TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
#Update

አሜሪካ ዩጋንዳ ላይ እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠነቀቀች።

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ፤ ኡጋንዳ ትላንት ያፀደቀችውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን #ወንጀል የሚያደርገውን ህግ " አሳፋሪ እና ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት " በማለት ተቃወሙ።

ባይደን ፤ " ይህ አሳፋሪ ድርጊት / ሕጉ መፅደቁን / በዩጋንዳ ውስጥ ያለው አስደንጋጭ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ሙስና የቅርብ ጊዜ እድገት አመላካች ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዜዳንት ባይደን ፤ የአሜሪካ ብሄራዊ ደኅንነት ም/ ቤት የዩጋንዳው ሕግ አሜሪካ ከአገሪቱ ጋር ባሏት ግንኙነቶች ላይ ምን አንድምታ እንዳለው አጥንቶ እንዲያቀርብ አዘዋል ተብሏል።

ከህጉ ጋር በተያያዘ ፤ አሜሪካ ለኡጋንዳ የምትሰጠውን እርዳታና ኢንቨስትመንት ልታቆም እንደምትችል ባይደን አስጠንቅቀዋል።

የሕጉን ተፅኖ ከግምት በማስገባትም የዩጋንዳ የአጎዋ (AGOA) ተጠቃሚነት እንደሚገመገም አሳውቀዋል።

ፕሬዜዳንቱ በከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ ወይም ሙስና ውስጥ በተሳተፈ ማንኛውም ሰው ላይ #ማዕቀብ እና ወደ አሜሪካ የመግባት #እገዳን ጨምሮ ተጨማሪ እርምጃዎችን እያጤኑ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ከባይደን በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን ፤ ህጉን ተቃውመዋል ፤ መስሪያ ቤታቸውም የአሜሪካ ዜጎች ወደ ዩጋንዳ በሚያደርጉት ጉዞ ላይ መመሪያ እንዲያወጣ አዘዋል።

የባይደን አስተዳደር የዩጋንዳ ፓርላማ አፈ ጉባኤ " አኒታ አሞንግ " አሁን ያላቸውን የአሜሪካ መግቢያ ቪዛ መሰረዙ ሮይተርስ ፣ እንዲሁም ዘ ኢስት አፍሪካን ዘግበዋል።

ከዚህ ቀደም የዩጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ምንም እንኳን ምዕራባውያን ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት (ተመድን ጨምሮ) ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ በዩጋንዳ ምድር የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን ወንጀል በሚያደርገው ረቂቅ ሕግ ላይ ፊርማቸውን እንዳያኖሩና እንዳያፀድቁ ማስጠንቀቂያዎችን ቢሰጡም ፕሬዜዳንቱ ትላንት መጠነኛ ማሻሻያ የተደረገበትን ሕግ በፊርማቸው በማኖር #አቅፅድቀውታል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Hawassa በሀዋሳ ከተማ በሚገኝ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ሜላት መሀመድ ትላንት ሰኔ 5/2015 ዓ.ም ቀትር ላይ በሁለት ተሽከርካሪ በመጡ ግለሰቦች 'መጠለፏን' ቤተሰቧቿ ተናግረዋል። የ14 ዓመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ሜላት ከትምህርት ቤት ወደ ወደ መኖሪያ ቤቷ በመመለስ ላይ እያለች በሀዋሳ ከተማ ሞኖፖል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ " ቤት ልትደርስ ጥቂት ሜትሮች ሲቀራት " በሃይል ታግታ…
" የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች " - የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ

ሐዋሳ ከተማ ውስጥ ታዳጊ ሜላት መሐመድን በመጥለፍ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የሐዋሳ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን ግለሰብ ትናንት እሁድ ምሽት 5: 30 አካባቢ  ይርጋለም ከተማ ዉሃ ልማት ቀበሌ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ ተሸሽጎ መገኘቱን ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ አየለ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ ተናግረዋል።

በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠረው ሳምሶን ሸኑ የተለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ የወንጀል ማጣራት ስራ እየተከናወ እንደሚገኝ ረዳት ኢንስፔክተር መልካሙ ገልጸዋል።

የጠለፋ ወንጀሉ ሰለባ የሆነችው ታዳጊ ለህክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዷን በማከል።

ታዳጊዋ ከጠለፋ መለቋቋን ታላቅ ወንድሟ እንዳልካቸው አስራትም አረጋግጧል።  ታዳጊዋ በሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት እያገኘች እንደምትገኝም ገልጿል።

ታዳጊ ሜላት መሐመድ ፤ ከቀናት በፊት በሐዋሳ ከተማ #በኃይል ወደ ተሽከርካሪ እንድትገባ ተደርጋ መወሰዷን ቤተሰቦቿ መግለፃቸው ይወሳል።

