TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ላለፉት 5 ቀናት #ዝግ ሆኖ የቆየው አማራ ክልልን ከትግራይን ክልል የሚያገናኘው መንገድ መከፈቱን ነዋሪዎች ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮ- ኤርትራ ድንበር፦

የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ሊያ ካሳን ትላንት ማምሻውን ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰርት በስልክ እንደተናገረችው፦ "በዛላምበሳ እና ራማ በኩል ያለው ድንበር እስካሁን ግልፅ ባልሆነልን ምክንያት #ዝግ ሆኗል። ጉዳዩን ለፌደራል መንግስት አሳውቀን መልስ እየጠበቅን ነው።"

የውጭ ጉዳዩ አቶ መለስ: "የኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ስለመዘጋቱ መረጃ የለኝም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀዋሳ‼️

ነገ ለሚደረገው #ሰላማዊ_ሰልፍ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ ከዞን ፖሊስ፣ ከክልሉ ልዩ ሃይልና #ከፌደራል_ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ሰልፉ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች በቂ ጥበቃ ያደርጋል። ከሪፈራል አደባባይ ጠዋት አንድ ሰዓት የሚጀመረው ሰላማዊ ሰልፍ መዳረሻው ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም ነው፡፡

ሰልፉ ወደ ብሉናይል የሚያወጣውን አስፓልት ይዞ ተስፋዬ ግዛው ህንጻ አደባባይ ሲደርስ ወደ ሃዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚገባና ማጠቃለያውን እንደሚያደርግ ተናግሯል። በዚህ ምክንያት መንገዶቹ ለተሸከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ እንዲሁም በበቂ የፀጥታ ሃይል ጥበቃ ይደረጋል፡፡ የከተማው ነዋሪ በሰልፉ ምክንያት #ስጋት ውስጥ እንዳይገባ በየክፍለ ከተማው #ውይይት መደረጉ ተገልጿል፤ ህዝቡም ለሰልፉ ሰላማዊነት #የበኩሉን እንዲወጣ ተጠይቋል፡፡

በተጨማሪ፦

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ #ሀሰተኛ_መረጃዎች ራሱን እንዲያርቅ ጥሪ ቀርቧል። ነዋሪው ምንም አይነት ሰላም የማደፍረስ እንቅስቃሴ ካየ ለፀጥታ ሀይሉ #ጥቆማ እንዲያደርስ ጥሪ ተላልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በእድሳት ምክንያት እስከ ግንቦት 01 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ #ዝግ ስለሚሆን ትርዒቶች #እንደማይቀርቡ አስታውቋል። እድሳቱን የሚያደርገው የአውሮፓ ህብረት ነው።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዝግ_ነው #ሀምሌ22

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ ሀምሌ 22 በሚካሄደው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ስለሚሳተፉ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ዝግ ሆነው ይውላሉ።

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ የሚዘጉ መንገዶች!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ለሚደረግላቸው የክብር አቀባባል ሥነ-ሥርዓት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች የተለመደውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላለፈ፡፡

ታህሳስ 02/2012 ዓም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኖርዋይ ኦስሎ ቆይታቸውን አጠናቅቀው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በሚደረግላቸው የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ላይ በርካታ የከተማችን ነዋሪዎች እና የውጭ ሀገር ዕንግዶች በተገኙበት የአቀባባል ሥነ-ሥርዓት ስለሚደረግ በመንገዶች ላይ የትራፈክ መጨናነቅ አንዳይከሰትና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሠረት፡-ነገ ታህሳስ 02 ቀን/2012 ከለሊቱ 11፡00 ሰዓት ጀምሮ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ እስከ ሚጠናቀቅ ድረስ ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ጀምሮ እስከ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት ባሉት ግራና ቀኝ መንገዶች ላይ ተሸከርካሪን ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ማቆም የተከለከለ ሲሆን ፡-አሽከርካሪዎችም አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

• ከኡራኤል ቤ/ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ወደ መስቀል አደባባይ

• ከቦሌ ኤድናሞል ወደ ቦሌ ዓለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ

• ከብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፤ ከፍል ውኃ ፤ ከለገሀር ፤ከካሳንችስ፤ከሳንጆሴፍ ትምህርት ቤት ፤ከስታዲየምንና ከሃራምቤ ሆቴል አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው #ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-12-11-3

@tikvahethiopiaBot
ደቡብ ኮሪያ በምሽት መዝናኛ ውስጥ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገች ነው!

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት በሴዑል በአንድ የምሽት መዝናኛ ውስጥ የተቀሰቀሰውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው።

የደቡብ ኮሪያ የበሽታ መቆጣጠር እና መከላከል ማዕከል ቅዳሜ ዕለት በቫይረሱ የተያዙ አዲስ 18 ሰዎች ተገኝተዋል ብሏል።

ከእነዚሀም መካከል 17 ወደዚህ የምሽት ክበብ ያቀኑ ናቸው። ለሰዎቹ በበሽታው ለመያዝ ምክንያት ነው የተባለ አንድ የ29 ዓመት ወንድ ተለይቷል።

የሀገሪቱ ጤና ባለስልጣናት ወደ ምሽት ክበቡ የሄዱ ሰዎች እራሳቸውን እንዲያገሉ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ወደ ምሽት ክበቡ ካቀኑ ሰዎች ጋር ግንኙነት ሊኖራቸው የሚችሉ ሰዎችን በመለይት ላይም ናቸው።

የሴዑል ከንቲባ በከተማዋ የሚገኙ መጠጥ ቤቶችና የምሽት መዝናኛ ክበቦች ላልተወሰነ ጊዜ #ዝግ እንዲሆኑ አዘዋል። "የሰዎች ቸልተኝነት ቫይረሱ እንዲቀሰቀስ ያደርጋል" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ #የሚዘጉ_መንገዶች

የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዕለቱ በ #ምኒሊክ_አደባባይ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የአከባበር ስነ ስርዓቱ እንደሚጀምር ፖሊስ የገለፀ ሲሆን ከዚያ በመቀጠል ወደ አድዋ ድልድይ የእግር ጉዞ እንደሚደረግና ዋናው ስነ ስርዓት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወን አሳውቋል።

በመሆኑም ፦

👉 በምኒሊክ አደባባይ በሚከናወነው የአከባበር ስነ ስርዓት ምክንያት ፦

• ከሰሜን ሆቴል ትራፊክ መብራት ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከዮሀንስ መብራት ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከጊዮርጊስ ቴሌ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከሀገር ፍቅር መታጠፊያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከብሪቲሽ ካውንስል ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከሲኒማ አምፒር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከእሪ በከንቱ ( እሪ በስራ) ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአራዳ ህንፃ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከሰባራ ባቡር ቶታል ወደ ጊዮርጊስ ቴሌ መስቀለኛ
• ከዳትሰን ሰፈር መገንጠያ ወደ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡

👉 ከምኒሊክ አደባባይ ወደ አደዋ ድልድይ የእግር ጉዞ በማድረግ በአድዋ ድልድይ የሚከናወነው ስነ ስርኣት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፦

• ከእንግሊዝ ኤምባሲ ትራፊክ መብራት ወደ አድዋ ድልድይ
• ከፈረስ ቤት ኮንደሚኒየም መታጠፊያ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከምስራቅ መገንጠያ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከሴፍቲ መብራት ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከ22 አደባባይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከቺቺኒያ ወደ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከካዛንቺስ ቶታል ወደ አቧሬ
• ከድሮው ሰንደይ ማርኬት ወደ ሴቶች አደባባይ
• ከሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከአቧሬ ጀርመን አደባባይ ወደ ሴቶች አደባባይ ያሉት መንገዶችን ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ #ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

