TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#VladimirPutin #NaredraModi
የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ ዛሬ BRICSን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ ያገኙትን እና በመጪው አዲስ አመት ወደ ተግባር የሚገቡትን አዳዲሶቹ የቡድኑ አባል ሀገራት፦
- ኢትዮጵያ፣
- አርጀንቲና፣
- ኢራን፣
- የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣
- ሳዑዲ አረቢያን
- ግብፅን " እንኳን ደስ አላችሁ " ሲሉ የደስታ መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል።
በሌላ በኩል ፤ ከBRICS መስራቾች አንዷ የሆነችው ሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ናሬድራ ሞዲ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የBRICS ቡድንን መቀላቀል" እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።
ሞዲ እንደ ንግድ፣ መከላከያ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ ኢትዮጵያ BRICSን እንድትቀላቀል ህንፍ ላደረገችው ድጋፍ አድናቆታቸውን ችረዋል።
በተመሳሳይ የቻይና መንግሥትም ለኢትዮጵያ " እንኳን ደስ እላችሁ " የሚል መልዕክት አስተላልፏል።
የBRICS ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ሲሆን የአዘጋጇ ሀገር ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ አሳውቀዋል።
(የፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን መልዕክት ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia