TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኩተሬ

በዛሬው ዕለት የዘገየው የኩተሬ የወረዳነት መዋቅር ጥያቄ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጠውና በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ህዝብ በተገቢው ኮታ እንዲወከል የኩተሬ ከተማና ዙሪያው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ድምጻቸውን አሰሙ።

በሰልፉ ላይ ፤ የኩተሬ የወረዳነት ጥያቄ ከ1993 ጀምሮ ከስልጤ የማንነት ጥያቄ ጎን ለጎን ሲጠየቅ እንደነበር የተናገሩት ነዋሪዎች በተለይ ከለውጡ በኋላ በተደጋጋሚ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል ቢባልም እስካሁን ምላሽ ባለማግኘታቸው ቅሬታቸውን ለማሰማት የአደባባይ ሰልፍ ለማድረግ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ፦

- ፍትህ ለኩተሬ፣
- ኩተሬ ወረዳነት ይገባታል፣
- ድምጻችን ይሰማ፣
- ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር፣
- ጥያቄያችን የመልማት ነው ... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተሰምተዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የኩተሬ ከተማና የአጎራባች የገጠር ቀበሌያት ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን ከአሊቾ ውሪሮ ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው እየተነሳ ስላለው ጥያቄ ቤተሰቦቻችን ያነጋገረ ሲሆን ሰልፉ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ገልጸዋል።

በሰልፉ ላይ ከወረዳው ጥያቄ ባለፈ በክልሉ ፍትሃዊ የተቋም ክፍፍል እንዲደረግ እና ፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል እንዲደረግ መጠየቁን አመልክተዋል።

የህዝቡን የመልማት ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ እንዲሰጥም ተጠይቋል።

ፍፁም ሰላማዊ መንገድን በተከተለ ሁኔታ ህዝቡ ለጠየቀው ጥያቄ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#VladimirPutin #NaredraModi

የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ ዛሬ BRICSን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ ያገኙትን እና በመጪው አዲስ አመት ወደ ተግባር የሚገቡትን አዳዲሶቹ የቡድኑ አባል ሀገራት፦
- ኢትዮጵያ፣
- አርጀንቲና፣
- ኢራን፣
- የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣
- ሳዑዲ አረቢያን
- ግብፅን " እንኳን ደስ አላችሁ " ሲሉ የደስታ መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከBRICS መስራቾች አንዷ የሆነችው ሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ናሬድራ ሞዲ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የBRICS ቡድንን መቀላቀል" እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

ሞዲ እንደ ንግድ፣ መከላከያ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ ኢትዮጵያ BRICSን እንድትቀላቀል ህንፍ ላደረገችው ድጋፍ አድናቆታቸውን ችረዋል።

በተመሳሳይ የቻይና መንግሥትም ለኢትዮጵያ " እንኳን ደስ እላችሁ " የሚል መልዕክት አስተላልፏል።

የBRICS ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ሲሆን የአዘጋጇ ሀገር ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ አሳውቀዋል።

(የፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በ5000ሜ ይወክል የነበረው ጥላሁን ሀይሌ ዛሬ ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።

አትሌቱ ለወራት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሃንጋሪ፣ ቡዳፔስት ቢያመራም ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል።

በዚህም ምክንያት አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ከአሰልጣኙ ጋር ከተማከረ በኃላ ዛሬ ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።

አትሌቱ ከዝርዝሩ ወጪ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በውሳኔው ማዘኑን እና ቅሬታውን በማህበራዊ ሚዲያ ካሰማ በኃላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።

ይሄም አትሌቱ ዜግነቱን #ይቀይራል የሚል ቢሆንም አትሌቱ ዜግነቱ መቀየር ሀሳቡም #እንደሌለው እና በቀጣይ ጠንክሮ በመስራት ኢትዮጵያን ወክሎ አቅሙን ማሳየት እንደሚፈልግ ለናሽናል ስፖርት ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ምሽት በተደረገ የ5000ሜ ማጣሪያ ውድድር ሁሉም የኢትዮጵያ ተወካዮች (ዩሚፍ ቀጀልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ፣ ሀጎስ ገ/ህይወት) ወደ ፍፃሜ ማለፋቸው ተረጋግጧል።

Via @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#TikTok #Kenya

በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ሀገሪቱ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

