓለም ኢኮኖሚ እና በሀገራት የኑሮ ውድነት ላይ በየዕለቱ እያሳደረ ያለው ግልፅ ተፅእኖ እየከፋ ነው።

በዩክሬን ዋና ከተማ ኬየቭ አቅራቢያ በምትገኝ " ቡቻ " በምትባል ከተማ የጅምላ መቃብር እና የሰዎች አስክሬን በከተማው ጎዳና ላይ ተጥሎ መገኘቱ ተሰማ።
ዩክሬን ፤ ሩስያ በቡቻ የጅምላ ግድያ ፈፅማለች ስትል ከሳለች።
የሩስያ ጦር ቡቻን ለቆ መውጣቱን ተከትሎ የጅምላ መቃብር እና መንገድ ላይ የወዳደቁ አስክሬኖች መገኘታቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት ገልፀዋል።
ፕሬዜዳንት ዜሌኒስኪ የተሰራጩ ፎቶዎችን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ፥ " የሩስያ ወታደሮች እናቶች ይህንን ማየት አለባቸው ፥ እዩ ምን አይነት ገዳዮችን፣ ዘራፊዎችን... እንዳሳደጋችሁ " ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኩሌባ ፤ በቡቻ ሆን ተብሎ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል ብለው G7 ጠንካራ ማዕቀብ እንዲጥል ጥሪ አቅርበዋል።
የቡቻ ከተማ ከንቲባ እንደገለፁት ፥ ቢያንስ 300 ሰዎች በጅምላ መቃብር ተቀብረዋል። የተገደሉት ሰላማዊ ሰዎች ናቸው ግድያውን የፈፀመው የሩስያ ጦር ነው ብለዋል።
በተጨማሪ ከኬየቭ ውጭ ባሉ ሌሎች ከተሞችም በሩስያ ጦር ተፈፅመዋል የተባሉ የጅምላ መቃብሮች እና አስክሬኖች በየጎዳናው እየታዩ ነው።
ሀገራት በሩስያ ላይ ውግዘት እያሰሙ ሲሆን ጀርመን የጦር ወንጀል ነው ብላዋለች።
ሩስያ እየወጣ ያለውን ሪፖርት አጥብቃ አስተባብላለች።
የሩስያ ጦር ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ፥ የሩስያ ወታደሮች ከአካባቢው እንዲወጡ የተደረገው እኤአ መጋቢት 30 እንደሆነ ገልጾ " የወንጀል ማስረጃዎች " ተብለው የታዩት የሩስያ ጦር ከወጣ በ4ኛ ቀን ነው ብሏል።
እኤአ መጋቢት 31 የቡቻ ከንቲባ በቪድዮ የሩስያ ጦር በከተማው እንደሌለ በቪድዮ እያሳዩ አረጋግጠዋል ነገር ግን አሁን የተባለውን አልጠቀሱም ብሏል።
ሩስያ ጉዳዩን ሀሰተኛ ዜና ስትል ውድቅ አድርጋዋለች።

#Russia #Ukraine
ሰሞኑን አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ በርካታ " ኢትዮጵያዊያን ሩሲያን ወግነው ዩክሬንን ለመውጋት " ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው።
ኢትዮጵያውያኑ በእጃቸው ላይ ዶክመት ይዘው ተሰልፈው ይታያል።
የሩስያ ኤምባሲ ፕረስ አታቼ የሆኑት ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን በሰጡት ቃል ፤ " ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው " ሲሉ መልሰዋል።
ነገር ግን ኢትዮጵያውን ወደ ኢምባሲው መሄዳቸው እውነት መሆኑን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያውያን ወደ ሩሲያ ኢምባሲ የሄዱት ለምልመላ ሳይሆን ለሩሲያ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት መሆኑን ነው የገለፁት።
ይሁንና ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት " በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢሜይል እና በአካል ከሩሲያ ጎን መሆናቸውን እያሳወቁን ነው ለዚህ እናመሰግናለን " ሲሉም አክለዋል።
