TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ

" በጸጥታ ችግር በሙሉና በከፊል የወደሙ 287 ትምህርት ቤቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ጥገና ያስፈልጋቸዋል" ሲል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ዘነበ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ "በጸጥታ ችግር በሙሉና በከፊል የወደሙ 287 ትምህርት ቤቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ጥገና ያስፈልጋቸዋል" ብለዋል።

"እንደሚታወቀው ክልሉ ከዚህ በፊት መተከልና ከማሽ ዞኖች አካባቢ የነበረውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በሙሉና በከፊል የወደሙ ትምህርት ቤቶች አሉ" ያሉት አቶ ምትኩ፣ "እነዚህን ትምህርት ቤቶች መልሶ የመገንባት አሁን ማኅበረሰቡ የጀመረው ሥራ አለ። መንግሥትም ደግሞ ራሱን አስችሎ ከባለ ሃብቶች፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ ትምህርት ቤቶችን የመጠገን ሁኔታ አለ" ሲሉ ተናግረዋል።

ወደሙ የተባሉት ተቋማት የት አካባቢ እንደሆነ እንዲያብራሩ ሲጠየቁም፣ በከማሽ፣ መተከል ዞኖች እዲሁም በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ መሆኑን ገልጸው፣ የወደሙት ትምህርት ቤቶች ብላክ ብርድ፣ ወንበር፣ ቤተ መጻሕፍት፣ አጋዥ መጻሕፍት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ውድመቱን ተከትሎ ምን ያህል ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ እንደሆኑ እንዲገልጹ ላቀረበላቸው ጥያቄ አቶ ምትኩ፣ "ወደ 50ሺሕ ገደማ ሕፃናት ናቸው በዚህ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑት" ብለዋል።
50 ሺሕ ገደማ ሕፃናት ሲባል በተለያዩ ምክንያቶች ለምሳሌ ቤተሰቦቻቸው በኢኮኖሚ ችግር ላይ በመሆናቸውና አብዛኛዎቹ ግን በአካባቢው ተፈጥሮ በነበረው የጸጥታ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ናቸው ሲሉ አክለዋል።

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጸጥታ ችግር ደረሰ ከተባለው የትምህርት ቤቶች ውድመት በተጨማሪ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በትግራይ ክልል ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው 2.4 ሚሊዮን ሕጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን፣ 1,218 ትምህርት ቤቶች ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ቢከፈቱም 722ቱ እንዳልተከፈቱ መረጃዎች የክልሉ ትምህርት ቢሮ በተለያዩ ወቅቶች ሲገልጽ ተስተውሏል።

በአፋር ክልል ከሰሜኑ ጦርነት ጋር በተያያዘ ሙሉ ለሙሉ ከወደሙ 65 ትምህርት ቤቶች አምስቱ መልሶ ግንባታ እንደተደረገላቸው፣ በከፊል ከወደሙት 694 ትምህርት ቤቶች መካከል 34ቱ እንደተጠገኑ እንዲሁም በ2016 የትምህርት ዘመን ይመዘገባሉ ተብሎ ከታቀደው 245 ሺሕ ተማሪዎች እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ የተመዘገቡት 126 ሺሕ ተማሪዎች መሆናቸው ተመላክቶ ነበር።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-09

@tikvahethiopia