በወቅቱ የአካቢው ሰው ሊታደጋት መሞከሩን፤ ሜላት ስትጮህም ይዟት የጠፋውን መኪና የፊትለፊቱን መስታወት የአከባቢው ሰው መሰባበሩን ፤ ከዛ በኋላ እየበረረ ማመለጡን የታዳጊዋ ቤተሰቦች ለቢቢሲ አማርኛ አገልግሎት መግለፃቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አፅድቀውታል ፤ ፈርመውበታል ! ዩጋንዳ የ " ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት " ን ወንጀል የሚያደርገውን ሕግ አፀደቀች። ዛሬ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ያፀደቁት / ፊርማቸውን ያኖሩበት የረቂቅ አዋጅ ሕግ ተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት የሚፈጽሙ ሰዎችን ሁሉ በዕድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጣ ነው። በአንዳንድ ሁኔታዎች ዳግሞ #የሞት ቅጣትን የሚያስከትል ነዉ። ረቂቅ ሕጉ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ በአገሪቱ…
" ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት የተሞላበት ነው " - ኡጋንዳ

የዓለም ባንክ ለኡጋንዳ አዲስ ብድር አልሰጥም ብሏል።

ይህን ያለው ለምን የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ህግን አውጥተሽ ተግባራዊ አደረግሽ በሚል ነው።

የዓለም ባንክ ኡጋንዳ ያወጣችው ሕግ " መሰረታዊ ከሆኑ እሴቶቼ ጋር ይቃረናል " ብሏል።

ተቋሙ ለሁሉም ኡጋንዳውያን ያለምንም ልዩነት " ከድህነት እንዲወጡ፣ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲያገኙ እና ሕይወታቸውን እንዲያሻሽሉ ለመርዳት " ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል።

በኡጋንዳ ከዚህ ቀደምም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነቶች ሕገ ወጥ የነበሩ ሲሆን ግንቦት ላይ በጸደቀው አዲሱ ሕግ መሰረት ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራትን ጨምሮ #ሞት ያስቀጣል።

በኡጋንዳ ተግባራዊ በተደረገው የፀረ ተመሳሳይ ጾታ ሕግ ፤ ከ18 ዓመት በታች ከሆነ ሰው ጋር የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የፈጸመና የኤችአይቪ ቫይረስ በደሙ ከሚገኝበት ሰው ጋር ግኝኑነት የፈጸመ ሰው እስከወዲያኛው ይሸኛል / የሞት ቅጣት ይፈረድበታል።

ዓለም ባንክ ይህ ሕግ ተግባራዊ ከተደረገ በኃላ አንድ ቡድን ወደ ኡጋንዳ አሰማርቶ የነበረ ሲሆን ሕጉ " በመሰረታዊነት የዓለም ባንክ ቡድን እሴቶችን ይቃረናል " ብሏል።

ራዕያችን " ዘር፣ ጾታ ወይንም ተመሳሳይ አፍቃሪነትን ሳይለይ ሁሉንም ያካተተ ነው " ሲል ገልጿል።

በሕጉ ውስጥ የተካተቱ አዳዲስ እርምጃዎች እስኪገመገሙ ድረስ " ለኡጋንዳ አዲስ ብድር እንዲጸድቅ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ አይቀርብም " የሚል ውሳኔ አሳልፏል።

ኡጋንዳ ምን አለች ?

የዓለም ባንክ የወሰደው እርምጃ ኢፍትሃዊ እና ግብዝነት ነው ብላለች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኡጋንዳ አምባሳደር አምባሳደር አዶኒያ አየባሬ ፥ " የገንዘብ ተቋሙን እርምጃ በጣም የከፋ ነው። የዓለም ባንክ የአሰራር ዘዴ እና የቦርዱን ውሳኔ እንደገና የማጤን ጊዜው አሁን ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዲኤታ ኦኬሎ በበኩላቸው ፤ እርምጃው ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር ወጥነት የለውም ብለዋል።

" የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የማይታገሱ በርካታ የመካከለኛው ምስራቅ አገራት አሉ። ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችንም የሚቀጡት በመስቀልና በመግደል ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" በአሜሪካ ውስጥ በርካታ ግዛቶች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚቃወሙ ወይንም የሚገድቡ ሕጎችን አውጥተዋል። ታዲያ ለምን ኡጋንዳ ላይ አነጣጠራችሁ ? "ሲሉም ጠይቀዋል።

ከዓለም ባንክ በተጨማሪ አሜሪካ በጸረ ተመሳሳይ አፍቃሪ ሕግ ምክንያት በኡጋንዳ ላይ ማዕቀብ ጥላለች። (ሮይተርስ/ቢቢሲ)

ኡጋንዳ ፤ ሕጉን ከማፅደቋ በፊት ከምዕራባውያን ሀገራት እና ተቋማት ብዙ ማስጠንቀቂያዎች ቢደርሳትም ሕጉ ለሀገሬ አስፈላጊ ነው በማለቷ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፈርመውት አፅድቀውታል፤ ተግባራዊም ሆኗል።

ከዚህ ቀደም የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ፤ #ምዕራባውያን አገራት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን መብቶች #በአፍሪካ አገራት ላይ #በኃይል ለመጫን እየጣሩ ነው ሲሉ ተናግረው ነበር።

ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ  " እንግዳ የሆነ ባህል / ተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንድንፈቅድ ምዕራባዊያኑ #ማዕቀብ በመጣል ጫና ያሳድራሉ " ሲሉ ነበር የገለፁት።

ስለ ኡጋንዳ አዲሱ ሕግ ለማወቅ ፡ https://t.iss.one/tikvahethiopia/78787

@tikvahethiopia
#Rwanda #UK

ዩናይትድ ኪንግደም (UK) ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ #ሩዋንዳ ለማዛወር የያዘችው እና ከፍ ያለ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር የታመነው ዕቅድ የሃገሪቱ ሕግ ሊሆን እንደተቃረበ ቪኦኤ ዘግቧል።

የዕቅዱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ስደተኞቹን #በኃይል ከአገር የማስወጣቱን ውጥን ማገድ የሚችል አዲስ የሕግ መቋቋሚያ ለማበጀት እየሰሩ እንደሆነ ተነግሯል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን እገዳ ተጽዕኖ ለማስቀረት እና በላይኛው ምክር የቀረበውን ተቃውሞ ለመቋቋም የታለመው ይህ ሕግ በዚህ ሳምንት በሃገሪቱ ፓርላማ ይድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

‘ የሩዋንዳ ዕቅድ ’ የሚል ቅጽል የተሰጠው ይህ ውጥን ጠቅላይ ሚንስትር ሪሺ ሱናክ ‘ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደዚያች አገር የሚያጓጉዙ ጀልባዎች እንቅስቃሴ’ ለማስቆም ለገቡት ቃል ‘ወሳኝ እርምጃ ነው’ ተብሏል።

የሱናክ ቃል አቀባይ ዴቭ ፓሬስ ምን አሉ ?

" የእንግሊዝ ፓርላማ በያዝነው ሳምንት በሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ከፍተኛ እንግልት እና ብዝበዛ የሚፈጽምባቸውን ሰዎች ህይወት የሚታደግ ህግ የማጽደቅ እድል ያገኛል።

አሁን ባለው አካሄድ መቀጠል እንደማንችል ግልፅ ነው። በመሆኑም ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜው አሁን ነው። " ብለዋል።


በአነስተኛ ጀልባዎች ተጓጉዘው የእንግሊዝ ቻናልን በማቋረጥ ከዚያ የሚደርሱትን ጥገኝነት ጠያቂዎች ወደ ምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ ለማዛወር እና በቋሚነትም ኑሯቸውን በዚያ እንዲያደርጉ በማቀድ ሁለቱ አገሮች የተፈራረሙት ስምምነት 2 ዓመታት አስቆጥሯል።

በፍርድ ቤት የታገደው ዕቅድ እንግሊዝን በትንሹ 470 ሚሊዮን ዶላር ሊያስወጣት እንደሚችል ቪኦኤ በዘገባው አስፍሯል። #VOA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተፈናቃዮችን ወደ ቤታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ፤ ይህም ይቀጥላል " - የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት

የብሔራዉ የደኅንነት ምክር ቤት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ባጋጠመ ግጭት፤ እንዲሁም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች ባጋጠሙ የጸጥታ ችግሮች የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች እንዳሉ ገልጿል።

" እነዚህ ተፈናቃዮች ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ እየሠራን ነው " ብሏል።

" የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በጋራ ሠርተው ብዙዎችን ከመጠለያ ጣቢያ ወደ ቤታቸው እንዲመለሱ ተደርጓል " ሲልም ገልጿል።

" በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል፤ #በራያ እና #አላማጣ አካባቢ ከተፈናቀሉ ዜጎች መንግሥትን ሳይጠብቁ በማኅበረሰባዊ መተሳሰብ ብቻ በርካታዎች ወደ ቤታቸው እየገቡ ነው " ሲል አመልክቷል።

በዚህ ሂደት " የተፈናቃዮችን ጉዳይ እንደ ፖለቲካ አጀንዳ አድርገው ሊጠቀሙ የሚፈልጉ አካላት መኖራቸው ታይቷል " ብሏል።

ም/ቤቱ እነዚህ ኃይሎች እነማን እንደሆኑ በግልጽ በስም ጠርቶ ባይገልጽም " ተፈናቃዮቹ ወደ ቤታቸው እንዳይመለሱ ፕሮፖጋንዳና ማስፈራሪያ ይደረድራሉ " ብሏል።

" አንዳንዴም #በኃይል ጭምር የተፈናቃዮችን መመለስ ለማሰናከል ይቃጣቸዋል። " ሲል ገልጿል።

" መንግሥት ካለበት የሞራል እና የሕግ ኃላፊነት የተነሣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቤታቸውና ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ይቀጥላል " ሲል አሳውቋል።

https://t.iss.one/tikvahethiopia/87168?single

@tikvahethiopia