ኢትዮጵያዊያን ይሄንን እያደረጉ ያለው ረጅም እና ታሪካዊ በሆነው የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ወዳጅነት ላይ ስለሚተማመኑ እንደሆነ ኤምባሲው ተገልጿል።
የዩክሬን ኤምባሲ ደግሞ ሩስያ ምልመላ እያደረገች ነው በሚል የተሰራጨውን መረጃ በተመለከተ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ ማጣሪያ ድረገፅ በሰጠው ቃል ፤ "ይህ አሳዛኝ ድርጊት ነው። አንድ ኢትዮጵያዊ በዚህ ጦርነት ህይወቱ ቢያልፍ ለዩክሬንም ሆነ ለኢትዮጵያ አሳዛኝ ክስተት ይሆናል። " ብሏል።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ እና የኢትዮጵያ ቼክ የመረጀ ማጣሪያ ድረገፅ ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#Russia #Ukraine ሰሞኑን አዲስ አበባ በሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ በር ላይ በርካታ " ኢትዮጵያዊያን ሩሲያን ወግነው ዩክሬንን ለመውጋት " ለመመዝገብ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው የሚል ምስል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ኢትዮጵያውያኑ በእጃቸው ላይ ዶክመት ይዘው ተሰልፈው ይታያል። የሩስያ ኤምባሲ ፕረስ አታቼ የሆኑት ማሪያ ቸርኑኪና ለአል ዐይን በሰጡት ቃል ፤ " ሩሲያ ለዩክሬን…
#Ukraine
በአዲስ አበባ የሩሲያ ኤምባሲ ፥ " ሩሲያ ለዩክሬን ጦርነት ኢትዮጵያዊያንን ለመቅጠር ማስታወቂያ አላወጣችም፣ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ሀሰተኛ ነው "፤ ኢትዮጵያውያኑ የተሰለፉት ድጋፍ ለመግለፅ ነው ማለቱ ይታወሳል።
የዩክሬን ኤምባሲ ግን ማስተባበያው እራሱ ሀሰተኛ ነው ብሏል።
ኤምባሲው፤ " በተለያዩ የማህበረሰብ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው " መባሉ " በራሱ ውሸት ነው " ሲል ገልጿል።
ሩሲያ አሁን ላይ ከኢትዮጵያ ወጣቶችን ለመመልመል ሙከራ እያደረገች ትገኛለች ብሏል።
የኤምባሲው የሚሽን ሃላፊ አሌክሳንደር ለአል ዓይን በሰጡት ቃል፥ ከሰሞኑ አንድ የሩሲያን ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሰ ሰው አዲስ አበባ ገብቷል ሲሉ ተናግረዋል።
የሰውዬው መግባት ከጉዳዩ ጋር ምን እንደሚያገናኘው ተጠይቀው " ዩኒፎርም የለበሰው ወታደር መቼም በግ ጠባቂ አይደለም፣ ወታደር እንጅ " ሲሉ መልሰዋል።
ሩሲያ "70 % የሚሆነው ጦሯ አልዋጋም ስላላት ኢትዮጵያውንን ለመመልመል ጥረት እያደረገች ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ግን ፈቃደኛ አልሆኑላትም" ሲሉም ተናግረዋል።
ሩስያ ምልመላ ለማድረግ እየሞከረች ነው ያለው የዩክሬን ኤምባሲ " የተለያዩ መደለያዎችን እሰጣለሁ " በማለት ነው ኢትዮጵያውያንን ለመመልመል ጥረት እያደረገች የምትገኘው ሲል ለአል ዓይን ኒውስ ገልጿል።
ምንም እንኳን ሩስያ "ለምልመላ ማስታወቂያ አላወጣሁም" ብትልም ዛሬም ሰዎች በተለይ ዶክመት የያዙ ወጣቶች ኤምባሲው በር ላይ ተሰልፈው እንደነበር ቢቢሲ ፅፏል።
በኤምባሲ በር ላይ ተሰልፎ የነበረ አንድ ወጣት በጥሩ ደመወዝ በወታደርነት ወይም በተገኘው ስራ ለመቀጠር እንደመጣ ተናግሮ " ሩሲያን እወዳታለሁ " ብሏል።
ስለጉዳዩ በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።