TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ትግራይ #ዓዲግራት

" ብርጌድ ንሓመዱ " የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቅስቃሴ በትግራይ ኢትዮጵያ ተቋቋመ።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ " ምምስራት ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ " ማለትም ' የብርጌድ ንሓመዱ  መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ምስረታ '  በሚል ርእስ በተለይ ኤርትራውያን በሚጠቀሙባቸው የማህበራዊ ትስስር ገፆች ሲዘዋወር ያገኘው የጥሪ ደብዳቤ በመያዝ #ሃቀኝነቱን ለማረጋገጥ ጥረት አድርጓል።

በትግርኛ ቋንቋ የተፃፈውና በማህበራዊ ትስስር ገፆች  የተሰራጨው ማህተምና ፊርማ  የሌለው በመላ ኢትዮጵያ ለሚኖሩ ኤርትራውያን የተፃፈው ደብዳቤ ሙሉ ቃል እንዲህ ይላል።

"... ይፋዊ  ምስረታ 'ብርጌድ ንሓመዱ ' መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ።

'ብርጌድ ንሓመዱ ' የተባለ የኤርትራውያን ህዝባዊ ማዕበል እንቅስቃሴ ለማጠናከር በምናካሂደው ህዝባዊ ስብሰባ እንድትሳተፉ በክብር ጥሪ እናቀርባለን።

        የስብሰባ ቦታ ዓዲግራት ትግራይ !!

                ሕጊ ይንገስ
               ምልኪ ይፍረስ !!
                ህግ ይንገስ
                አምባገነንነት ይፍረስ "

የጥሪ ደብዳቤውን በመከተል የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራት ተጓዘ ።

ስብሰባ ይካሄድበታል ወደ ተባለ ቦታ በመሄድ ከአስተባባሪዎች ተገናኘ። አስተባባሪዎቹ ለድህንነታቸው ሲባል ስማቸው ምስላቸውና በኤርትራ የየት አከባቢ ነዋሪዎች እንደነበሩ  ለመጥቀስ ፍቃደኞች አይደሉም።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከአስተባባሪዎቹ በመሆን ስብሰባ ወደ ተጠራበት ሰፊ አዳራሽ ይደርሳል። በሰፊ አዳራሹ ቁጥራቸው አነስተኛ ተሰብሳቢዎች ተገኙ።

አስተባባሪዎቹ ለጥንቃቄ ሲባል ፎቶ ማንሳትም ሆነ ድምፅ መቅረፅ አይፈቀድም ባሉት መሰረት የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ሪፓርተር የተባለውን በመቀበል ሰብሰባውን ተከታትሏል።

ይኸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባል እንደረጋገጠው 'ብርጌድ ንሓመዱ 'የተባለው የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣቶች እንቀስቃሴ ' ብርጌድ ንሓመዱ ጨንፈር ትግራይ መላእ ኢትዮጵያ ' ማለት የ 'ብርጌድ ንሓመዱ ' የመላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በይፋ በዓዲግራት ተቋቁመዋል። እንቅስቃሴው የሚያስተባብሩ አመራሮቹም መርጠዋል።

የእንቅስቃሴው አስተባባሪዎች እንዳሉት ፤ " ከ30 ዓመታት በላይ ያለ ህዝባዊ ምርጫ በአምባገነንነት ተቀምጠዋል " ያሉትን የኤርትራ መንግስት ለመጣል በመላ ዓለም በሚኖሩ ኤርትራውያን ወጣቶች እየተደረገ ያለው ትግል በመደገፍና በመቀላቀል ትግሉ በመላ ኢትዮጵያ በሚኖሩ ኤርትራውያን ተቀባይነት እንዲያገኝ አበክረው ይሰራሉ።

የ ' ብርጌድ ንሓመዱ  መላ ትግራይ ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ' በሚል የኤርትራ መንግስት የሚቃወም የወጣት ኤርትራውያን እንቅስቃሴ በይፋ የተመሰረተባት የትግራይዋ ዓዲግራት ከተማ ከኤርትራ ደንበር በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ትገኛለች ሲል ቲክቫህ ኢትጵያ የመቐለ ቤተሰብ ከዓዲግራት ዘግቧል። 

@tikvahethiopia