👉 በመስቀል አደባባይ የሚከናወነው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፦

• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከፒኮክ ትራፊክ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ባምቢስ
• ከጥላሁን አደባባይ( መሿለኪያ) ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር
• አልሳምጨለለቅ ህንፃ ወደ ለገሀር
• ከገነት መብራት ወደ ለገሀር
• ከጠማማ ፎቅ (ገነት ሆቴል) ወደ ሜክሲኮ
• ከሱዳን ኤምባሲ (ጠማማ ፎቅ) ወደ ሜክሲኮ
• ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ወደ ሜክሲኮ
• ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ
• ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም ወደ ለገሐር
• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቲያትር
• ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት መብራት
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን መብራት
• ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኢምግሬሽን መብራት(ፖስታ ቤት)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ
• ከሚያዚያ 27 አደባባይ (4 ኪሎ) ወደ ፓርላማ መብራት
• ከጥይት ቤት ወደ ግቢ ገብርኤል
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ አሽከርካሪዎች #ሌሎች_አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።

ከነገ እሮብ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሸከርካሪን #አቁሞ_መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አዲስ_አበባ #የሚዘጉ_መንገዶች የካቲት 23 ቀን 2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በዕለቱ በ #ምኒሊክ_አደባባይ በመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ለበዓሉ መታሰቢያ ጉንጉን አበባ በማስቀመጥ የአከባበር…
#ማስታወሻ

ነገ የካቲት 23/2015 ዓ/ም የሚከበረው 127ኛው የአድዋ ድል በዓልን ምክንያት በማድረግ የበዓሉ ስነ ስርዓት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

👉 በምኒሊክ አደባባይ በሚከናወነን የአከባበር ስነ ስርዓት ምክንያት  ፦

• ከሰሜን ሆቴል ትራፊክ መብራት ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከዮሀንስ መብራት ወደ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ
• ከአፍንጮ በር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከጊዮርጊስ ቴሌ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከራስ መኮንን ድልድይ ወደ ደጎል አደባባይ
• ከሀገር ፍቅር መታጠፊያ ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከብሪቲሽ ካውንስል ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከሲኒማ አምፒር ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከእሪ በከንቱ ( እሪ በስራ) ወደ ጊዮርጊስ አደባባይ
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአራዳ ህንፃ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከአቡነ ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ወደ ምኒሊክ አደባባይ
• ከሰባራ ባቡር ቶታል ወደ ጊዮርጊስ ቴሌ መስቀለኛ
• ከዳትሰን ሰፈር መገንጠያ ወደ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ስነ ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚደረጉ ይሆናል ፡፡

👉 ከምኒሊክ አደባባይ ወደ አደዋ ድልድይ የእግር ጉዞ በማድረግ በአድዋ ድልድይ የሚከናወነውን ስነ ስርኣት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ  ፦

• ከእንግሊዝ ኤምባሲ ትራፊክ መብራት ወደ አድዋ ድልድይ
• ከፈረስ ቤት ኮንደሚኒየም መታጠፊያ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከምስራቅ መገንጠያ ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከሴፍቲ መብራት ወደ ምስራቅ አጠቃላይ
• ከ22 አደባባይ ወደ ዘሪሁን ህንፃ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከቺቺኒያ ወደ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከካዛንቺስ ቶታል ወደ አቧሬ
• ከድሮው ሰንደይ ማርኬት ወደ ሴቶች አደባባይ
• ከሴቶች አደባባይ ወደ አድዋ ድልድይ
• ከአቧሬ ጀርመን አደባባይ ወደ ሴቶች አደባባይ ያሉት መንገዶችን ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ #ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

👉 በመስቀል አደባባይ የሚከናወነው የበዓሉ አከባበር ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ፦