ስምምነቱ የተደረሰው " ቲክቶክ ያልተገቡ ቪዲዮዎችን ያሰራጫል " በሚል እንዲታገድ ከአንድ ግለሰብ ለሀገሪቱ ፓርላማ ከቀናት በፊት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡

የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያው ኩባንያ ቲክቶክ፣ በመድረኩ ላይ የሚወጡትን ቪዲዮዎች መቆጣጠርን በተመለከተ ከኬንያ ጋር በጋራ ይሠራል ሲል የፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት አመልክቷል።

ይህን በተመለከተም ከኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾ ዚ ችው ጋር መነጋገራቸውን ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት፣ " ያልተገቡ ናቸው " የሚባሉ ቪዲዮች ከመድረኩ እንደሚወገዱ ታውቋል።

በአፍሪካ በቲክቶክ ላይ የሚወጡትን የቪዲዮዎች ይዘት በተመለከተ ቁጥጥር ለማድረግ ኩባንያው በኬንያ ቢሮ እንደሚከፍት ዋና ሥራ አስፈጽሚው ሾ ዚ ችው ይፋ ማድረጋቸውም ታውቋል።

ቲክቶክ ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፤ ህዝቡንም እያሳሳተ ነው በሚል ቲክቶክ እንዲታገድ አዛለች። እግዱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በተመሳሳይ ቴሌግራምም እንዲታገድ ውሳኔ ከተሰጠባቸው መተግበሪያዎች አንዱ ነው።

ሶማሊያ አሸባሪ ድርጅቶችና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውሏል በሚል ነው እንዲታገዱ ያዘዘችው።

@tikvahethiopia
የባንክ አካውንት ለመክፈት ወደባንክ ቅርንጫፍ መምጣት ቀረ! ባሉበት ሆነው የአፖሎ ዲጂታል ባንክ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ!

መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ። 
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo 
አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!
#Apollodigitalbank #Apollodigitalproduct #Abyssiniabank #poweredbybankofabyssinia #BankofAbyssinia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all
#Amhara

ልዩ ልዩ ሹመቶች ይሰጥበታል እንዲሁም በክልሉ ሰላም እና ደህንነት ላይ ይመክራል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ እየተካሄደ ነው ተብሏል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረው ዛሬ በአማራ መዲና ባህር ዳር ከተማ ነው።

አንድ ቀን ይቆያል በተባለው በዚህ አስቸኳይ ጉባኤ ምክር ቤቱ በክልሉ በወቅታዊ ሰላምና ደህንነት ጉዳይ አተኩሮ እንደሚወያይና ችግሮች በዘላቂነት በሚፈቱበት መንገድ የቀጣይ አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሏል።

በተጨማሪ ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ሹመቶችን እንደሚሰጥ ተነግሯል።

የአማራ ክልል ባለፉት ወራት በተለይም የልዩ ኃይል መልሶ የማደራጀት ውሳኔ ከተላለፈ በኃላ በተለያዩ ቦታዎች የፋኖ ኃይሎች ከመንግስት ጋር የትጥቅ ግጭት ውስጥ ገብተዋል። 

ምክንያት ተብሎም የተነገረው " የአማራ ህልውና ያሳስበናል፣ ፍትህ እና ነፃነትን እንሻለን ልዩ ኃይሉ መፍረስ የለበትም፣ የክልሉ አስተዳደር የአማራን ህዝብ ጥቅም እያስጠበቀ አይደለም " በሚል ሲሆን በቅርቡ በትልልቅ ከተሞች ሳይቀር የለየለት የከተማ ውስጥ ግጭት ተካሂዶ ነበር።

በነዚህ ግጭቶችም እጅግ በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል። በርካታ ሰው ተጎድቶ ሆስፒታል ገብቷል ፤ ከፍተኛ ንብረትም ወድሟል።

በግጭቱ ወቅት እና ቀደም ብሎ የተለያዩ ሲቪል እና የፀጥታ ኃይሎች " ባልታወቁ  ኃይሎች " እየተባለ ሲገደሉ ነበር።

በትልልቆቹ የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ቢመለስም አሁንም ወጣ ባሉ ቦታዎች የትጥቅ ግጭት እንዳለ የሚጠቁሙ መረጃዎች አሉ።

