#ኩተሬ
በዛሬው ዕለት የዘገየው የኩተሬ የወረዳነት መዋቅር ጥያቄ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጠውና በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ህዝብ በተገቢው ኮታ እንዲወከል የኩተሬ ከተማና ዙሪያው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ድምጻቸውን አሰሙ።
በሰልፉ ላይ ፤ የኩተሬ የወረዳነት ጥያቄ ከ1993 ጀምሮ ከስልጤ የማንነት ጥያቄ ጎን ለጎን ሲጠየቅ እንደነበር የተናገሩት ነዋሪዎች በተለይ ከለውጡ በኋላ በተደጋጋሚ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል ቢባልም እስካሁን ምላሽ ባለማግኘታቸው ቅሬታቸውን ለማሰማት የአደባባይ ሰልፍ ለማድረግ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ፦
- ፍትህ ለኩተሬ፣
- ኩተሬ ወረዳነት ይገባታል፣
- ድምጻችን ይሰማ፣
- ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር፣
- ጥያቄያችን የመልማት ነው ... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተሰምተዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የኩተሬ ከተማና የአጎራባች የገጠር ቀበሌያት ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን ከአሊቾ ውሪሮ ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው እየተነሳ ስላለው ጥያቄ ቤተሰቦቻችን ያነጋገረ ሲሆን ሰልፉ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ገልጸዋል።
በሰልፉ ላይ ከወረዳው ጥያቄ ባለፈ በክልሉ ፍትሃዊ የተቋም ክፍፍል እንዲደረግ እና ፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል እንዲደረግ መጠየቁን አመልክተዋል።
የህዝቡን የመልማት ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ እንዲሰጥም ተጠይቋል።
ፍፁም ሰላማዊ መንገድን በተከተለ ሁኔታ ህዝቡ ለጠየቀው ጥያቄ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።
@tikvahethiopia