• ከመገናኛ  ወደ መስቀል አደባባይ
• ከዘሪሁን ህንፃ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአትላስ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከፒኮክ ትራፊክ መብራት ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ኡራኤል
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ ባምቢስ
• ከጥላሁን አደባባይ( መሿለኪያ) ወደ ሴንጆሴፍ ት/ቤት
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ 
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድ  ወደ ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን መስቀለኛ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር
• አልሳምጨለለቅ ህንፃ ወደ ለገሀር
• ከገነት መብራት ወደ ለገሀር
• ከጠማማ ፎቅ (ገነት ሆቴል) ወደ ሜክሲኮ
• ከሱዳን ኤምባሲ (ጠማማ ፎቅ) ወደ ሜክሲኮ
• ከአፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት ወደ ሜክሲኮ
• ከዲአፍሪክ ሆቴል ወደ ሜክሲኮ
• ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንዶሚኒየም ወደ ለገሐር
• ከጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቲያትር
• ከሜትሮሎጂ ወደ ፖስታ ቤት መብራት
• ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ኢምግሬሽን መብራት
•  ከጎላ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢምግሬሽን
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ወደ ኢምግሬሽን መብራት(ፖስታ ቤት)
• ከንግድ ማተሚያ ወደ ኦርማ ጋራዥ
• ከሚያዚያ 27 አደባባይ (4 ኪሎ) ወደ ፓርላማ መብራት
• ከጥይት ቤት ወደ ግቢ ገብርኤል
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል  የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ አሽከርካሪዎች #ሌሎች_አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።

ከዛሬ ረቡዕ የካቲት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በተገለጹት መንገዶች ላይ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓታት ተሸከርካሪን #አቁሞ_መሄድ የተከለከለ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Wolaita

ነገ ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ/ም በዎላይታ ዞን የድጋሜ ሕዝበ ውሳኔ ምርጫ (ሪፈረንደም) ድምፅ አሰጣጥ ይካሄዳል።

ስለ ሪፈረንደሙ ምን እናውቃለን ?

- የመራጮች ምዝገባ እና የድምፅ መስጠት ሂደት በአንድ ቀን የሚደረግ ይሆናል።

- የቀረቡት ሁለት አማራጮች ናቸው። እነሱም ፦

ነጭ እርግብ ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #እንደግፋለሁ

ጎጆ ቤት ፦ የ6ቱ ዞኖች (ኮንሶ፣ ዎላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋሞ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና የ5ቱ ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ደራሼ) በአንድ የጋራ ክልል መደራጀትን #አልደግፍም

- ድምፅ መስጠት የሚጀመረው ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ነው።

- በ1,812 የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ድምፅ ይሰጣል ፤ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል።

- ከአዲስ አበባ 5,215 ፤ ከዎላይታ ዞን 3,845 ተመልምለው በቦርዱ የሰለጠኑ አስፈፃሚዎች በምድብ ጣቢያዎቻቸው ላይ ይገኛሉ።

- ከነገ ድምፅ የመስጫ ቀን ጋር በተያያዘ በዞኑ በሚገኙ የፌዴራል እና የክልል መንግስታዊ ተቋማት ስራ አይኖርም።

- ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት #ዝግ ሆነው ይውላሉ።

- የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሆስፒታሎችን ጨምሮ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት …ወ. ዘ. ተ) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ ማከናወን ይችላሉ። እንዲዘጉ አይገደዱም።

- የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Tigray #Update

ከጥቅምት 3 እስከ 5/2016 ዓ.ም ተፈፃሚ የሚሆነው የትግራይ የሃዘን ቀን ማሰፈፀምያ መመሪያ ይፋ ሆነ።

ከመስከረም 21/2016 ዓ/ም ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆንና የጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕረዚደንት ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ ፊርማ ያረፈበት 18 አንቀፆችን የያዘ የትግራይ የሃዘንና መርዶ " መመሪያ ቁጥር 022016 " ምን ይላል ? 

