TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HappeningNow

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ የሚውል ያለውን አዲስ አገልግሎት (መተግበሪያ) ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር እያከናወነ ይገኛል።

አገልግሎቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢግል ላይን ሲስተምስ ቴክኖሎጂ ትብብር እንደተዘጋጀ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፥ " አዲሱ የሆቴሎች መተግበሪያ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ ላይ የሚውለው ሲሆን የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፉን አሰራር እንደሚያዘምን ይጠበቃል " ብሏል።

@tikvahethiopia
#HappeningNow

" አዲስ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ትውልድ "

ሴንተር ፎር አድቫንስመንት ኦፍ ራይትስ ኤንድ ዴሞክራሲ (ካርድ) “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ በሚል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል።

ዛሬ የሚመረቁት 364 የሚሆኑ የመንግሥትና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች መሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ፅንሰ ሐሳቦችን፣ የሥርዓተ ፆታ እኩልነት፣ ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት እንዲሁም የመሰብሰብና የመደራጀት መብቶች ላይ ሥልጠናዎችን ወስደነዋል።

በዛሬው ዕለት በኢንትር ላግዠሪ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የሰብዓዊ መብት ፌስቲቫል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚዴቅሳ ተገኝተዋል።

መርኃግብሩን የካርድ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር በፍቃዱ ኃይሉ በንግግር ከፍተዋል።

🔴 Live : https://fb.watch/9Rmjulyc8J/

@tikvahethiopia
#HappeningNow

በአሁኑ ሰዓት የጦር ሀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የአውደ ውጊያ ውሎ የሜዳሊያ ሽልማት እና አዲሱ የመከለከያ ጠቅላይ መምሪያ ህንጻ ምረቃ እየተከናወነ ይገኛል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የሰልፍ እና የአየር ትርዒትም ቀርቧል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopia
#HappeningNow

በሰሜን ኢትዮጵያ ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ በአፋርና በአማራ ክልሎች የተከሰተውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በተመለከተ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ያካሄደውን የምርመራ ሪፖርት ይፋ እያደረገ ይገኛል።

ኮሚሽኑ የሪፖርቱን ድምዳሜዎችና ምክረ ሀሳቦችን ይገለጻል ተብሎ ይጠበቃል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በዚሁ መርሃ ግብር ላይ የተገኙ ሲሆን በቀጥታ የምርመራ ሪፖርቱን የሚመለከቱ ጉዳዮችን በፅሁፍ ይልኩላችኃል።

አመቺ ቦታ ላይ ያላችሁ እና ጥሩ የኔትዎርክ ግንኙነት ያላችሁ በቲክቫህ መጋዚን በኩል #ቀጥታ በድምፅ ለመከታተል ይኸኛውን ሊንክ ይከተሉ : t.iss.one/tikvahethmagazine?livestream

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትኩረት📣 የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ፤ " የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ቅዱስ ላልይበላ ዓለም አቀፍ ቅርስ ሊመለከት ይገባል " ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። ብፁዕነታቸው ቅዱስ ላልይበላን በማስመልከት ዛሬ በተሰጠ መግለጫ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በነበረው ጦርነት የቅዱስ ላልይበላ ቅርስ የቱሪዝም እና የከተማው እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጫና ውስጥ መውደቁን…
#HappeningNow

" ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልከቱ ! "

ለታሪካዊው እና ዓለማቀፋዊው የላልይበላ ቅርስ በሸራተን አዲስ ሆቴል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

የቅዱስ ላልይበላ አብያተ ክርስቲያናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን የሁሉም ሃይማኖቶች እና ብሔረሰቦች ከዚያም አልፎ የዓለም ሁሉ ቅርስ በመሆናቸው ቅርሱን በመጠበቅ ላይ ያሉ ወገኖችን መርዳትና መደገፍ የዓለም ሁሉ ትኩረት ሊሆን እንደሚገባ ተገልጿል።

" ወደ ቅዱስ ላልይበላ ተመልከቱ!" በሚል ጥሪ ዛሬ በሸራተን አዲስ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

በዚህም ለጥንታዊው እና ታሪካዊው ላልይበላ ካህናት፣ ገዳማውያን፣ ቅርስ ጠባቂዎች ፣ የአብነት ተማሪዎች ፣ አረጋውያን እና ህጻናትን ለመርዳት ብሎም የቅርሱን ልማት ለማፋጠን ሁሉም እንዲረባረብ ጥሪ መቅረቡን የኢኦተቤ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ማስታወሻ፦ ድጋፍ ማድረግ የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ አቢሲኒያ እና ዳሽን ባንኮች በ 👉 0712 የባንክ የሒሳብ ቁጥር ድጋፍ ማድረግ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia
#HappeningNow

ኢትዮ ቴሌኮም ቴሌብር መላ፤ ቴሌብር እንደኪሴ እንዲሁም ቴሌብር ቁጠባ የተሰኙ የፋይናንሻል አገልግሎቶችን ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል።

ቴሌ ብር መላ፦ የቴሌብር ደንበኞቹን ባንቀሳቀሱት የገንዘብ ዝውውር መሰረት ታይቶ እስከ በቀን እስከ 2,000 በወር ደግሞ እስከ 10,000 ብር የሚደርስ ብድር የሚያመቻች አገልግሎት ነው።

ቴሌ ብር እንደኪሴ ፦ በቴሌብር አማካኝነት ግብይት በሚፈጸምበት ጊዜ የቴሌብር ሂሳቦ ከሚገዙት እቃ በታች ከሆነ ቀሪውን ክፍያ ጨምሮ ለሻጭ ይከፍልና ገንዘብ ገቢ ሲያደርጉ ከሂሳቦ ላይ ተቀናሽ የሚያደርግ አገልግሎት ነው።

ቴሌብር ቁጠባ፦ ቴሌብር ላይ ካለው የገንዘብ መጠን ላይ መቆጠብ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን በሁለት አማራጮች ማለትም በወለድና ያለወለድ የቀረበ ነው። የወለድ መጠኑም 7% ሲሆን ወለዱ መጠን በቀን ተሰልቶ በሂሳቦ ገቢ ይደረጋል።

ተጨማሪ መረጃ እንልክላችኃለን!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" አዲሱ ስርዓተ ትምህርት " የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ክልሎች አስፈላጊ መፅሀፍትና ቋንቋ የመተርጎም ስራ እየሰሩ ሲሆን በፍጥነት ወደ መፅሀፍ የማሳተም ስራ እንዲገባ እየተሰራ ነው ተብሏል። በዚህም ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የመጀመሪያ…
#HappeningNow #AddisAbaba

በ2015 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ በሚግባው አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ዙሪያ ውይይት ተጀመረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ስልጠና እና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2015 የትምህርት ዘመን ወደ ሙሉ ትግበራ የሚገባውን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራን በተመለከተ ከግል እና መንግስታዊ ካልሆኑ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶች ጋር የውይይት መድረክ መካሄድ መጀመሩን ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ከትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንደተገኘው መረጃ ፤ የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ተሞክሮ የተጠናቀቀ ሲሆን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

በተመሳሳይ በቀጣይ ዓመት የ2ኛ ደረጃ ካሪኩለም የሙከራ ስራ በተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ላይ የሚሞከር ሲሆን 2016 ዓ/ም ላይ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ቅዱስ ፓትርያርኩ ለህክምና ከሄዱበት አሜሪካ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ሲገቡ አቀባበል ይደረግላቸዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ሕክምናቸውን አጠናቀው ነገ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ይመለሳሉ። ቅዱስ ፓትራርኩ ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው መመለሳቸውን…
#HappeningNow

ቅዱስነታቸው በሰላም ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው ተመልሰዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በሀገረ አሜሪካ ሲያደርጉ የነበረውን ሕክምናቸውን አጠናቀው ዛሬ ጷጉሜን 1 ቀን 2014 ዓ/ም ወደ ኢትዮጵያና ወቅዱስ መንበራቸው በሰላምና በመልካም ጤና ተመልሰዋል።

የቅዱስነታቸውን ወደ ሀገርና ወቅዱስ መንበራቸው መመለስን ተከትሎ በአሁን ሰዓት የአቀባበል ሥነሥርዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እየተካሄደ ነው።

የፎቶ ባለቤት : የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶክተር ዊሊያም ሩቶ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ፕሬዜዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተቀብለዋቸዋል። ሩቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሀገር አቀፍ የቴሌኮም ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። ዶ/ር…
#HappeningNow

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱን በአዲስ አበባ " ወዳጅነት አደባባይ " በአሁን ሰዓት እያካሄደ ይገኛል።

በዚሁ ስነስርዓት ላይ ቀደም ብሎ እንደተገለፀው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የኬንያው ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ተገኝተዋል።

Photo Credit : Safaricom Ethiopia

@tikvahethiopia