TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድርቅ #ትግራይ
" ከምበላባቸው ቀናት #ጦሜን የማድርባቸው ቀናት ይበዛሉ " - የሰንዓለ ነዋሪ
" በድርቅ ምክንያት 6 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ ... 89 ከመቶ ነዋሪ በከባድ የደርቅ አደጋ ላይ ይገኛል " - ዒስራ ዓዲ ወጀራት ወረዳ
በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዒስራ ዓዲ ወጀራት ወረዳ ባጋጠመው ድርቅ ምክንያት 6 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
ፅ/ቤቱ ፤ በወረዳው ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ያጋጠመው ድርቅ በጊዜው ካልተገታ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።
ወ/ሮ ኣልጋነሽ ከበደ በወረዳው የሰንዓለ ነዋሪ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው።
ወ/ሮ ኣልጋነሽ ፤ ከማሳቸው የሚያገኙት ገቢ ከአመት አመት ስለማይመግባቸው ድሮውኑ በሴፍትኔት እገዛ ሲተዳደሩ ነበር።
በጦርነቱ ምክንያት የሴፍትኔት አገልግሎት በመቆሙ የዘንድሮ ድርቅ መቋቋም አቅቷቸዋል። በዛ ላይ አህታቸው በረሃብ ምክንያት በመሞትዋ ሁለት ልጆችዋን የመንከባከብ ሃላፊነት በእሳቸው ላይ ወድቀዋል።
ወ/ሮ ኣልጋነሽ ችግሩ የሚይዙት የሚጨብጡት አሳጥቷቸው ከሚበሉባቸው ጦማቸው የሚያድሩባቸው ቀናት እንደሚበዙ ተናግረዋል።
ከወረዳዋ ሰንዓለ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ብቻ ድርቅ ባስከተለው ችግር ቄያቸው ጥለው ከተሰደዱ 40 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች አንድዋ ወ/ሮ ፎቴን ኣባዲ ናቸው።
በድርቁ ምክንያት ከማሳቸው ያገኙት ገቢ ባለመኖሩ ፣ በዛ ላይ ከምግባረ ሰናይ ተቋማትና መንግስት የሚሰጥ እርዳታ በመቆሙ ቤታቸው ቆልፈው እግራቸው ወደ መራቸው ተሰደዋል።
ድርቅ ባስከተለው ረብ አስከአሁን 6 ሰዎች መሞታቸው የሚገልፁት የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሃሪፈያ ግደይ ፤ የወረዳው 89 ከመቶ ነዋሪ በከባድ የደርቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
የምግባረ ሰናይ ድርጀቶች የፌደራልና የክልሉ መንግስታት ችግሩ በመረዳት ቶሎ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀረቡት ሃላፊዋ ፣ በተለይ እናቶችና ህፃናት ታሳቢ ያደረገ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲደረግ ማሳሰባቸውን የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማድረግ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያጋጠመው ደርቅ የሚመለከት ተከታታይ መረጃዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆን ፤ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ሶስት ወረዳዎች ባጋጠመ የድርቅ አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ የመንግስት አካላት መናገራቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
@tikvahethiopia