የመርዶና የሃዘን ስነ-ሰርአቱ ጥቅምት 2 ታውጆ ከጥቅምት 3 እስከ 5 የሃዘን ቀናት ይሆናል። ጥቅምት 6 /2016 ዓ.ም የሃዘን ቀን ስነ-ሰርአቱ ያበቃል።

ከጥቅምት 3 እስከ 5 /2016 ዓ.ም በሚኖሩ የሃዘን ቀናት በመመሪያ የተከለከሉና በህግ የሚያስቀጡ ዝርዝር ተግባራት ተቀምጠዋል።

1ኛ. ስፓርታዊ ጨወታዎች ጨምሮ ድምፅ የሚፈጥር ንግዳዊና ንግዳዊ ያልሆነ ተግባር የተከለከለ ነው።  

2ኛ. ቀንና ማታ በሙዚቃ በመታጀብ የሚሰሩ መጠጥ ቤቶች ፣ የቡናና ተመሳሳይ የሽያጭ አገልግሎት የሚሰጡ ዝግ ይሆናሉ።

3ኛ. ሰርግ ፣ የህፃናት ክርስትና ፣ ልደትና የመሳሰሉ ድምፅ የሚፈጥሩ ተግባራት አይፈቀዱም። 

4ኛ. ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው። 

በትግራይ ደረጃ የሚከናወነው የሃዘን ቀን ስነ-ሰርአት ተጠናቆ ተለዋጭ መመሪያ እስከሚሰጥ ድረስ ፍፁም የተከለከሉና በህግ የሚያስቀጡ ተግባራት የሚከተሉት ናቸው። 

1ኛ. የተሰዋ ታጋይ አስከሬን ካረፈበት ቦታ ማንሳትና ማዘዋወር የተከለከለ ነው።

2ኛ. የተሰዋ ታጋይ ሃወልት መገንባት ወይ ደግሞ ያረፈበት መቃብር ማሻሻልና መለወጥ የተከለከለ ነው።

3ኛ. የተሰዋ ታጋይ አስከሬን ያረፈበት ቦታ መጠቆምና ከቦታው ለማንሳት ጥቅም መጠየቅና መቀበል የተከለከለ ነው።

4ኛ. የተሰዋ ቤተሰብ ክብርና መንፈስ የሚጎዳ ፣ የሚያደበዝዝ ተግባር መፈፀም የተከለከለ ነው።

5ኛ. አገልግሎት ሰጪ የግል ድርጅቶች ሳይጨምር መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት #ዝግ ይሆናሉ።

በመመሪያ የተጠቀሱ ህጎች የማያከብሩና የሚጥሱ ግለሰቦችና ተቋማት ከ10 ሺህ እስከ 50 ሺህ ቅጣት የተቀመጠ ሲሆን ቅጣቱን ለማስፈፀም የፓሊስና የፍትህ አካላት ያካተተ 8 ኣባላት ያሉት ግብረ ሃይል በወረዳና ቀበሌ ደረጃ መቋቋሙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

#TikvahEthiopiaMekelle

@tikvahethiopia
#ዎላይታ

“ ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው ” - አንድ የጤና ባለሙያ

“ ዞኑም፣ ከተማ አስተዳደሩም ሆስፒታል ቢኖር የሚል ሀሳብ አለው ” - የወላይታ ሶዶ ዞን ጤና መምሪያ።

በወላይታ ዞን የሚገኙ አንድ የጤና ባለሙያ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦ " የቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ የመንግሥት ሆስፒታል ባለመኖሩ ሕዝቡ እስከ ሞት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ነው " ብለዋል።

" እንደ አገር የሚተገበረው የሕዝብ ጤና ተቋማ ጥምርታ ሌሎች አካባቢዎች ላይ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ያለ ቢሆንም ለቦሎሶ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ግን ተግባራዊ አልሆነም " ሲሉ ወቅሰዋል።

" የሕዝብ ብዛት ከ1 ሚሊዮን እስከ 1.5 ሚሊዮን ከሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ተሰርቶ አገልግሎት መሰጠት እንዳለበት ይገለጻል። የቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ ሕዝብ ከ1 ሚልዮን እንደሚበልጥ ይገመታል። ህዝቡ ግን ይህንን ሰብአዊ መብት ለማግኘት አልታደለም " ብለዋል።

ለተነሳው ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የወላይታ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ኤካ አነጋግሯል።

ምን መለሱ ?

