TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Djibouti

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በ38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገብተዋል።

ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል።

በሌላ በኩል ፦

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሓምዶክና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሰሞነኛው የግብፅ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ዙሪያ :

#Djibouti

• የግብፁ ፕሬዝደንት አብዱልፈታህ አል ሲሲ ከጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ለመወያየት ዛሬ ማለዳ ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል፡፡

- የፕሬዚዳንቱ የጅቡቲ ጉብኝት በዓይነቱ የመጀመሪያ ነው ተብሏል።

- የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በጋራ ትብብር እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ታውቋል። በተለይም በፀጥታ ፣ በወታደራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሁለቱን ሀገራት ትብብር ማጠናከር የውይይቱ ዓላማ መሆኑ ተጠቁሟል።

 - የግብፅና የጅቡቲ መሪዎች የጋራ በሆኑ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት እና ሀሳቦችን ለመለዋወጥም አቅደዋል፡፡

#Kenya

• ግብፅ እና ኬንያ በትናንትናው እለት ወታደራዊ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

- በናይሮቢ የተፈረመው ስምምነት ዓላማ የሁለቱን ሀገራት የጋራ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር አካል ነው።

- ግብፅ ከኬንያ ጋር ያደረገችው ወታደራዊ ስምምነት እ.ኤ.አ. በ2021 በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት ጋር ያደረገችው አራተኛ ስምምነት ነው፡፡

- ከኬንያ በተጨማሪ ከሱዳን ፣ ከኡጋንዳ እን ከብሩንዲ ጋር ግብፅ ወታደራዊ ስምምነት ፈርማለች፡፡

#Sudan

• ግብፅ እና ሱዳን በትናንትናው ዕለት ለ 6 ቀናት የሚቆይ ሁለገብ የጋራ ወታደራዊ ልምምድ በሱዳን ጀምረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ከሁለቱ ሀገራት ጋር ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት የሚካሔደው ይህ ልምምድ ፣ የናይል ጠባቂዎች (Nile Protectors/ናይል ፕሮቴክተርስ) የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

#አልአይን

@tikvahethiopia
#Djibouti : በጅቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እያቀኑ የሚገኙት የተ.መ.ድ (UN) ምልክት ያለባቸው ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ናቸው ሲል በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋዊ ትዊተር ገፁ አሳውቋል።

እነዚህ ተሽከርካሪዎች በዳርፉር በ #UNAMID ስር በሰላም ማስከበር ስራ አገልግሎት ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti

ከሰሞኑን በዩጋንዳ እና ሩዋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደረጉት እና ከሀገራቱ መሪዎች ጋር የመከሩት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አሁን ደግሞ ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ፕሬዜዳንታ ጋር በስልክ ተወያያተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኡመር ጌሌ ጋር የተወያዩት በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ነው። በውይይታቸው የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ተብሏል።

ዶ/ር ዐቢይ እና ኢማኤል ኡመር ጌሌ በቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያም መክረዋል ፥ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን በጠበቀ መልኩ የሁለትዮሽና የቀጠናዊ ግንኙነትን ለማጠናከር ተነጋግረዋል።

በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደተገኘው መረጃ።

@tikvahethiopia
#Djibouti

በሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የተመራው የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ልዑክ ጂቡቲ ይገኛል።

ልዑኩ ሄሪቴጅ ኢንስቲትዩት በተባለው አለም አቀፍ የጥናትና ምርምር ተቋም አማካኝነት በየአመቱ የሚያዘጋጀው መድረክ ላይ እየተሳተፈ ነው።

መድረኩ በዋናነት በምስራቅ አፍሪካ ወቅታዊ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና በቀጠናው ውህደት ላይ ትኩረቱ ያደረገ ሲሆን የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ናቸው በንግግር የከፈቱት።

የጅቡቲ እና የሶማሊያ ሪፐብሊክ ባለስልጣናት እንዲሁም የኬንያ የቀድሞ ጁብሊ ፓርቲ መሪ ሌሎች ሙሁራን ተገኝተዋል።

የዘንድሮው መድረክ "በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ያሉ ችግሮች የመረጋጋት ተስፋን ይጎትታሉ?" በሚል ርዕስ ነው የተካሄደ ሲሆን ከተለያዩ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የተውጣጡ እውቅ ምሁራን ፅሁፎች አቅርበው ውይይት ተደርጓል።

በመድረኩ በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ በቀጠናው ያለው አንደምታ ተዳሷል።

የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ፥ " ወራሪውና አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ የከፈተው ወረራ ቀጠናውን ለማተራመስ የተነሳ ስለሆነ የቀንዱ ሀገራት በጋራ ሊመክቱ ይገባል " ብለዋል።