መንግሥት ከጦርነት ገና ያላገገመውን ክልል እያመሱ ያሉት " የተደራጁ ዘራፊ ኃይሎች " ናቸው ፤ እነዚህን ኃይሎች ላይ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ መስመር እንደሚያሲዝ በመግለፅ ወደ ተግባር ገብቶ እየሰራ እንደሚገኝና እነዚህን ኃይሎች ከተማ ውስጥ ሆነው ይደግፋሉ የሚላቸውን አካላት በቁጥጥር ስር እያዋለ እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል።

በክልሉ በተፈጠረው የለየለት ቀውስ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ፣ የንግድ እና ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ተቋርጦ መቆየቱ፣ በአጠቃላይ ነዋሪዎች የፀጥታ ሁኔታው ባደረሰው ከፍተኛ ጫና የለየለት ችግር ውስጥ መውደቃቸው ይታወቃል።

ፎቶ፦ ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዘንድሮው የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል እንዴት እየተከበረ ነው ?

የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል ካለፉት ዓመታት እጅግ በተሻለ ድምቀት በትግራይ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በዋነኝነት ትግራይ ውስጥ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው።

ከእሁድ ነሃሴ 13/2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መከበር የጀመረው በዓሉ ፤ ነሃሴ 13 ና 14 / 2015 ዓ.ም በዓዲግራት ከተማ በይፋ የማርያ ስነ-ሰርዓት ተከብረዋል።

ነሃሴ 15/2015 ዓ.ም አመሻሽ በመቐለ የሐወልቲ ሰማእታት ቅጥር ግቢ በአሸንዳ ሴቶች የሻማ ማብራት ስነ-ሰርዓት ተከናውነዋል።

ነሃሴ 16 /2015 ዓ.ም አሸንዳ በተምቤን ዓብይ ዓዲ ተከብሯል።

በተጨማሪ ባዛው ዕለት ከሰአት በኋላ በመቐለ በተለመዶ " ባሎኒ ስቴድዮም " ተብሎ በሚጠራው ቦታ ይፋዊ የአሸንዳ ፣ ማርያ ፣ ዓይኒ ዋሪ በዓል አከባበር ተካሂዷል።

በመቐለ ሮማናት አደባባይ የበዓሉ መንፈሳዊ አመጣጥና ትርጉም የሚሳይ ፕሮግራም ተካሂዶ ነበር።

መቐለ በነበረ ይፋዊ የበዓሉ ስነስርዓት ላይ  ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉ አባገዳዎችና ሃደ ስንቄዎች ተገኝተው የነበረ ሲሆን የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የ10 ሚሊዮን ብር  ድጋፍ ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አድርጓል።

የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በዓል ምክንያት በማድረግ 23 ሰአሊዎች ያሳተፈ የስእል እግዚብሽንም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በኤግዚብሽኑ የቀረቡ የቅብ ስእሎች አብዛኞቹ በትግራይ የተካሄደው አስከፊ ጦርነት ያስከተለው ምስቅልቅል ፣ አሸንዳና ውበት ፣ ከጦርነት በኋላ የሚካሄደው የመልሶ ግንባታና ተስፋው የሚያመላክቱ ስእሎች ያካተቱ ናቸው።

የስእል ኤግዚብሽኑ በመቐለ የሰማእታት ሃወልት ሙዚየም የቀረበ ሲሆን እስከ ነሃሴ 21/ 2015 ዓ.ም ይቆያል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የአሸንዳ 2015 ዓ.ም የሞዴሎች ውድድር የተካሄደ ሲሆን ነሃሴ 18 10 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የከተማ ታላቅ ሩጫ በመቐለ ተካሂዷል።

ዘንድሮ መቐለ ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ ድምቃለች ተውባለች ዋና መንገዶችዋ በሰው ተጨናንቀዋል።

ከተማይቱ ፤ በባህላዊ አለባበስና የፀጉር አሰራርና አጋጌጥ በተዋቡ የአሸንዳ ሴቶች ተጨናንቀዋል።

በዘንድሮው በዓል ከትግራይ ውጭ የመጡ በርካታ እንግዶች ያሉ ሲሆን ከነሱ መካከል የውጭ ቱሪስቶች ይገኙባቸዋል። 

ነሃሴ 24 /2015 ዓ.ም በኣክሱም ከተማ የአሸንዳ ዓይኒዋሪ በዓል እንደሚካሄድ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ችለናል።

መረጃውን አሰባስቦ ያደረሰን የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

ፎቶ ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / Mekelle Tikvah Family

@tikvahethiopia