አረካ እና ቦሎሶ ሶሬን አማክሎ አገልግሎት የሚሰጥ ዱቦ የመጀመሪያ ደረጃ የግል ሆስፒታል አለ። የሕዝቡ ቅሬታ ‘የመንግሥት ሆስፒታል ለምን አይኖርም’ የሚል ነው ቅሬታው አግባብነት ያለው ነው።

ሌሎችም ምንም አይነት ሆስፒታል የሌለባቸው አካባቢዎች ላይ ቅድሚያ ተሰጥቶ የመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እየገነባ ነው የቆየው ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ይኼኛውም አካባቢ (ቦሎሳ ሶሬ ወረዳ እና አረካ ከተማ) በመንግሥት ሆስፒታል ተደራሽ ቢሆን ጥሩ ነው የሚለውን እንደ ዞን መግባባት ላይ እየደረስን ነው።

እንደ ዞን፣ የከተማ አስተዳደርም ይሄ ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ እንደሆነ ተቀብሏል። ጥያቄው እንደ ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን፤ ለግንባታው የሚያስፈልገው በጀት እንዲታቀድበት፣ በመደበኛ የመንግሥት በጀት እንዴት መስራት እንደሚቻል እየታሰበበት ነው።

በሌላ በኩል ቅሬታ አቅራቢ ጤና ባለሙያው በበኩላቸው፣ “ ለህዝብ ተሰርቶ አገልግሎት እንዲሰጡ የተሠሩ ጤና ጣቢያዎች ቢኖሩም ብዙዎቹ #ዝግ_ናቸው” ብለዋል።

አንድ የግል ሆስፒታል ቢኖርም ለመታከም የዋጋ መናር እንደሚስተዋልበት፣ የብቁ ቀዶ ጥገና ችግር እንዳለ፣ በዚህም አንዲት እናት ችግር እንደደረሰባቸው፣ የጤና ባለሙያዎች ከሰለጠኑበት ሙያ ውጪ ስለሚሰሩ ከዚህ በፊት ሁለት እናቶች እንደሞቱ አስረድተው፣ ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ይህንኑ ቅሬታ በተመለከተ የዞኑ ጤና መምሪያ ቢሮ  ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ምን ምላሽ ሰጡ ?

ትክክል ነው። ያለው ሂደት አጠቃላይ ዝርዝሩን እኛም ይዘናል። ሕዝቡም ያነሳል፣ ትክክል ነው። የሕክምና ባለሙያዎች (የዱቦ ሆስፒታል) አሁን በቂ እውቀት ያላቸው ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ነው። አጋጣሚ የተፈጠሩ ክፍተቶች ለምን ተፈጠሩ የሚለውን እናያለን።

በእኛ ደረጃ ዝግ የሆነ ጤና ጣቢያ የለም። ጤና ባለሙያ ተመድቦ ሁሉም ጤና ባለሙያዎች አገልግሎት እየሰጡ ነው በሥራ ሰዓት። ግን አልፎ አልፎ ከትርፍ ሰዓት ክፍያ በጊዜ ባለመከፈሉ ምክንያት ‘አልተከፈለም’ በሚል ሥራ ቦታ ላይ የባለሙያ አለመገኘት ሁኔታዎች አሉ።

የጤና ባለሙያው በበኩላቸው ፦
- የትርፍ አበል አለመከፈል፣
- በደመወዝ መቆራረጥ ምክንያት ቅሬታ ስላለ፣ ሌጋማ፣ ዎይቦ፣ ጋራ ጎዶ፣ ባንጫ እና ሌሎች ጤና ጣቢያዎች በቀን አንድ ባለሙያ ገብቶ የሚመጡ ሕሙማንን ወደ ሆስፒታል እንዲሄዱ መረጃ ከመስጠት ውጭ የሚሰጠዉ አገልግሎት የለም " ብለዋል።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ መንገዶች ይዘጋሉ።

በአዲስ አበባ ' መስቀል አደባባይ ' ነገ #ቅዳሜ ከሚደረግ የድጋፍ ሰልፍ ጋር በተያያዘ መንገዶች እንደሚዘጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ከንጋቱ 11፡00 ሰአት ጀምሮ ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ ፦