አክለው ፥ " ጠ/ ሚ ዐቢይ አህመድ በማንኛውም ሀገር ላይ ጣልቃ ገብነት እንዳይኖርና አሸባሪው ህወሓት በምስራቅ አፍሪካ ያደርግ የነበረውን ጣልቃ ገብነትና የማተራመስ ስትራቴጂን ተከላክለው መልካም የሆነ ጉርብትና በሀገራት መካከል እንዲኖር አድርገዋል " ብለዋል

በተጨማሪ በመድረኩ ላይ አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድና ልዑካቸው የኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የኢትዮጵያውያን ብቻ ነው በማለት የኢትዮጵያን ድምፅ አሰምተዋል።

@tikvahethiopia
#Egypt #Djibouti

ኢማኤል ኦመር ጌሌ ግብፅ ገብተዋል።

የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ከፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በተደረገላቸው ግብዣ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ትላንት ለሊት ግብፅ ገብተዋል።

ፕሬዜዳንቱ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ናቸው የተቀበሏቸው።

በዛው ዕለት ሁለቱ መሪዎች ስብሰባ የሚኖራቸው ሲሆን በሁለትዮሽ ጉዳዮቻቸውና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሏል።

ፎቶ፦ የጅቡቲ ፕሬዜዳንት (ኢሳማኤል ኦመር ጌሌ)

@tikvahethiopia
#Djibouti #Ethiopia

የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ ቤትዎ እንኳን በደህና መጡ " ያሉ ሲሆን " በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በጋራ ጉዳዮቻችን ላይ ፍሬያማ ውይይት እንደምናደርግ እምነቴ ነው " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Djibouti #Ethiopia የጎረቤት ሀገር ጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ለሁለት ቀን የስራ ጉብኝት ዛሬ ኢትዮጵያ ገብተዋል። በሁለት ቀን የስራ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደርጋሉ። የፕሬዚዳንቱን መምጣት ተከትሎ ጠ/ሚር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ " የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ወንድሜ ኢስማኤል ኦመር ጌሌ ወደ ሁለተኛ…
#Ethiopia #Djibouti

ትላንት ለሁለት ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትላንት ኢትዮጵያ የገቡት የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ እና ልዑካቸው ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ልዑካቸው ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱ በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር።

ከተነሱት ጉዳዮች መካከል ፦

👉 የንግድ፣
👉 የግብርና ሙዓለ ነዋይ ፍሰት፣
👉 የጋራ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣
👉 ቱሪዝም፣
👉 ኢነርጂ እና ሌሎች ዘርፎችን ኢኮኖሚያዊ ትስስርን ባማከለ መልኩ ማጠናከር ይገኙበታል።

መረጃውን ከጠ/ሚ ፅ/ቤት ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #Djibouti

በጅቡቲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እንደተገኘው መረጃ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የነዳጅ ማከማቻ ተርሚናል በጋራ ለማልማት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የነዳጅ ማከማቻው በጂቡቲ ነጻ ወደቦች ቀጠና የሚካሄድ ነው።

የመግባቢያ ስምምነቱ ሃገራቱ ወደፊት በዘርፉ ለሚያካሂዱት ልማት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠርና ተጨማሪ እድሎችን ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

@tikvahethiopia
#Djibouti

የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጅቡቲ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጅቡቲ ያቀኑት ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እንዲሁም ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ነው።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከከፍተኛ ልዑካን ቡድን ጋር ጅቡቲ በደረሱበት ወቅት ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ ናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው።

ትላንት ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ኢማኤል ኦማር ጌሌ ለዶ/ር ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመት ኬንያ ፣ ናይሮቢ እንደነበሩ ይታወሳል።

#Update

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማሻሻል ባደረጉት ጥረት፣ እ.ኤ.አ የ2022 የዓለም ኢስላሚክ የፋይናንስ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል ሽልማታቸውንም በጅቡቲ ተቀብለዋል።

@tikvahethiopia
#Djibouti

45 ስደተኞች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።

ከየመን 310 ስደተኞችን በመጫን በጉዞ ላይ የነበሩ ሁለት ጀልባዎች ሰጥመው እስካሁን ባለው 45 ሰዎች መሞታቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።

የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጠባቂ እንዳስታወቀው አደጋው በሰሜናዊ ምዕራብ ሖር አንጋር አካባቢ ካለው የባህር ዳርቻ 150 ሜትሮች ርቆ ነው የተከሰተው።

ከሰኞ ጀምሮ በተደረገው ፍለጋ በህይወት የተረፉ 115 ሰዎች ማዳን እንደተቻለ የጅቡቲ የባህር ጠረፍ ጥበቃ አሳውቋል።

እስካሁን በርካታ ስደተኞች የደረሱበት አልታወቀም።

@tikvahethiopia