- ከቴዎድሮስ አደባባይ በብሄራዊ ቴአትር ወደ ወደ መስቀል አደባባይ ሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ

- ከኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል አደባባይ ላይ

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ እና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ መስቀል አደባባይ አጎና ሲኒማ

- ከቅ/ቂርቆስ ቤ/ክርስቲያን በአዲሱ መንገድ  ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ ለገሀር መብራት

- ከሜክሲኮ ወደ መስቀል አደባባይ ቴሌ   ለሚጓዙ ለገሀር መብራት

- ከጌጃ ሰፈር አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ሰንጋተራ ትራፊክ መብራት ላይ

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA ሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ለተሽከርካሪ #ዝግ ይሆናሉ ተብሏል።

አሽከርካሪዎች መንገዶቹ እንደሚዘጉ አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ከዚህ ባለፈ በተጠቀሱት መንገዶች ከዋዜማው ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሰልፉ ፍፃሜ ድረስ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ወይም ማሳደር ተከልክሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የነገው የመስቀል አደባባይ ሰልፍ #መንግሥትን የሚደግፍ ሰልፍ መሆኑን ለማወቅ ችሏል።

@tikvahethiopia
#አዲስአበባ #መታወቂያ

“ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” - CRRSA

ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው አዲስ አበባ ከተማ ለመጡ ተገልጋዮች የመታወቂያ አገልግሎት በቅርብ ጊዜ መሰጠት ይጀመራል ተብሎ ነበር።

ነገር ግን እስካሁን አገልግሎቱ አልጀመረም።

ነዋሪዎችም መቼ እንደሚጀምር ጠይቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቼ ነው አገልግሎቱ መስጠት የሚጀምረው ? ሲል የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዮናስ አለማየሁን ጠይቋል።

እሳቸውም በሰጡት ምላሽ፣ “ በጣም በአጠረ ጊዜ ውስጥ እንጀምራለን ” ብለዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዝርዝር ምን አሉ ?

➡️ ከመሸኛ ጋር ተያይዞ ፣ ከክፍለ አገር ለሚመጡ ሙሉ ለሙሉ አገልግሎቱ #ዝግ አይደለም።

- በሕመም፣
- በትምህርት እድል፣
- ተጋቢዎች ሆነው ከሌላ ቦታ ሲመጡ እዚህ (አ/አ) አንዱ ተጋቢ ካለና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ከሆነ፣
- በሥራ ዝውውር ከሆነ እነዚህ ሁሉ አልተከለከሉም። የተፈቀዱ አገልግሎቶች ናቸው።

➡️ የተከለከለው፣ ያለ ምክንያት ዝም ብሎ ለሚመጣ ነዋሪ ነው። ያለ ምክንያት ስንል በእርግጥ በምክንያት የሚመጣ አለ። ግን አዲስ አበባ ውስጥ ያለውን አጠቃላይ ነዋሪ አገልግሎት ቁጥጥር ለማበጀት የተደረገ ነው።
 
ኃላፊው በሰጡት ቃል ፥ " መሸኛ አስገብተው መረጃዎችን እየተጠባበቁ ያሉትን ለማስተናገድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን አጠናቀናል " ብለዋል።

በጣም ባጠረ ጊዜ እንደሚጀመር አመልክተዋል።

" የገጠመን አንዱ ትልቅ ፈተና የነበረው (ለ15 ቀናት አካባቢ) አዲስ መዝጋቢ መመዝገብ ከባድ ሆኖብን ነበር፣ ቴክኒካል ችግር ተከስቶ። እሱን ፈትተናል " ያሉት አቶ ዮናስ " በዚህ ምክንያት አዲስ ተመዝጋቢ የሆኑ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የነበሩ ተገልጋዮች ቁጥራቸው ከፍ (አገልግሉቱን በመቋረጡ) ስላለ እሱን ማቅለል ስላለብን ነው። እሱን እንዳቀለልን እንጀምራለን " ሲሉ አስረድተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia